عزالدين ابافيطا Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

*የዓሹራ_ፆም ያለው ትሩፋት*

*فضل صوم يوم عاشوراء*

ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ አንሁ) በዘገቡት ሀዲስ ነቢዩ (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና በመጡ ግዜ የሁዶች ዓሹራን ሲፆሙ አይተዋቸው ለምን እንደሚፆሙት ሲጠይቋቸው \"ይህ ቀን መልካም ቀን ነው፣ አላህ በኒ ኢስራኢልን ከጠላታቸው ነፃ ያወጣበት ቀን ነው፣ በዚሁ ምክንያት ሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) ፆሙት\" በማለት መለሱላቸው። ነቢዩም (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) \"እኔ ለሙሳ ከናንተ ይበልጥ የተገባው ነኝ\" በማለት ፆሙት ሌሎችም እንዲፆሙት አዘዙ። (ቡኻሪ) በሌላ

በሙስሊም ዘገባ \"ይህ ታላቅ ቀን ነው። ሙሳንና ህዝቦቹን ነፃ ያወጣበትና ፈርኦንንና ህዝቦቹን ያሰመጠበት\" በማለት ተዘግቧል።

عن ابن عباس رضي الله عنهما قال: قَدِمَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآله وَسَلَّمَ المَدِينَةَ فَرَأَى اليَهُودَ تَصُومُ يَوْمَ عَاشُورَاءَ، فَقَالَ: «مَا هَذَا؟» قَالُوا: هَذَا يَوْمٌ صَالِحٌ، هَذَا يَوْمٌ نَجَّى اللهُ بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنْ عَدُوِّهِمْ، فَصَامَهُ مُوسَى، قَالَ: «فَأَنَا أَحَقُّ بِمُوسَى مِنْكُمْ»، فَصَامَهُ، وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ. أخرجه البخاري في صحيحه.

وفي رواية مسلم- ((هذا يوم عظيم أنجى الله فيه موسى وقومه وغرّق فرعون وقومه))

فعَنْ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ : مَا رَأَيْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَتَحَرَّى صِيَامَ يَوْمٍ فَضَّلَهُ عَلَى غَيْرِهِ إِلا هَذَا الْيَوْمَ يَوْمَ عَاشُورَاءَ وَهَذَا الشَّهْرَ يَعْنِي شَهْرَ رَمَضَانَ . \" رواه البخاري

ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ አንሁ) \"ነቢዩ (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከዓሹራእ እና ከረመዳን ሌላ አንድንም ፆም ከሌላው አስበልጠው ትኩረት የሰጡበት አላየሁም\" ብሏል። (ቡኻሪ)

فعن عَبْدِ اللهِ بْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُمَا قال: حِينَ صَامَ رَسُولُ اللهِ صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ وآله وَسَلَّمَ يَوْمَ عَاشُورَاءَ وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، إِنَّهُ يَوْمٌ تُعَظِّمُهُ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآلِهِ وَسَلَّمَ: «فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ إِنْ شَاءَ اللهُ صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ» قَالَ: فَلَمْ يَأْتِ الْعَامُ الْمُقْبِلُ حَتَّى تُوُفِّيَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآلِهِ وَسَلَّمَ. أخرجه مسلم في \"صحيحه\"

አብደላህ ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ አንሁ) የአላህ መልእክተኛ ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም የአሹራን ቀን ፁመው ሰሀባዎቻቸውንም እንዲፃሙ ባዘዙ ጊዜ፦ ይህ ቀን እኮ አይሁዶችና ነሳራዎች የሚያልቁት ቀን ነው አሉዋቸው። እሳቸውም፦ \"የአላህ ፍቃድ ሆኖ ቀጣይ አመት ከደረስን ዘጠነኛውንም ቀን እንፃማለን\" አሉ። ነገር ግን የቀጣዩ አመት አሹራ ሳይደርሱ ሞቱ።\" (ሙስሊም)

ዘጠነኛውን ቀን መጨመር የተፈለገበት ምክንያት ከአይሁዶችና ከነሳራዎች ለመለየት ነው።

وقال رسول الله صلى الله عليه وسلم : \" صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ \" رواه مسلم

የአላህ መልክተኛ ( ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) \"የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን አመትና የቀጣዩን አመት ወንጀል እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ። የዓሹራ ፆም ደግሞ ያለፈውን አመት ወንጀል እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ\" ብለዋል። (ሙስሊም)

በነዚህ ፆሞች የሚታበሱት ወንጀሎች ትናንሽ (ሰጋኢር) ወንጀሎች ናቸው። ትላልቅ ወንጀሎች የተለየ ተውባ ይፈልጋሉ።

በዘንድሮ አመት 1446 አመተ ሂጅራ ዘጠነኛው ቀን ሰኞ ሲሆን አስረኛው ማክሰኞ ስለሆነ ሁላችንም እንዳያመልጠን በጉጉት እንጠባበቅ ።

★ በእነዚህ ቀናት ጾም ከመጾም ውጭ ከወትሮው ለየት ያለ የሚደረግ ኢባዳም ሆነ የሚኬድበት ቦታ የለም ።

አላህ ደርሰው ከሚፆሙት ያድርገን ይወ ፍቀን

✍️ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅ

Send as a message
Share on my page
Share in the group