Translation is not possible.

የ12 አመቱ ትንሹ ሮናልዶ ፡ አባቱን አይፎን ግዛልኝ ብሎ ጠየቀው ።

የሮናልዶ መልስ ፡ አይ አሁን አይፎን አይገዛልህም የሚል ነበር ። አንተ አሁን የሚያስፈልግህ በትምህርትህ ላይ ማተኮር ፡ ከዛም የኳስ ችሎታህን ማዳበር እንጂ ፡ ስልክ ይዘህ ጊዜህን እንድታባክን አልፈልግም አለው ።

ትንሹ ሮናልዶ ፡ መጠየቁን አላቋረጠም ስልክ የምፈልገው ከአንተ ጋር ለመደዋወል ነው ።

ሮናልዶ ይህን ሲሰማ ok ከኔ ጋር ለመደዋወል ከሆነማ ፡ በርግጥም ስልክ ያስፈልግሀል ብሎ ፡ እናቱ ይይዙት የነበረውንና ፡ ከአመታት በፊት የተቀመጠውን ፡ ስማርት ያልሆነ ትንሽ ስልክ አውጥቶ ፡ ይህን ያዝና ሲምካርድ አስገብተን ትጠቀምበታለህ ብሎ ሰጠው ።

....

ለወላጆች ፡

ለታዳጊዎች ስልክ የምትሰጡ ወላጆች መቸስ በሀብት ብዛት ከሮናልዶ አትበልጡም ። ይህ ሰው ቢፈልግ ለልጁ አደለም አይፎን ሌላም መግዛት ይችላል ። ግን በቃ እንደማይጠቅመው ስላወቀ ሊገዛለት አልፈለገም ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group