UMMA TOKEN INVESTOR

misbah Abdu shared a
Translation is not possible.

👉ክፍል አራት

↝የትንሹ ዚና አደገኝነት

በዑለሞች አተያይ የእጅ ዚና ሲባል የዘመኑ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ባዳ(አጅ ነቢ)ሴቶችና ወንዶች የሚጻጻፉትና የሚላላኩት የተለያዩ ሕገወጥ መልዕክቶችም በዚህ ውስጥ ይጠቃለላሉ፡፡! በተለያዩ መንገዶች ቴክስት ሜሴጆችን የሚጽፉ ጣቶችም ከእጅ ይቆጠራሉ፡፡ የሞባይል ስክሪኖችን የሚነካኩና ቻት ሴክስን፣ ፎን ሴክስንና የወሲብ ፊልምን ሳይቀር ጠቅ ጠቅ የሚያደርጉ ጣቶችም በዚሁ ውስጥ ይካተታሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ይህ እውነታ ወደ ዓይን ዚና፣ ወደ ምላስ ዚና፣ ወደ ጆሮ ዚናና ወደሌሎችም ሁሉ በየፊናቸው በሚኖራቸው ተሳትፎ ልክ ይለጠጣታል፡፡❗️

     👉 ⑤/ የእግር ዚና አደገኛነት

አንድ የአላህ(ﷻ)ባሪያ መልካም ነገርን ለመሥራት ሲሄድ በተራመደ ቁጥር አጅር ያገኛል፡፡ የእግሮቹ ዱካ ያረፉበት ቦታ ሁሉ ይጻፍለታል፡፡ ይህንኑም ቀጥሎ ካለው ቁርኣናዊ አንቀጽ መረዳት ይቻላል፡፡

Surah Ya-Sin (يس), verses: 12

إِنَّا نَحْنُ نُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ وَنَكْتُبُ مَا قَدَّمُوا۟ وَءَاثَٰرَهُمْ وَكُلَّ شَىْءٍ أَحْصَيْنَٰهُ فِىٓ إِمَامٍ مُّبِينٍ

እኛ ሙታንን እኛ በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን፡፡ ያስቀደሙትንም ሥራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን፡፡ ነገሩንም ሁሉ ገላጭ መሪ በኾነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው፡፡

በዚህ አንቀጽ ውስጥ «ወኣሣረሁም»(ፈለጎቻቸውንም) የሚለውን ቃል አንዳንድ ዑለሞች ሲተረጉሙት የእግሮቻቸውን ፋና(ዱካ)ማለት ነው ይላሉ፡፡

በዚሁ መሠረት አንድ ሰው ወደ ኸይርም ሆነ ወደ ሸር ሲራመድ እርምጃው ሁሉ ይመዘገባል፡፡ ግለሰቡ ወደ ሸር ሲራመድም የእግር ወለምታ አጋጥሞታል ይባላል፡፡ የእግር ወለምታ ደግሞ ልክ እንደ ምላስ ወለምታ ሁሉ ከባድ ነው፡፡ አላህ(ﷻ)በሱረቱል ፉርቃን ውስጥ ስለ ዲባዱር-ረሕማን ባህሪያት በተናገረባቸው አንቀጾች ውስጥ እነርሱ በንግግራቸውም ሆነ በእርምጃቸው ትክክለኞችና ቀጥተኞች እንደሆኑ ግልጿል፡፡ አላህ(ﷻ)እንዲህ ይላል፡-

Surah Al-Furqan verses: 63

وَعِبَادُ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى ٱلْأَرْضِ هَوْنًا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ ٱلْجَٰهِلُونَ قَالُوا۟ سَلَٰمًا

የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም(በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው፡፡

      (አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)

  ኢንሻ አላህ 👉 የልብ ዚና አደገኛነት ይቀጥላል

ከእነዚህን የሸይጧን ወጥመዶች ራሳችንን ቁጥብ ካደረግን ከብዙ መጥፎ መዘዞች እንርቃለን ነገር ግን እንደ ቀልድ ምንዳፈራቸው ከሆነ መጨረሻው መጥፎ ነው ሚሆነው።

ሁላችንም በምንችለው በውስጥ መስመር ለጓደኞቻችን ሼር እናድርግላቸው።

      👉 ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር

https://t.me/menhaj_Asselefiy101A

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group