UMMA TOKEN INVESTOR

Ayub Nur Сhanged his profile picture
2 months
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

በባንኮች ውስጥ ገንዘባችሁን የምታስቀምጡ ወገኖች በጣም ጥንቃቄ አድርጉ። በተለይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ከነ ጭራሹ ሳያውቁ ከአካውንታቸው የሚፈፀመው ዘረፋ ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ ነው ያለው። ባንኮች ከአንድ ደንበኛቸው ሂሳብ የተወሰደ ገንዘብ እንዴት ወደየትኛው ሂሳብ እንደገባ እንደማያውቁ ወይም እንዴት የገባበትን እያወቁ ማስመለስ እንደማይችሉ በጣም ግራ የሚያጋባ ነው።

ለማንኛውም በየጊዜው ገንዘባችሁ መኖሩን አስረግጡ። በተለይ ሙስሊሞች በብዛት እየተዘረፉ ነው። ከዚያ አመልክቱ ይባላሉ። እስካሁን ድረስ የተወሰደበት እንጂ ተወስዶበት አመልክቶ የተመለሰለት መኖሩን አላውቅም። ብትችሉ እነሱ ዘንድ ከማስቀመጥ ንብረት ላይ ወይም ስራ ላይ አውሉት።

Ibnu Munewor

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ኑ የእህታችንን ዘይነብ አዳነ ህይወት እንታደግ!

እህታችን ዘይነብ አዳነ አሁን ላይ  ዱባይ ውስጥ  የሰው ቤት ሰራተኛ ነች።

የእህታችን የበሽታዋ መነሻ እብጠት ነበር።

አሁን ላይ ደግሞ   እብጠቱ ወደ ካንሰር ተቀይሯል። ሳይሰራጭ በፍጥነት በኦፕሬሽን መውጣት እንዳለበት ሀኪሞች ገልፀውላታል።

ህክምና ለማድረግ አቅም የለኝም እናንተ ሙስሊም ወንድም እና እህቶቸ ሆይ በሽታው ጊዜ ስለማይሰጥ  በምትችሉት ሁሉ  በአላህ ስም እርዱኝ  እያለች ነው።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000255648695 ኢብራሂም ሙሀመድ

ዱባይ

First Abu Dhabi bank

ሙሀመድ ሰዒድ

1111005814311001

IbanAb060351111005814311001

የሳውዲ ተቀባይ

00966531392447

ለተጨማሪ መረጃ

ስልክ ቁጥር

ዘይነብ አዳነ +971547767319

+971545077962

0547323703

ዘይነባ አዳነን ለመርዳት የተከፈተው

WhatsApp ግሩፕ👇 https://chat.whatsapp.com/C592tDAiTLy2qLS4TFe9rF

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የዓለም ህዝብ ግን አይገርምም⁉️

=======================

(ዓለም በዚህ ዘመን አይታው የማታውቀው የጦር ወንጀልና የዘር ጭፍጨፋ በጘዝ'ዛ)

||

✍ 365 km² ስፋት ባላት አነስተኛ ከተማ ውስጥ 2.3+ ሚሊዮን ዜጎች ተጠጋግተው ይኖሩባታል። በዚህች densely populated በሆነች ከተማ ላይ ለተከታታይ 3 ሳምንታት ያላባራ ከ12 ሺህ ቶን በላይ ቦምብ ሲዘንብ፤ በዚህም ሳቢያ፦

1) በትንሹ 7,028 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙስሊሞች ሲገደሉ፣

2) ከ70% በላይ የሚሆኑት ህፃናትና ሴቶች ሲሆኑ (2,913 ህፃናትና 1,709 ሴቶች)፣

3) 18,482 የሚሆኑት ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ሲዳረጉ፣

4) ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 481 የሚሆኑት ሲገደሉ (ከመካከላቸው 209 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው።)፣

5) ከ1,650 በላይ የሚሆኑት ጀናዛቸው እንኳ ሳይገኝ እስካሁን ድረስ በቦምብ በፈራረሱት ህንፃዎች ስር ሲሆኑ (ከመካከላቸው 940 ህፃናት አሉበት።)፣

6) 731 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙሉ ቤተሰቦች ሲገደሉ፣

⑦) 101 የጤና ባለሙያዎች ሲገደሉና 100 የሚሆኑት ሲቆስሉ፣

⑧) 12 ሆስፒታሎችና 32 የጤና ማዕከላት በነዳጅ እጥረትና በቦምብ ጥቃት ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ፣

9) በኢንኩቤተር ውስጥ የሚገኙ ከ130 በላይ የሚሆኑ ህፃናት ያሉበት ሆስፒታል ባጋጠመው በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ነፍሳቸው በእንጥልጥል ላይ ሲገኝ፣

