UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

👉:-ልብ እና አንጎል ጠባቂው መድሐኒት: አሞክስሊን!!

👉:-የልብ ህመም የሰዉ ልጆችን በቀዳሚነት የሚያጠቃ የውስጥ ደዌ ችግር ነው።  ልክ እንደኛ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ነዋሪዎች ላይ የሚከሰተው የልብ ችግር ሳይንስ ማጥፋት የሚችለው ቢሆንም እኛን እያጠፋን ይገኛል።

👉:-ልብ ስትታመም አብሮ አደጋ ላይ የሚወድቀው አንጎል ነው።Amoxicillin የልብ ችጎርን እና እስትሮክን የሚከላከል:የሚጠብቅ ፍቱን መድሐኒት ነው።

👉:-የቶኔሲልና ላንቃ ኢንፌክሺን መዘዙ በትኩሳት የሚቆም አይደለም፤ወደ ልብ በመዛመት ልብን በዘላቂነት የሚያጠቃ አደገኛ ና የልጆችን መቦረቂያ ዘመን የሚነጥቅ ተላላፊ በሽታ ነው። ህመሙ የችግር ህመም ነው። ችግሩ የኢኮኖሚና የአመለካከት ነው።

👉:-በኛ ሀገር በህፃናት ላይ የሚከሰተው  የልብ ህመም መነሻው ብዙ ግዜ ኢንፌክሺንን በግዜና በተገቢው መልኩ ባለማከም የሚመጣ ነው። የቶንሲልና ላንቃ ኢንፌክሺን አንዳንድ ግዜ የቆዳ ላይ መግል ቁስል ተገቢውን ህክምና ካላገኘ ቀስ ብሎ ወደ ልብ ይዛመታል። የሚዛመተው ብዙ ግዜ ኢንፌክሺኑ ሳይሆን ለኢንፌክሺኑ የሚመረተው ፀረ-ተህዋሲያን ማምከኛ አማካኝነት ነው።

👉:-ችግሩ ሰዉነት እራሱን በራሱ ማጥቃት በመጀመር የሚፈጠር ነዉ ።ለዚህ ጣጣ የሚዳርገው በመገፋፋትና በማላኮስ የሚተውነው ደግሞ የቶንሲልና ላንቃ ኢንፌክሺን መንስኤ የሆነው ባክቴሪያ ነው።

👉:-በሀገራችን ህፃናት በልብ ህመም ከታመሙ አንደኛው በተፈጥሮ  የልብ ክፍተት መኖር ፣ ሁለተኛውና አሳሳቢው በዚህ ኢንፌክሺን መዘዝ የሚመጣው የልብ በር መብገን ነው።

👉:-በዚህ ሰዓት የቶንሲልና ላንቃ ኢንፌክሺን ምልክቶችን የማያውቅ አለ ተብሎ አይታሰብም። ችግሩ ማሳከምና ህክምናውን በአግባቡ መጨረስ ላይ የተተበተበ ነው።

👉:-ከፍተኛ ትኩሳት፣የቶንሲልና ላንቃ ላይ ዙሪያ መቅላት እና ነጭ ነጭ ነጠብጣብ ጣል ጣል እና ማስመለስ ለመዋጥ መቸገር ዋና ዋና ምልክቶች ናቸው። የቶንሲል እና የላንቃ ብግነት  በተለያየ ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል(በጀርም እና በሙቀት መለዋወጥ).ከጀርሞቹ መካከል በባክቴሪያ የሚመጣው ነው ለልብ ጠንቅ የሚሆነው። ሆኖም ይኸንን በትክክል ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ በመሆኑ እነዚህ ምልክቶች የታዩበት ህፃን የጅምላ ህክምና ማግኘት ይኖርበታል።

👉:-*ከሁለት አመት በታች ይኸ ባክቴሪያ የማጥቃት እድሉ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑና ዋና መንስኤዎቹ ቫይረሶች ስለሆኑ ህክምናው የድጋፍ ህክምና ነው። አሞክስሊን መስጠት አያስፈልግም።

👉:-እድሜአቸው ከሁለት-3 አመት በላይ የሆኑ ህፃናት ግን አሞክስሊን  መውሰድ አለባቸው።ችግሩ ያለው ከዚህ ላይ ነው።

ችግር ፩ )

መድሐኒቱ በየቤቱ ና ጎረቤት በመገኘቱ አስፈላጊነቱ ተመናምኗል። በዚህም የሚያድን መስሎ ያለመታየት እሳቤ ዳብሮ ከፍተኛ መሰናክል እየፈጠረ ይገኛል። መድሐኒቱ ልብን የሚጠብቅ አስተማማኝና ምቹ መድሐኒት ነው። ከልብ የሚነሳ ስትሮክ መንስኤን በመከላከል እስተሮክን ይከላከላል።

ችግር ፪)

ከሁለት ቀን በኋላ ትኩሳቱ ሲጠፋና ልጆቹ ወደ ነበሩበት የጤና ሁኔታ ሲመለሱ "ይበቃዋል ደግሞ ከተለመሰበት እሰጠዋለሁ " በሚል ቸልተኝነት/አለማወቅ መድሐኒቱ መድሐኒትነቱን እንዲያጣ የሚያደርግ ሰፊ የማህበረሰብ ችግር ይታያል። መድሐኒቱ በዋናነት የሚሰጠው ትኩሳት ለማብረድ ሳይሆን የልብ ጤንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ነው።

