1 year Translate
Translation is not possible.

መመለስ እንደምናስበው ቀላል አይደለም

የምናስበው ከባድ እንኳ ቢሆን . . .

ወይም መጀምሪያ የሆነ ያልተስተካከለ ወይም ደግሞ ልኩን ያለፈ ፍራቻ ነበረኝ ውስጤ ላይ . . .  እኔ አላውቅም ብቻ ግን ይሄ በተደጋጋሚ ወንጀል ላይ መሆኔን አውቄ  ልመለስ ስል ያለውን ስሜት ወሏሂ በምን ቋንቋ እንደምገልጸው አላውቅም በቃ ቃላት የለኝም . . . በ አንድ በኩል ከወንጀሌ   ለመመለስ ማደርገው እያንዳንዷን ጥረት እወደዋለሁ በቃ ሄደቱን ራሱ ዱአ ለማድረግ እጄን ማንሳቴ ፥መስገዴን   ። . . . በሌላ በኩል ልክ የሰራሁትን ወንጀል ማሰብና ማስተንተን ስጀመር በአለም ላይ ያሉ ሰዎች በሙሉ ንጹህ ሆነው እኔ ብቻ አሏህን እያመጽኩ  እንደሆነ ይሰማኛል በቃ የአሏህ ቁጣ በእኔ ወንጀል ምክንያት በሌሎች ላይ እንዳይወርድ እሰጋለሁ ፥

አሏህ በዚህች ምድር ላይ  ከፈጠራቸው ባሮች ከዚህ በፊትም ከነበሩ ህዝቦች እንደኔ የታገሰው ሰው በምድር ላይ ያለ አይመስለኝም ። በጥበቡ ብቻ ወንጀሌን ከዛሬ ነገ ትመለሳለች ብሎ ይመለከተኛል ።ምንም አያረገኝም ። በቃ ልክ ጌታየ ይቅር በለኝ ብየ እጄን ሳነሳ ሚታየኝ የኔ ወንጀል ክብደት ነው አሏህን በቀን በለሊት ያመጽኩት ነው ሚመጣብኝ ፡ምንም ሳያጎልብኝ ባበላኝ ባጠጣኝ እኔ እሱን ያለገደብ ድንበሩን መጣሴ ነው ትዝ ሚለኝ . . . አእምሮየ ላይ ሚመላለሰው እስካሁን በዚህ ወንጀሌ አሏህ እንዴት አላጠፋኝም ሚለው ነው ። የምር የአሏህ ቻይነት ግርም ይለኛል ።

. . . እጄን ሳነሳ እንባየም ብን ብሎ ይጠፋል ።አላውቅም የታባቱ እንደሚሄድ አእምሮየ ውስጥ ተደብቆ የኔን ደካማነትና የማልረባ መሆኔን እንደኔ በወንጀል የተጨማለቀ ሰው እንደሌለ ይነግረኛል ። ልቤም ይህንኑ ነው ሚለኝ ማይሆን ስሜት ይሰማኛል

ጌታየን ሚያስደስቱ ለይል እየሰገዱ ቀን ሚጾሙና በኢባዳ ሚያሳልፉ ምርጥ ሰዎች ስለመኖራቸው ዛሬም አልጠራጠርም ። ታዲያ እኒህ የአሏህ ባርያዎች ባሉበት ምድር እነዛ ነብያችንን የተከተሉ ሰሀቦችን ባሳለፈች መሬት . . . ዛሬ እኔ ተፈጥሬ ምድርን በኔ ወንጀል ብቻ አብቃቃታለው የኔ ወንጀል ለሁሉም፡ሰዎች ቢከፋፈል ሚያብቃቃቸው ይመስለኛል ።

ያቺ በነብዩ ዘመን ዚና ሰርታ ነብያችንን ተቀጥቅጬ ይግደሉኝ ስትል የነበረችና ልጇን ከወደለች ቡሃላ ተቀጥቅጣ ስትገደል ደሟ ኻሊድን ሲነካው ኻሊድም በወንጀሏ ሲያነውራት  ነብያችን እንዲህ ነበር ያሉት "ኻሊድ ሆይ የእሷ ተውበት እኮ ለሁሉም ቢከፋፈል ለሁሉም ያብቃቃዋል" (hadisun ketesasatku armign )

እንደተባለላት ሴት እኔ ደግሞ ዛሬ የእሷን ተቃራኒ ሆኜ

የ እሷ ተውበት ሁሉንም ሲያብቃቃ

የኔ ወንጀል ለሁሉም ይተርፋል ፤

ከወንጀል ያብቃቃቸዋል ።

ታዲያ ይሄን ያህል ልዩነት ኖሮን ጌታየ ይቅር ይለኝ ይሆን ?