⑩) ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ንጹሐን ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች፣ በት/ቤቶች፣ በሆስፒታል ግቢዎች፣ በመስጂዶችና ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ሳለ በዛው ባሉበት ጥቃቱ ሲያገኛቸው…(ከሰው ነፍስ አይበልጥምና ወደ አመድነት ስለተቀየሩት ውብ ህንፃዎችና መሠረተ ልማቶችማ አውርተን አንዘልቀውም።)

የሰለጠነ ተብዬው ዓለም አሁንም «ጦርነቱ ይቁም!» ከማለት ይልቅ «እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት አላት፣ ሐማስ መጥፋቱን ማረጋገጥ አለባት፣ ከጎንሽ ነን፣ ሐማስ ሽብርተኛ ነው፣ በሐማስ ጥቃት ለሞቱተረ እስራኤላዊያን አዝነናል!…» እያሉ ነው።

ትንሽ አሻሻልን የሚሉት ደግሞ ጦርነቱ መቆም የለበትም፤ ግን የተወሰነች እርዳታ ይግባላቸው ይላሉ።

እስካሁን በጋዛ መብራት የለ፣ ውሃ የለ፣ ምግብ የለ፣ ነዳጅ የለ…። በዚህ የተነሳ የቆሰሉትና መደበኛ ህመም የሚታመሙትም መታከም አልቻሉም።

ዙሪያውን በከበባ ስለሆነ ለጠናበት ታማሚ የውጭ ሕክምና እንዲያገኝ ማድረግ አልተቻለም።

እስራኤል ከላይ በአየር ከምታዘንበው የቦምብ ዝናብ ባሻገር ከምግብና ውሃ እንዲሁም ከሕክምና ከልክላ በጅምላ ጭፍጨፋ የጦር ወንጀልና የዘር ማፅዳት ወንጀል በመፈጸም ላይ ትገኛለች። ይህ ሁሉ የሚሆነው ዓለም እያዬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ተመድ ተብዬውም ሆነ የትኛውም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚል ተቋም ሁሉ የውሃ ሽታ ሆኗል። የነርሱ ህግ እነርሱን ለማዳን እንጂ ለሌላው አይሠራም። እነርሱ ዘንድ የሙስሊም፣ የዓረብና የአፍሪካዊ ሞት ከውሻቸው ሞት በታች ነው።

ግን ነፍስ ሁሉ እኩል ናትና የእጃቸውን አንድ ቀን ማግኘት አይችሉም። ነገ ላይ በሌላ የነርሱ አካል ላይ ጥቃት ሲፈጸም በሚዲያቸውም ሆነ ባልተጻፈው ህጋቸው ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ሲለፍፉ እናገኛቸዋለን።

አላህ ውርደታቸውን ያቅርበው፤ ለተበዳዮች ነስሩን ያፍጥነው።

አላህ የአሸናፊዎች ሁሉ አሸናፊ የሆነ ጥበበኛና ታጋሽ ጌታ ነው። አንድ ቀን አይርላቸውም።

#muradtadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Ayub Nur shared a
Translation is not possible.

ሙዓዊያ እና ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁማ በተጋጩ ግዜ ሁለት

ኢስላማዊ ስረወ መንግስት ተመሰረተ የሮሙ ንጉስ ይህን ሰምቶ

እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈ።

<<ከሮም ንጉሰ ነገስት ለ ሙስሊሞች መሪ ሙዐዊያ አቡ ሱፍያን!!

