UMMA TOKEN INVESTOR

mussa ebrahim shared a
Translation is not possible.

ይህን ሰምና ወርቅ ያዘለ ጹሁፍ አምብቡልኝማ

እንደ ሰማሁት በጹሁፍ ቀይሄ አመጣሁላችሁ

አንድ ታላቅ የአረቡ አለም አሊም በዳአዋ መድረካቸው ላይ ያጋሩት ኮመዲ አዘል ቁም ነገር ያለው ንግግር ነው ።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አንድ መንድር ላይ የሚኖር እጅግ በጣም አጭበርባሪ

ሰው ነበር ይህ ሰው ህይወቱ የሚመራው አጭበርብሮ በሚያገኘው ገንዘብ ነው

አንድ አህያ ነበረችው አንድ ቀን አህያው አፍዋን ከፍቶ ወርቅ ሞላባት እና ገቢያ ሊሸጣት አወጣት

አህያይቱ ገቢያው ላይ አስጮሀት ስትጮህ ከአፍዋ ወርቆቹ ወዳደቁ ገበያተኞቹ ተገመው ያዩዋት ሊገዙዋት ቋመጡ ስንት ናት ስንት እቺ ወርቅ ምትተፋ አህያ እያሉ ገቢያው አደሩለት እሱም ውድ ነው ውድ ነው እያለ አጓራ አንዱ ቱጃር በውድ ዋጋ ገዝቶት ቤቱ ወሰዳት ቤት አስገብቶ ቢያጮሀት ከአፍዋ ምንም ጠብ አላለም

በቃ ተሸወድኩ አለና የሰፈሩን ሰው ይዞ አጭበርባሪውን ሰው ፍለጋ ሄዱ እና ቤቱ ደረሱ እሱ ከሩቅ አይቶዋቸው ስለ ነበር ተደበቀ ቤቱ ሲገቡ ሚስቱ ነው ያለችው ባልሽ ሸውዶናል የት አለ አሉዋት እስዋም አሁን ወጣ ቆዩ ይሄ ውሻ ልላክበት አለችና አንድ ውሻ ፈትታ ለቀቀች እናተ እዚህ አረፍ በሉ ውሻይ ይዞት ይመጣል አለቻቸው

ትንሽ እንደ ቆዩ ሰውየው ውሻውን ይዞ መጣ

ሰዎቹ ተገረሙ የመጡበት ጉዳይ ረስተው ይሄ ለማዳ ውሻህ እንግዛህ እያሉ ቤቱን ገቢያ አደረጉት እሱም በውድ ዋጋ ለአንዱ ሸጠለት ገዢው ቤት ወስዶ ውሻው ለአደን አሰማራው በዛው ጠፍቶ ቀረ አሁምን ተመልሰው ሸወደን ያ ሰው እንሂድ ብለው ቤቱ ገቡ ሲገቡ የለም ሚስቱ ናት ያለችው የት አለ ባልሽ ሸውዶናል አሉዋት ቆዩ ልጥራው ብላ ጠርታው መጣች

ልክ ሲገባ ቡና አላፈላሽላቸውም አላት እስዋም አው አለች

ለምን አለና ሚስቱን በአቴፊሻል ጩቤ ወጋት እስዋም ነገሩን ስለ ምታቅ ቀድማ በልብስዋ ውስጥ ደም መሳይ ነገር ይዛ ነበርና እሱን አፍሳ ወደቀች ሰዎቹ ግራ ገባቸው

አጭበርባሪው ሰውዬ ቆዩ ቆዩ አንዴ አለና ከኪሲ የሆነ ዋሽት መሳይ ነገር አውጥቶ በዋሽንት አጠገብዋ ሄዶ አዜመለት እስዋም ተነስታ ቆመች ከዛ ቡና አፈላች እየጠጡ ሳላ ይሄ ጉደኛ ዋሽትህ ሽጥልን አሉት እሱም ይሄማ ውድ ነው አላቸው ቢሆንም ሽጥልን የኛ እዳ አለብህ አሉት እሱም እሺ ብሎ ለአንዱ ሸጠለት ።

