የመን ይፋዊ በሆነ መልኩ እስራኤል ጋር ጦርነት ያወጀች የመጀመሪያዋ ሀገር ሁናለች
የየመን ታጣቂ ሃይሎች ሚሳኤሎችን እና ዩኤቪዎችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፋቸውን ተናግረዋል።
...
“የእኛ የታጠቁ ሃይሎች በእስራኤል የተለያዩ ኢላማዎች ላይ እጅግ ከባድ የሚባሉ የባለስቲክ እና የክሩዝ ሚሳኤሎችን እንዲሁም በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን አስወነጭፈናል" ሲል ገልጿል። ከነዚህ ውስጥ ረጅም ርቀት የሚጓዙ ሚሳኤሎች የእስራኤል የኒውክለር ማብላያን ኢላማ ያደረጉ ጭምር ነበሩ ተብሏል።
...
የየመን ጦር ሃይሎች ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ያህያ ሳሪ የእስራኤል ጥቃት እስኪቆም ድረስ ሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም የተሻሉ ጥቃቶችን ማድረሳችንን እንቀጥላለን ብለዋል።
...