ባንተ እና በዐሊይ መካከል የተከሰተውን ግጭት

ሰምተናል።ስለዚህም ለሙስሊሞች መሪ አንተ መሆን

እንዳለብህም ስለምናምን አንተ ፍቃድህ ከሆነ የዐሊይን ጭንቅላት

ቀንጥሶ የሚያመጣልህን ወታደር ልላክልህ>>

ይህ ደብዳቤ ሙዐዊያ ጋር እንደደረሰም ሙዓዊያም

<<ከሙዓዊያ ለሮም መሪ!!! ሁለት ወንድማማቾች ስለተጣሉ

አንተ ምን አገባህ? አፍህን የማትዘጋ ከሆነ ጅማሬው እኔ ጋ የሆነ

እና ፍፃሜው አንተ ጋ የሆነ ሰራዊት ልኬ አንገትህን በማስቀንጠስ

ለዐሊይ በስጦታ መልኩ አበረክትለታለሁ>>

#ይህ_ትክክለኛ_ሙስሊሞች_ሳለን_ነው

_____

___

ካሊድ ኢብን ወሊድ ለፐርሺያው ንጉሰ ነገስት እንዲህ ሲል

ደብዳቤ ፃፈለት

<<ስለም ትድናለህ። እንቢ ያልክ እንደሆን ግን፤ እናንተ ህይወትን

የምትወዱትን ያህል ሞትን የሚወዱ ሰራዊቶችን ይዤልህ

እመጣለሁ።>>

ንጉሱ ይህን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ የቻይናውን ንጉስ የጦር እርዳታ

ሊለምነው ደብዳቤ ፃፈለት።

የቻይናውም ንጉስ እንዲህ ሲል ደብዳቤ መልሶ ላከለት።

<<ንጉስ ሆይ! ተራራን እንኳን ለመናድ ካሰቡ ምንም

ከማያግዳቸው ወታደሮች ጋር ለመጋፈጥ አቅሙ ስለሌለኝ

ጥያቄህን መፈፀም አልችልም።>>

# ምን_ያህል_ሀያላን_እንደነበርን_ተመልከቱ

_____

____

በደውለቱል ዑስማኒያ የአገዛዝ ዘመን የሙስሊም ወታደሮች የጦር

መርከቦቻቸውን ይዘው በአውሮፓ ደሴቶች ሲያልፉ በአከባቢው ያሉ

አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ሙስሊሞች መጥተው ፈትህ

እንዳያደርጉ በመፍራት ከበሮ ከመምታት እና ምንም አይነት ድምፅ

ከማሰማት ይቆጠቡ ነበር።

#ያኔ_ጀግና_ሳለን

_____

____

በደውለቱል ኡስማኒያ የአገዛዝ ዘመን በያንዳንዴ ቤት ደጅ ላይ

ሁለት የበር ማንኳኩያዎች ይኖራሉ። አንዱ ትልቅ ሲሆን አንዱ ትንሽ

ነው። በትልቀኛው ከተንኳኳ አንኳኪው ወንድ ነው'ና በሩን ሊከፍት

ሚመጣው ወንድ ይሆናል። ነገር ግን በትንሸኛዋ ከተንኳኳ

አንኳኪዋ ሴት መሆኗ ስለሚታወቅ ሴት ትከፍትላታለች።

በዚያ ምርጥ ዘመን አንድ ቤት ውስጥ ሰው ከታመመ ደጅ ላይ

ቀይ አበባ ይንጠለጠል ነበር። ያን አበባ የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ

እዝያ ቤት በሽተኛ መኖሩን ስለሚያውቁ በበሩ ሲያልፉ ድምፃቸውን

ዝቅ ያደርጉ ነበር።

#ሹፍ_ምን_እንመስል_እንደነበር !!!

_____

_

ግዜው ሰላሁዱን አል አዩቢ በይተል መቅዲስን ባስመለሰበት ግዜ

ነበር። እና ጦርነቱ ነገውን ሊጀመር ማታ ላይ የጦር መሪው

ሰላሁዲን የወታደሮቹን ድንኳን እየዞረ ሲያዳምጥ፤ ግማሹ ለይል

ይሰግዳል፣ ሌላው ቁርአን ይቀራል፣ የተቀሩት ደግሞ ይዘክራሉ።

ግን ድንገት በሆነ ድንኳን አጠገብ ሲያልፍ በድንኳኑ ውስጥ ያሉት

ሁሉም ተኝተው ነበር። ይህን ግዜ፦"በዚህች ድንኳን አዳሪዎች

ምክንያት ልንሸነፍ እንችላለን" ብሎ አለፈ።

#ማንተኛበት_ዘመን

_____

___

ቀደምት ዑለማኦች በሶስት ነገራት አደራ ይባባሉ ነበር።

1፦ሰውዬው በሱ እና በአላህ መካከል ያለውን ግንኙነት ካሳመረ፤

በሱ እና በሌሎች መካከል ያለው ግንኙነት ያምርለታል።

2፦ሰውዬው ሚስጥራዊ ተግባሩን ካሳመረ አላህ ይፋዊ ተግባሩን

ያሳምርለታል።

3፦ሰውዬው የአኪራው ጉዳይ ካስጨነቀው አላህ የዱንያውንም

የአኪራውንም ጉዳይ ያግራራለታል።

_____

_

#ትልቁ_ኪሳራ_ማለት_ይህ_ነው

ጀነት ስፋቷ የምድርን እና የሰማያትን ያህል ሁና ላንተ በሷ ቦታ

ሳይኖርህ ሲቀር...ትልቅ ኪሳራ ነው።

በእለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ ቁርአንን መቅራት ካልተካተተ ትልቅ

ኪሳራ ነው።

ይህን ፅሁፍ በማሰራጨት ጓደኛህን እንድታነቃው ይከጀላል!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group