የወንጀሌ ክፋት  ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ከቶኝ የመመለሻ በሩን እንዳላይ እንዳልደርስበት አርጎኛል ። እና ደግሞ ወደጌታየ መመለስን ሳስብ በፊት ላይ የነበርኩበትን ትንሽየ የኢማን ጥፍትና ያስታውሰኛል ግን መመለስ አለመቻሌ ደግሞ እንደ እግር እሳት ያቃጥለኛል . . . አንዳንዴ ሳስበው ያቺን ትንሿን ጥፍጥና ሁሌም እንደናፈኳት ምኖር ይመስለኛል  ወይም ደግሞ ምን አልባት ከዚህ የባሰ ሀል ውስጥ ገብቼ ጭራሽ ምንም እንዳላስታውስም እሆን ይሆናል ።

ልቤ ግን ሁሌም መመለስን ይፈልጋል የምር የሆነ የቀልብ ሰኪናን . . .  አሏህ ግን ለምንድነው የሰዎችን የኢማን ደረጃ ሚለያየው ? ሁሉንም ባሮቹን ለእሱ ተገዢ ማረግ ሲችል ለምን ግን ? ሚያምጹትንም ፈጠረ ?

ለምን እንደሆነ እኔም አይገባኝም

ምልሹን ለእናንተ ትቻለው

እኔኮ ሚገርመኝ ሶሀቦች የነበሩበት ዘመን እና የእኛ ዘመን ይሄን ያህል ልዩነት መፍጠሩ ነው ።

ግን ለኸይሩ ነው?

.

.

.

ወደ መጀምሪያየ ስመለስ

የዱአየ መጀመሪያ

እጄን ስዘረጋ እኒህ ያልኳችሁ ሁሉ ይመጡብኛል ።

የዱአየ መካከል

ዝብርቅርቅ ያለ የጥፋተኝነት ፥ የወንጀለኝነት . . . ስሜት ይሰማኛል ። ከዛ ደግሞ ትንሽ ወደኋላ ተመልሼ ከወንጀላቸው የተመለሱ እነዚያ ድንቅ ባሮችን አስታውሳለው . . . ከሁሉም ተመላሾች ግን ሚገርመኝ 100 ሰዎችን ገድሎ ከዛም ወደ አሏህ ተመልሶ ጌታው ተውበትን የተቀበለውን ባርያ

እኔ ምለው ግን ምን አይነት ተውበትን ቢያደርግ ነው ? ምን ያህል አሏህን ፈርቶ ቢጸጸት ነው ጀነትን ያገኘው ?

የዚህን ባርያ ተውበት ሳይ ትንሽ ልቤ ትረጋጋለች ጌታየ ምንም ወንጀል ብሰራ እስከተመለስኩ ድረስ ይቅር እንደሚለኝ ይሰማኛል ።እሱን ይቅር ያለ ጌታ እኔን ይለኛል ሚል ተስፋ ይኖረኛል ።

ተስፋየ ግን እንዳለ ሆኖ እንዴት ነው መመለስ ምችለው ነው ትልቁ ጥያቄ ? ? 

የዱአየ መዝጊያ

የሰውየውን ታሪክ አስታውስሼ ጌታየን ማረኝ ብየ በትንሽ ተስፋ ዱአየን እቋጫለው ። ከዛም ልቤ ትንሽ መረጋጋትን ታገኛለች

. . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

እና ግን ሚያናድድነውና ድጋሚ ራሴን ምወቅሰው እዛ ወንጀል ላይ ስመለስ እንደውም ከነበረኝ ብሶብኝ ራሴን አገኘዋለው ።

ይሄ ቆይ ምን ይባላል e

እያሾፍኩ ? 

ብሞትስ ?

ብሞትስ ብየም አስባለው ሚገርመው ሁሌም ወንጀል ስሰራ ብሞትስ ብየ ማስበው  ግን ምንም አይነት ስሜት አይሰማኝም ብሞትም ሞትኩ ነው ብየ አቀለዋለው እናም ይሄን ማሰቤ ወንጀልን ከመስርት አይገድበኝም ። ይልቁንም አሏህ ባለ ቀን ለመመለስ እጄን ስዘረጋ ያኔ ወንጀል ውስጥ እያለሁ ብሞት ኖሮስ ንየ አስብና ፍርሃት ሀዘን ይወረኛል እዛ ወንጀል ላይ ድጋሚ እንዳልገኝ ልቤ ይነግረኛል

በመጨረሻም

ይሄንኑ ሂደት እየደጋገምኩ እቀጥላለው. . .

ወይ አልመለስ ወይ ወንጀለኛ አልሆን  ወጣ ገባ እላለው

Send as a message
Share on my page
Share in the group