UMMA TOKEN INVESTOR

About me

I don't worry if i'm worthy I will just smile and live my life

Translation is not possible.
መውሊድ የማናከብረው ነቢዩን ስለምንወዳቸው ነው።ምንም እንዳትከራከረኝ እርግጠኛ ነኝ።
ውዴታን በትዕዛዝ እንጂ በአመፅ አንገልፅም። የምቶደውን አካል ትታዘዘዋለህ እንጂ አሻፈረኝ አትለውም። አይይይ..ካልክ መንገዱን እሾህ ያድርግልህ ነው የምልህ
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች
1000646950647
👉ሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚገኙ በማህበራዊ ሚዲያና በተለያየ መንገድ የሚገናኙ ስለ ጎርፉ አደጋ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ የሚገኙ የስልጤ ተወላጆች ለተፈናቃዮች የበኩላቸውን የቁሳቁስ፣ የአልባሳት፣ የምግብ፣ የገንዘብ...ድጋፍ ለማሰባሰብ ነይተው በመነጋገር አስተባባሪ መርጠዋል። ከአስተባባሪዎቹም 3ቱ ተመርጠው በጋራ የባንክ አካውንት ከፍተዋል። ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ ስልካቸውን ፈልገን እናመጣላቹሃለን። የከፈቱት የባንክ አካውንት ደግሞ ከታች የተያያዘው ነው። ሁላችንም የቀኩላችን እናድርግ።
👉ይህ ጉዳይ የስልጤ ብቻ ጉዳይ ስላልሆነ ሌሎች ማህበረሰቦችንም የበኩላቸውን ወገናዊና ሰባዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ እናስተባብር።
👉አንድ ሆነን በአንድ ቋት ለተረጂዎች እንድረስ። ይህ በሁለቱም ወረዳ ያሉትን ተፈናቃዮች ያገኛትን ነገር ያደርሳል። በለተይ በተለይ በአይነት መደገፍ የምትፈልጉ ከስር አድራሻ አለላችሁ!!
👇👇👇
አዲስ አበባ የምትገኙ
በአይነት አልባሳት፣ ብርድልብስ፣ ፎጣዎች፣ ፓምፐርስ፣  የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስና ምግብ ነክ ነገሮችን በበጎ ፍቃደኝነት የሚንቀሳቀሱ ወንድም እህቶች አሉ አድራሻም ተዘጋጅቷል መለገስ ማቀበል የምትፈልጉ በስልክ ቁጥሮች ደውሉ ባላችሁበትም መተው ይወስዳሉ።
  +251911079793 አዲስ አበባ ማንኛውም አከባቢ
   +251913442474 አዲስ አበባ
   +251927368484 አለም ባንክ አግኖት ዳዛይን
    +251943892917 ቤተል
    +251912351944  ቤተል
     +251975387161  መርካቶና አከባቢው
ለወገን_ደራሽ_ወገን_ነው!!
ሼር ሼር ሼር በማድረግ እናዳርሰው!!
https://t.me/Ibnugarad
Telegram: Contact @Ibnugarad

