UMMA TOKEN INVESTOR

About me

★ Studies Medicine at Arba Minch University

Followings
1
Translation is not possible.

በ ልባችን ውስጥ ወደ አሏህ ከመመለስ በቀር የማይጠፋ ህመም አለ።ከርሱ ጋር ለብቻ በማውጋት እንጂ የማይወገድ ብቸኝነት አለ።እርሱን በማወቅ በመደሰት፣ የሱን ጉዳይ ደስ እያሉ በመፈፀም እንጂ እፎይታ የማይሰጥ ሀዘን አለ።ከርሱ ጋር አንድ በመሆን፣ ወደርሱ በመሸሽ እንጂ የማንገላገለው ጭንቀት አለ።የርሱን ትእዛዞች፣ ክልከላዎች እና ውሳኔዎች ወደን በመቀበል፣ እስክንገናኘው ታግሶ በመቆየት እንጂ የማይጠፋልን የ ፀፀት እሳት በልባችን ውስጥ አለ። በውስጣችን  እርሱን ብቻ በመፈልግ፣ በመውደድ፣ አዘውትሮ በማስታወስ ለርሱ ራስን በመስጠት ብቻ እንጂ የማይቆም ከፍተኛ ፍላጎት አለ፤ዱንያ ሙሉ ቢሰጠን እንኳን መቼም የማይሞላው አይነት ፍላጎት!

ሀሳቡ የ ኢብኑል ቀይም ነው።በጣም ከምወድለት ኪታቦቹ በ አንዱ ያገኘሁት ነው

T.me/kedegagochu_alem

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

በእጃችን ላይ የሚገኘውን ጸጋ እርሳስና እስክርቢቶም ቢሆን ዋጋቸውን አሳንሰን አንመልከት።

ነብዩላህ ሙሳ صلى الله عليه وسلم በትሯን በተመለከተ ለመሆኑ ይች በቀኝ እጅህ የያዝካት ምንድን ነች ተብሎ ሲጠየቅ

ይችማ

ድጋፌ፣

ለፍየሎቼ ቅጥል ማራገፊያዬ፣

እንድሁም ሌሎች ብዙ ብዙ ጉዳዮቼን የምከውንባት ዘንጌ ነች ማለቱ ጸጋዎችን በብዙ መልኩ መመልከት ተገቢ እንደሆነ ጠቋሚ ነው ይላሉ።

T.me/kedegagochu_alem

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከ ሰለፎች አንዱ የሚያዝናናህ ነገር ምንድነው ተብሎ ሲጠየቅ ፊት ለፊቱ ላይ ያለውን ኪታብ ያዝ አድርጎ የ ሚያዝናናኝ ይህ መጽሃፍ ነው ብሎ መለሰለት።

ጠያቂውም

መጠየቅ የፈልግኩት ከመጸሃፎች ሳይሆን ከሰዎች ሁሉ የሚያዝናናህ ማን እንደሆነ እንድትነግረኝ ነው ሲለው፣

አሊሙም "በ መጽሃፍ ውስጥ ያሉት ስዎች ናቸው " ብሎ መለሰለት።

ጠቃሚ መጽሃፍ ሊክደን የማይችል፣ አስተማማኝ የ እድሜ ልክ ጓደኛ ነው።

T.me/kedegagochu_alem

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

በ ግልፅ የ አሏህ ወዳጅ በድብቅ ደግሞ የርሱ ጠላት አትሁን።

ለ ኢብሊስ፣ ለስሜትህና ለነፍስህ በግልፅ ጠላት ሆነህ በድብቅ ወዳጃቸው አትሁን።

ሁለት ፊት፣ ሁለት ምላስ ያለው ሰዎች እንዲያመሰግኑክ፣ እንዲያከብሩክ አሏህን ፈሪ ሰው እንደሆንክ እያሳየህ ልብህ ግን ከሃዲ የሆነ ሰው አትሁን።

ይህን አጥንት ሰርሳሪ ምክር የለገሰን ቢላል ኢብን ሰዒድ رحمه الله ነው።

ሱብሃን አሏህ!

T.me/kedegagochu_alem

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የወላጆችን ሞት ተከትሎ ለነሱ ዱዓእ ማድረግን መዘንጋት እነሱን ከመበደል ይቆጠራል ያሉ ሰለፎች ነበሩ።

T.me/kedegagochu_alem

Send as a message
Share on my page
Share in the group