ገዢው ቤት ገባና ለሚስቱ ውዴ ገራሚ ዋሽት ገዛሁ አለና ሚስቱን በጩቤ ወጋት ዋሽቱ ቢነፋ ቢነፋ ሚስቱ ሆዬ አሸልባለች ለጎረቤቱ ሞክርልኝ ብሎ ሰጠው እስም ሚስቱን ወግቶ ዋሽቱ ሚለው ቢለው አሸልባች በዚህ መልኩ መላው የመደሬው ሰዎች ሚስቶቻቸገ ገደሉ

አባ ወራዎቹ ተናደው ገንፍለው ያን አጭቤ ሰው በቁም አገለውም ባህር ውስጥ ነው ምንጨምረው ብለው ዝተው አጭቤው ጋር መጡ

አፍነው ያዙት መዳበሪያ ውስጭ ጨምረው ተሸከመው

ባህር ወደ አለበት እሩቅ መንገድ ጉዞ ጀመሩ

በጉዞ መሀል አረፍ አሉ ደካም አለና እንቅልፍ ሸለባቸው

አጭቤው ሰው ከመዳበሪያው ውስጥ በንቃት አለ

አንድ ምስኪን ገበሬ በዛጋ አለፈ እከሌ ብሎ ጠራው ፍታኝ አለው ማን ነው ያሰረህ አለው እነዛ ሰዎች በግድ አግባ ትዳር ያዝ አሉኝ እና አንዲት የሀብታም ልጅ ሊድሩኝ ነው እኔ እንቢ ስለ አሉኩ ነው አለው ገበሬው ሰው ፈታው

አጭቤው ሰው ለምን አንተ አታገባትም እቺን ሀብታብ እንስት አለው እሺ አገባታለሁ አለ ገበሬው በቃ ና በኔ ቦታ ብሎ ገበሬው በመዳበሪያ አስሮ ወደ ቤቱ አቀና

ሰዎቹ ከእቅልፍ እንደ ነቁ ማዳበሪያው ተሸክነው ባህር ውስጥ ጣሉት ገበሬው በማያቀው ነገር ተሰዋ ሰዎቹ ሰፈራቸው ሲመለሱ አጭቤው ሰው አለ ተገረሙ እንዴት መጣህ አሉት እናንተ ከባህሩ እንደ ጣላቹኝ አንዲት ልእት ልጅ አገኘችን ማዳበሪያው ፈታ ብርም ሰጥታ ከባሽሩ አወጣችኝ እንዳምው አለችኝ አለ አጭቤው ምን አለችህ አሉት የባህሩ ዳር ላይ ስለ ጣሉህ እኔ አገኘሁህ መሀል ላይ ቢጥሉህ ኖሮ ታላቅ እህቴ አግታህ ብዙ ብር ትሰጥህ ነበር አለችኝ አላቸው እና ታላቅ እህትዋ ከባህሩ መሀል ላይ አለች አሉት አው አላቸው በቃ እኛም ሄደን ብር አናምጣ ብለው ከባህሩ መሀል ላይ ሰምጠው ቀሩ

አጭበርባሪው ሰውዬ ብቻውን ከሚስቱ ጋር መንደሩን እንደ ፈለገ ይኖርበት ጀመር ።

ታሪክ አበቃ ቁም ነገሩ ወዲህ ነው

ያ አጭበርባሪው ሰው እስራኤል ነው

ሚስቱ አሜሪካ ናት

ህዝቦቹ አረቦች ናቸው ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
mussa ebrahim shared a
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
image
image
image
image
image
+8
Send as a message
Share on my page
Share in the group
mussa ebrahim shared a
Translation is not possible.

#ሳውዲ_የታሰረችው ከ4 ወር በሗላ የተጠየቀችውን ብር ካልከፈለች #ሞቷን_አስቀድሞ_የተነገራት #የቡታጅራ ተወላጅ የሆነችው #የለይላ_ኑርሰቦ ጉዳይ #የሁሉም ሰው ጉዳይ ስለሆነ #ልንደርስላት ይገባል፡፡

###################

የለይላ ኑርሰቦ ጉዳይ #በቤተሰቦቿ :#በበጎ_አድራጎት_ማህበሮች #በእድሮች #በነጋዴዎች #በአርሶ_አደሮች #በመንግስት_ሰራተኞች #በወረዳ #በከተማ #በዞን #በኢትዮ_ሳውዲ ብቻ የሚፈታ ችግር አይደለም የእሷ ጉዳይ #ሰው_ለሆነ ሁሉ ጉዳይ ነው ቢሆንም እኛ #ያልጀመርነው ችላ ያልነው ጉዳይ መቼም #ኢትዮ_ሳውዲ_ኢምባሲ ትኩረት ይሰጠዋል ብሎ መጠበቅ ከባድ ነው፡፡