Telegram: Contact @Ibnugarad

يا مقلب القلوب ثبت قلبي على دينك
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
እንኳን ደስ አላችሁ የ10ኛ ዙር ተማሪዎች
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
“ዓይኔ ለአፍታ ቢበራ ላየው የምመኘው ቁርአንን ነው“፡-የዳሊ ኩምቤ ኢማም
***************************
“ከ10 ትውልድ በፊት በመንደራችን ትኖር የነበረች አንዲት ሴት የሌላ ዓለም ፍጡር በህልሟ ተገልጦ እጅግ ብልህ እና አስተዋይ ዓይነ ስውር ልጅ እንደምትወልድ ይነግራታል፡፡
ይቺ ሴት በህልሟ እንዳየችው ፈጣሪውን የሚፈራ በሳል ዓይነ ስውር ልጅ ትወልዳለች፡፡
እኔን ጨምሮ በትውልድ ቅብብሎሽ ዛሬ ላይ የደረስን የእርሷ ዘሮች በሙሉ ዓይነ ስውር ነን፡፡ በመንደራችን ከሁለት ሰው ውስጥ አንዱ ዓይነ ስውር ነው”
ይህ ጭው ባለው የሰሃራ በረሃ ከዓለም ተገልለው የሚኖሩት የ’ዳሊ ኩምቤ’ መንደር ነዋሪዎች ኢማም ንግግር ነው፡፡
ልበ ብርሃኑ ኢማም ‘ቡህ’ ከመንደራቸው ነዋሪዎች ውስጥ ከፊሉ ዓይናማ ከፊሉ ደግሞ ዓይነ ስውር ሊሆኑ የቻሉት ከላይ በተረኩት የህልም ትንቢት እንጂ በሌላ አይደለም ይላሉ፡፡
በሰሃራ በረሃ እምብርት ከሞሪታኒያ ዋና ከተማ ‘ኑዋክቾት’ በ1 ሺህ ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ”የዓይነ ስውራን መንደር“ የዓለምን ትኩረት ስባለች፡፡
እዚህ ስፍራ ለመድረስ የበረሃውን ንዳድ ታግሶ የአሸዋውን ባህር ለሁለት ቀናት ማቋረጥ ግድ ይላል፡፡
በረሃው ከሚያጥበረብር ብርሃን ውጭ ለዓይን ወሰን የሚሆን አንዳች ተፈጥሯዊ ልምላሜ እና ሰው ሰራሽ ስልጣኔ አይታይበትም፡፡
መብራት፣ ስልክ፣ ኮምፒዩተር፣ ኢንተርኔት፣ መኪና፣ ፎቅ፣ ሆቴል፣ ቢሮ…ሁሉም የሉም፡፡
እንደነገሩ ከተሰሩት መኖሪያ ቤቶች ውጭ መንደሯ ያሏት ሁለት ትልቅ ሀብቶች አንድ መስጅድ እና አንድ መድረሳ ቤት ናቸው፡፡
ኢማሙ ውኃ እንደወርቅ የሚቆጠርባትን በርሃማዋን ሀገር ሞሪታኒያን ያጠጡት “አያቶቼ ናቸው” ይላሉ፡፡
“አላህ (ሱ.ወ) ለእኛ ከሰጠን ድንቅ ስጦታዎች ውስጥ አንዱ በዚህ ጭልጥ ያለ በረሃ ውስጥ የውኃ ምንጮች የት እንዳሉ ማወቅ ነው፡፡
ሞሪታኒያ ውስጥ ያሉ የውኃ ምንጮችን በአብዛኛው ፈልጎ ያገኘው እንደኔው ዓይነ ስውር የነበረው አባቴ ነው፡፡ አያቶቼም ውኃ የት እንዳለ የማወቅ ልዩ ጸጋ ነበራቸው”
ሌላኛዋ በስም ያልተጠቀሰች የመንደሩ ነዋሪ ፈጣሪ ግልጡን እንዳያዩ ከልክሎ ስውሩን የሚያዩበትን ረቂቅ ዓይን ልባቸው ላይ የማብራቱ እንቆቅልሽ ለእርሷም አጃኢብ የሚያሰኝ መሆኑን ትገልጻለች፡፡
እንደ እሷ ዓይነ ስውር የሆኑ ወንድም እና እህቶቿን እናታቸው እንደምትንከባከባቸው እነሱም እናታቸውን በመታዘዝ የልጅነታቸውን አጉድለው እንደማያቁ ትናገራለች፡፡
“የመንደሯን መንገዶች የቤቴን ያህል አውቃቸዋሁ፡፡ መስኪድ ለመሄድ፣ ውኃ ለመቅዳት እና ሌሎች ጉዳዮችን ለመከወን ምንም የሚቸግረን ነገር የለም፡፡ መሪ ሊያስፈልገን የሚችለው ከመንደሯ ከወጣን ብቻ ነው” ትላለች፡፡
ከፊሉ ዓይናማ ከፊሉ ዓይነ ስውር በሆነባት በዚህች መንደር ወንዱም ሴቱም ለኢስላማዊ ዕውቀት ያላቸው መሰጠት የሚያስደንቅ ነው፡፡
ሳቂታዋ ዓይነ ስውር ዓለም ላይ ቁርአን እንደማጥናት የሚያስደስታት ምንም ነገር እንደሌለ ትገልጸለች፡፡
የዳሊ ኩምቤው ኢማም ቡህ “ዓይንዎ ለአፍታ ቢበራ ምን ለማየት ይጓጓሉ?” ተብለው ሲጠየቁ መልሱን ለመስጠት ጥቂት ማሰብ አላሻቸውም፡፡
