Ali Mengesha Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Ali Mengesha shared a

★ እህቴ አትሸወጅ★

አንቺን ለማማለል ቢለፋ ቢደክመ,

ፊትና ውስጥ ሊከትሽ ቢሯሯጥ ቢያሴርም,

ከዲንሽ ሊያርቅሽ ቢያምጥ ቢሟቅቅም,

ጥንቁቅ ሁነሽ ተገኝ ጭራሽ አይቀርብሽም,

★★★★★★★★★★★★★★★★

አንቺ ከጠነከርሽ ካልሆንሽ ለፈስፋሳ,

በአቋምሽ ቀጥ ካልሽ ካልሆንሽ ቀለስላሳ,

ላናገረሽ ሁላ ካልሆንሽ መለስላሳ,

እህቴ አትመችም ለስራ አጥ ጎረምሳ,

----------------------------------------------------------

ወደድኩሽ እያለ ቢሽሞነሞንብሽ,

ልሞት ነው በፍቅርሽ እያለ ቢያወራሽ,

ሸሪአን ሳይጠብቅ ከሆነ እንዲ ያለሽ,

ተይው እርር ይበል እውነት ከሞተልሽ,

★ ጠብቂ እህቴ★

Hi ሲልሽ Hi ሳቲይ በሩን ከሸነጎርሽ,

ከዲንሽ በስተቀር ሌላውን ከረሳሽ,

ለስሜትሽ ሳይሆን ለሀቅ ከፀናሽ,

ከመጥፎ ጓደኛ ርቀሽ ካገለልሽ,

ከማይረባ ቦታ ርቀሽ ከተገኘሽ,

ልብስሽን በወጉ ሰትረሽ ከለበሽ,

በሙሉ ሁኔታሽ ሀያእ ካልተለየሽ,

ይህ የወንድ አልጫ አይደርስም ከደጅሽ,

★★★★★★★★★★★★★★

የተዘጋጀ አለ ላንቺ የተቀመጠ,

አላህ ያኖረልሽ በሱና የሰመጠ,

በዲኑ ጠንካራ በሀቅ የነጠጠ,

ላንቺ እውነተኛ ፍቅር ልቡን ያቀለጠ,

ለሚተነኩልሽ አይኑ የፈጠጠ,

አለሽ ውድ ስጦታ ከአላህ የተሰጠ,

★★★★★★★★★★★★

እናም እህቴዋ‼️

★★★★★★★★★★★

ስሜትን ተይና ታነጪ በሱና,

ቀጥ ብለሽ ተጓዢ በነብዩ ሱና,

አላህ ያዘዘሽን መርሀባ በይና,

ክልክላቱን ራቂ ነፍስያን ተይና,

ይሄ ለአኼራሽ ዋጋ አለውና,

★★★★★★★★★★

Send as a message
Share on my page
Share in the group