እውነት ለመናገር እቺ ልጅ #እህትክ_እህትሽ ብትሆን በዚህ ልክ አትዘናጋም ነበር? እባካችሁ ነግ በኔ ነው #እንተጋገዝ_አንጨካከን ለበጎ ተግባር ማንንም መጠበቅ አያስፈልገውም፡፡

#የቡታጅራ ህዝብ ደግሞ #በጎነት ወትሮም #ልማዱ ነው አሁንም በእህቱ #የሚጨክን አንጀት ያለው ሰው የለም #የመጠባበቅ ጉዳይ ሆኖበት ይመስለኛል፡፡

######ጉዳዩ እንዲህ ነው####

11 ዓመት እስር ቤት ያለች እህት 😭

ለይላ ኑርሰቦ ትባላለች ። የቡታጅራ ልጅ ናት ። ለይላን እናት ና አባቷም መሬት ሽጠው በ2005 ነበር ወደ ሳውዲ የላኳት ። ቤተሰቤን እለውጣለሁ ብላ ሳውዲ ከሄደች 11 ዓመት ሆናት ...

ነገር ግን

ሳኡዲ በመጣች በ5 ወሯ ሰውየው ሊደፍራት ሲታገል " ፈጣሪ የሚጠላው ነገር ነው ፣ ሀራም ነው " ብላ እሱን እማታለው ብላ ሳታቅ የአሰሪዋን ልጅ መታቻት ህፃኗ ከ 5 ወር በኃላ ሞተች 😪

የሳውዲ ህግ የገደለ ይገደል ነውና በለይላም የሞት ፍርድ ተፈረደባት 😪 በስተመጨረሻ የሳውዲ ቃዲዎች ጉዳዩን በጥልቀት እንደገና በማየት ፍርዱን በብር ቀየሩላት፡፡

ምክንያቱም

1ኛ ልጅቷን የገደለቻት አስባ አለመሆኑ(በስህተት መሆኑን)

2ኛ ልጅቷ የሞተችው ከመታችት ከ6 ወር በሗላ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት ነው፡፡

እህታችንን ከእስር ቤት ለማውጣት 2 ሚሊዮን የሳውዲ ሪያል በኢትዮጵያ 60,000,000 ብር ተጠይቋል ይህንንም በአንድ ዓመት ውስጥ አስገቡ ተብሏል ።

ለቤተሰቡ ከኢምባሲ መረጃው የደረሰን ውሳኔው ከተወሰነ ሊጠናቀቅ 4 ወር ብቻ ሲቀረው ነው ይላሉ፡፡

ቤተሰቦቿ እያለቀሱ ነው

"ልጃችን ከሀገር ከወጣች 11 ዓመት ነው 11ኑንም ዓመት ታስራለች ፣ የሞት ፈርዶ ጠብቋታል ፣ 11 ዓመት ጠብቀን ትመጣለች ብለን ስንጠብቅ ልጃችንን ሊገድሉብን ነው 😪 የልጃችንን ዓይን ማየት እንፈልጋለን 😭 11 ዓመት እያለቀሰን ነው😭

እርዱን ፣ ልጃችንን አድኑልን

እኛን ለመለወጥ ነበር ሳውዲ የወጣችው 😪 " እያሉ ያለቅሳሉ

አባቷ ሲያለቅስ ያሳዝናል 😭

እናቷ ስታለቅስ ታሳዝናለች 😭

አሁን የምትገኘው ሳውዲ መነዝ እስር ቤት ላይ በስቃይ ነው

እህታችንን ከሞት ፍርድ ከስቅላት እናድናት 🤲

መርዳት ባትችሉ share በማድረግ የሚረዳትን ሰው ያፈላልጉ

እህታችንን ለመርዳት 1000571065065

image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
mussa ebrahim shared a
Translation is not possible.

من الوهلة الأولى قد تحسبونه فيلما سينمائيا💔

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group