“ዓይኔ ለአፍታ ቢበራ ላየው የምመኘው ቁርአንን ነው፡፡ በአይምሮዬ ሸምድጄ የማስተምረውን የፈጣሪን ቃል በእጄ መጻፍ ካለመቻሌ በቀር አንዳች አልጎደለብኝም “ ይላሉ፡፡
ከ10 ትውልድ በፊት በህልም የተነገረው “ራዕይ“ አካል በመሆናቸው ደስተኛ መሆናቸውን የሚገልጹት ኢማሙ ፈጣሪ ያደረገላቸውን ለመዘርዘር አቅሙ እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡
ኢማሙ ዓይን ማስተዋልን፣ መታዘዝን እና ትህትናን አጥፍቶ ፈጣሪን ወደ ማየት ካላደረሰ ለእርሳቸው ኪሳራ መሆኑን በአባትነት መክረው ሲያበቁ፣ “የቁርአን ማስተማሪያዬን ላሳይህ” ብለው የ‘ፕሮጀክት ሃፒነስ’ ጋዜጠኛውን እጅ ይዘው ወደ መድረሳ ቤታቸው መሩት፡፡
EBC
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
ነጃሺ ለነብዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) የላኩላቸው ደብዳቤ የት ነው የሚገኘው?
ነጃሺ ለነብዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) የላኩላቸው ደብዳቤ በቱርክ ይገኛል ተብሎ እንደሚገመት አንድ ትልቅ ሰው ካሁን በፊት አጫውቶኝ ነበር። ይህ እንደ አንድ ፍንጭ ይዤው ቆይቼአለሁ። ዛሬ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ፍንጭ አግኝቼአለሁ።
ይህ ተጨማሪ ፍንጭ ያገኘሁት ፕሮፌሰር ሑሴን አሕመድ (1996) "Aksum in Muslim historical traditions" ከተሰኘው ፅሑፍ ነው። በዚህ ፅሁፍም ነጃሺ ለነብዩ ሙሐመድ የላኩላቸው ደብዳቤ በቱርክ እንደሚገኝ የሚጠቁም ተጨማሪ ማስረጃ አግኝቼአለሁ።
ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ በመስከረም 13/1924 (እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር) እትሙ ላይ የግብፁ አሕራም ጋዜጣ ማርች 13/1931 ይዞት ወጥቶ የነበረው አጭር ማስታወሻ አስነበቦ ነበር። መረጃው በቤሩት የአሕራም ጋዜጣ ዘጋቢ የነበረ ሰው የቱርኩ ሱልጣን ዓብድል ሐሚድ ልጅ የሆነው ሳሊም አግኝቶት እንደነበረ እና የአክሱም ነጉስ ነጃሺ ለነብዩ ሙሐመድ የላኩላቸው ደብዳቤ በእጁ እንደሚገኝ ደብዳቤውም አባቱ በሰርጉ ጊዜ በስጦታ የሰጠው እንደሆነ እንደነገረው የሚያትት ነው።
ይኸው ፅሑፉ:-
The Amharic newspaper,  Berhanenna Salam , in its issue of Meskerem 13.1924 E.C., carried a story, based on a report published in al Ahram of 13 March 1931, about the despatch from Beirut of a cable by a correspondent of the Egyptian daily in which he said that he met Salim, a son of the Turkish Sultan, Abd Al Hamid (1864-1909), who claimed that the letter of the Aksumite ruler to the Prophet was in his possessi, and that it had been given to him, by his father as a wedding present.
ሙሀመድ ሀጎስ
https://t.me/Ibnugarad
Telegram: Contact @Ibnugarad

Telegram: Contact @Ibnugarad

يا مقلب القلوب ثبت قلبي على دينك
Send as a message
Share on my page
Share in the group