👉:=ይኸን ጥቅም ለማግኘት መድሐኒቱ አስር ቀን ያለ አንዳች ማቋረጥ መስጠት የቤተሰብ ግዴታ ነው።ባለሙያዎችም የሚወስደውን የቀን ብዛት በትክክልና በአፅንዖት ማስረዳት ይገባቸዋል። ለአምስት ቀን/ሰባት ቀን በመስጠት የቶንሲል ኢንፌክሺኑን እንጂ ማከም የሚቻለው በልብ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጠንቅ መከላከል አይቻልም።

👉:=ወላጆች አሞክስሊንን የልጆቻቸው ልብ ጠባቂ አድርገው በማሰብ ሲያስፈልግ በትክክልና በአግባቡ መስጠት ይገባቸዋል።"ጠባቂ ፈጣሪ ነው "ብላችሁ እንደማትተቹ አምናለሁ።

👉:-ትኩሳቱ ከጀመሩ በዘጠኝ ቀናት ውስጥ ተጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት በመውሰድ ብቻ ነው የልብ ጥቃትን መከላከል የሚቻለው።

👉👉:-በዚህ የልብ ችግር የተጠቁ ህፃናት ለእስትሮክ ተጠቂዎች ናቸው። መድሐኒቱ ልብን ብቻ ሳይሆን የሚጠብቀው አንጎልንም ጭምር ነው። ብዙ ወጣት ሰዎች በስትሮክ ሲጠቁ የሚታዩት በዚህ ኢንፌክሺን መዘዝ በመጣ የልብ ጤና እክል አማካኝነት ነው።

👉:-አሞክስሊን የደጅ ጠበል እንደሚባለው በቤታችን መገኘቱ ሊጠቅመን ሲገባ ሳንጠቀምበት እየተጎዳን መሆኑን ልብ ብለው ለሚያስፈልገው ልጅዎት ይስጡ፤ይከላከሉ፤ይጠብቁ።

👉👉:-አሞክስሊን እና ቤተ-ዘመዶቹ በሁለት መንገድ የመከላከል ስራ ይሰጣሉ።

፩ የመጀመሪያ ደረጃ መከላከል፦የልብ ችግር ከመፈጠሩ በፊት

፪ የልብ ችግር ከተፈጠረ በኋላም ችግሩ እንዳይባባስና አጣዳፊ እንዳይሆን ይከላለካሉ። የሚያዋጣው የመጀመሪያ መከላከል ላይ ከፍተኛ ትኩረት ማድረጉ ነው።

*በዚህ ሰዓት በዚህ ኢንፌክሺን መዘዝ የመጣን የልብ ችግር በቀዶ ጥገና ለማከም ያለውን  ወረፋ ያየና የችግሩ ስፋትና ክብደትን የተረዳ መጮኽ እንዳለብን ይረዳል። የምንጮኸው በቀላሉ ማድረግ የምንችለውን ባለማድረጋችን ሰፊና ውስብስብ ለሆነ የልብ ችግር  ልጆች በለጋ እድሜአቸው እየተጠቁ ስለሆነ ነው።

*መከላከል ሁነኛ መንገድ ነው፤ለዚህ ደግሞ አሞክስሊን በእጆዎ ነው።በአሞክስሊን ጠብታ ልጆችዎን መታደግ ይችላሉ፤አይዘናጉ።

👉:=አሁን እንኳ አሞክስሊንም አንድ ሺ አምስት መቶ ድረስ እየተሸጠ መምጣቱን እያየን ነው።በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዳንሆን ይታሰብበት!

መልካም ጊዜ!

ዶ.ር መስፍን በኃይሉ

@HakimEthio

https://ummalife.com/Meryemhassen

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሁሉንም የኮሚኒኬሽን መንገዶች ሁሉ ዘጉ፤ በዓለም አቀፍ ህግ መጠቀም የተከለከለውን የፎስፎረስ ቦንብ በንፁሃን ህፃናት፣ እናቶችና አዛውንት ላይ ሲያዘንቡ አደሩ።

ይህ ሁሉ የሚሆነው “ስልጡን” ነኝ በሚለው ዓለም ገደብ የለሽ ድጋፍ እንደሆነ ስታይ የሚከተለውን የልእለ-ኃያሉን ቃል ታስታውሳለህ፦

“በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት (ምእምናን መከራ) ብጤ ሳይመጣችሁ ገነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልክተኛውና እነዚያ ከርሱ ጋር ያመኑት «የአላህ እርዳታ መቼ ነው?» እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ነካቻቸው፤ ተርበደበዱም፡፡ ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው (ተባሉም)፡፡” (አል-በቀራህ:214)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#umma_life__ በቀላሉ__Follower__እናሳድግ

#ሙሉውን_ Step_ቀድመው_ያንብቡ!

1 ፕሮፋይላችሁ ላይ ገብታችሁ ከላይ በቀኝ በኩል ያለውን ነጠብጣብ በመንካት #profile_link አችሁን copy አድርጉ

2 ከዛ እዚህ ፓስት ስር ገብታችሁ comment ላይ past አድርጉት

3 ለምሳሌ የኔን አካውንት https://ummalife.com/Mamekamil

4 ኮመንት ላይ ያሉትን ሁሉንም ሊንክ በመንካት follow አድርጉ!

5 follow አድርጋችሁት ያልመለሰ ሰው Replay አድርጉለት

6 ይህን post ሼር ማድረግ ግዴታ ነው ካልሆነ ፓስቱ ይደበቃል!!

Mohammed Kamil | UmmaLife

Mohammed Kamil | UmmaLife

Mohammed Kamil: Mohammed Kamil. Nikname: @Mamekamil | One Ummah — One Network - was created as a response to the Internet technology needs of Muslims and all adherents of traditional value
Send as a message
Share on my page
Share in the group