Translation is not possible.

በ ልባችን ውስጥ ወደ አሏህ ከመመለስ በቀር የማይጠፋ ህመም አለ።ከርሱ ጋር ለብቻ በማውጋት እንጂ የማይወገድ ብቸኝነት አለ።እርሱን በማወቅ በመደሰት፣ የሱን ጉዳይ ደስ እያሉ በመፈፀም እንጂ እፎይታ የማይሰጥ ሀዘን አለ።ከርሱ ጋር አንድ በመሆን፣ ወደርሱ በመሸሽ እንጂ የማንገላገለው ጭንቀት አለ።የርሱን ትእዛዞች፣ ክልከላዎች እና ውሳኔዎች ወደን በመቀበል፣ እስክንገናኘው ታግሶ በመቆየት እንጂ የማይጠፋልን የ ፀፀት እሳት በልባችን ውስጥ አለ። በውስጣችን  እርሱን ብቻ በመፈልግ፣ በመውደድ፣ አዘውትሮ በማስታወስ ለርሱ ራስን በመስጠት ብቻ እንጂ የማይቆም ከፍተኛ ፍላጎት አለ፤ዱንያ ሙሉ ቢሰጠን እንኳን መቼም የማይሞላው አይነት ፍላጎት!

ሀሳቡ የ ኢብኑል ቀይም ነው።በጣም ከምወድለት ኪታቦቹ በ አንዱ ያገኘሁት ነው

T.me/kedegagochu_alem

Send as a message
Share on my page
Share in the group