ነጃሺ ለነብዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) የላኩላቸው ደብዳቤ የት ነው የሚገኘው?
ነጃሺ ለነብዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) የላኩላቸው ደብዳቤ በቱርክ ይገኛል ተብሎ እንደሚገመት አንድ ትልቅ ሰው ካሁን በፊት አጫውቶኝ ነበር። ይህ እንደ አንድ ፍንጭ ይዤው ቆይቼአለሁ። ዛሬ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ፍንጭ አግኝቼአለሁ።
ይህ ተጨማሪ ፍንጭ ያገኘሁት ፕሮፌሰር ሑሴን አሕመድ (1996) "Aksum in Muslim historical traditions" ከተሰኘው ፅሑፍ ነው። በዚህ ፅሁፍም ነጃሺ ለነብዩ ሙሐመድ የላኩላቸው ደብዳቤ በቱርክ እንደሚገኝ የሚጠቁም ተጨማሪ ማስረጃ አግኝቼአለሁ።
ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ በመስከረም 13/1924 (እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር) እትሙ ላይ የግብፁ አሕራም ጋዜጣ ማርች 13/1931 ይዞት ወጥቶ የነበረው አጭር ማስታወሻ አስነበቦ ነበር። መረጃው በቤሩት የአሕራም ጋዜጣ ዘጋቢ የነበረ ሰው የቱርኩ ሱልጣን ዓብድል ሐሚድ ልጅ የሆነው ሳሊም አግኝቶት እንደነበረ እና የአክሱም ነጉስ ነጃሺ ለነብዩ ሙሐመድ የላኩላቸው ደብዳቤ በእጁ እንደሚገኝ ደብዳቤውም አባቱ በሰርጉ ጊዜ በስጦታ የሰጠው እንደሆነ እንደነገረው የሚያትት ነው።
ይኸው ፅሑፉ:-
The Amharic newspaper, Berhanenna Salam , in its issue of Meskerem 13.1924 E.C., carried a story, based on a report published in al Ahram of 13 March 1931, about the despatch from Beirut of a cable by a correspondent of the Egyptian daily in which he said that he met Salim, a son of the Turkish Sultan, Abd Al Hamid (1864-1909), who claimed that the letter of the Aksumite ruler to the Prophet was in his possessi, and that it had been given to him, by his father as a wedding present.
ሙሀመድ ሀጎስ
https://t.me/Ibnugarad