Aminu temam Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Aminu temam shared a
Translation is not possible.

ከዛሬው ጉባኤ የወጣ የጋራ ስምምነት መግለጫ!

🔴 በጋዛ ሰርጥ ላይ ያለውን የእብደት ጦርነት ለማስቆም ታሪካዊ፣ ልዩ እና ቆራጥ ውሳኔ ወስዷል።

🔴 በጋዛ ሰርጥ ላይ ለ17 አመታት የቆየውን ከበባ ለማንሳት ውሳኔ ሰጥቷል።

🔴 የራፋህ ድንበርን በቋሚነት በመክፈት፣ ለነዳጅ፣ ለእርዳታ እና ለህክምና ቁሳቁሶች ምቹ መተላለፊያ እንዲሆን ተወስኗል።

🔴 የጋዛ ሰርጥ መልሶ ግንባታን የሚያግዝ ፈንድ የጋራ ጥምረት በአስቸኳይ በማቋቋም ከ41 ሺህ በላይ ሙሉ በሙሉ የወደመ መኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም ከ222 ሺህ በላይ በከፊል የወደሙ መኖሪያ ቤቶችን የመንግስት መስሪያ ቤቶችን፣ መስጊዶችን፣ ቤተክርስትያኖችን፣ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመገንባት የወሰነ ሲሆን ይህን የፈፀሙ የጦር ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ እና ለአለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች እና ለሚመለከታቸው ፍርድ ቤቶች ለማቅረብ የአረብ እስላማዊ የህግ አካል ለማቋቋም ተወስኗል።

🔴 የወራሪዋ አምባሳደሮች ከአረብ እና ሁሉም እስላማዊ ሀገራት ማባረር ፣የሀገራቸውን አምባሳደሮች በመጥራት እየተፈጸመ ላለው ወንጀል እና እልቂት ምላሽ እና ይህንን ወራሪ ሙሉ በሙሉ ቦይኮት ለማድረግ ተወስኗል።

🔴 ወራሪውን ከፍልስጤም ግዛት ማባረር፣ ወረራውን ማስቆም እና እየሩሳሌም ዋና ከተማዋ በማድረግ የፍልስጤም ሀገርን ለመመስረት ስምምነት ላር ተደርሷል።

የሙሐመድ ትውልድ From Ultra palestine

#palestine

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Aminu temam shared a
Translation is not possible.

ይቺህ የማዲባ ሀገር ለካ እንዲህ ጉደኛ የመርህ ሀገር ኖራለች። መቼስ ይህ የእስራኤል-ፍልስጤም ጦርነት የብዙ ሀገራትን ገመና እና የአቋም ዥዋዥዌ አሳይቶናል። በተቃራኒው ደቡብ አፍሪካ የማይነቃነቅ፣ የማይወዥቅ ፅኑ የመርህ ሀገር መሆኗን ደግማ ደጋግማ አስመስክራለች። እንደ ዉድ ልጇ ማዲባ ጥቁር እና ነጩን የያሲር አረፋትን እስካርፍ ለብሳ ለፍትህ ታምና ገዳይ አምባገነኖችን አውግዛለች። የደቡብ አፍሪካን ያህል ለፍልስጤማውያን እስራኤልን በግልፅ የወቀሰ የአረብ ሀገር እንኳ የለም።

ከሰሞኑ ደግሞ ህፃናትን ከሚጨፈጭፍ ስርዓት ጋር ቴል አቪቭ መቀመጥ የለባቸውም ብሎ ድፕሎማቶቿን በሙሉ ጠርታለች። ትላንት ደግሞ የሀገሪቱ ፓርላማ በእስራኤል-ሐማስ ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባው ላይ የደቡብ አፍሪካ ዉጭ ጉዳይ እና ዓለማቀፍ ትብብር ሚንስትር ዶር ናሌዲ ፓንዶር እጅግ የሚያስደምም ንግግር ተናግሯል። ቆራጥነቷ እና ልበሙሉነቷ ይገባል። በመሐል አንድ ነጭ ተነስቶ እርሰዎ ሴትዮ ባለፈው ቴህራን ሄዱ፣ ቀጥሎ ለሐማሱ መሪ ደውሎ አነጋገሩ...አዝማሚያዎት አላማረኝም..አሸባሪዎችን እየደገፉ ይሁን እንዴ አላቸው። ይህን ግዜ እሳት ጎርሶ እሳት ለበሱ። ከእንባቸው ጋር እየታገሉ ጠረጴዛ እየደበደቡ መናገር ጀመሩ...

እኛ የአፓርታይድ ጠባሳ ያረፈብን ሰዎች ነን። ጠባሳው ጉልህ ነው። ያን የኛን መከራ ፍልስጤማዊያን አሁን እየኖሩት። አንድ የቤተሰቤን ታሪክ ልናገር..አያቴ ብርቱ ሰው ነው። ታታሪ ሰራተኛ ነው። ትልቁ ሕልሙ በደርባን ከተማ መኖሪያ ቤት መስራት ነበር። በልፋቱም ይህን ሕልሙን አሳክቶ ከባለቤቱ ጋር ደርባን ውስጥ ወደ ገዛው ቤቱ ገባ። ምን ዋጋ አለው..ይህ አከባቢ ለነጭ እንጂ ለጥቁር አይፈቀድም ተባለ። ያለ ካሳ ላቡን አፍስሶ የገዛውን ቤት ተነጠቀ። ወዲያውኑ በልብ ድካም አረፈ.....

ይህን ታሪክ ብቻ ተናግሮ አልቋጩም። የእስራኤልን ጅምላ ፍጅት በፅኑ አወገዙ። የፍልስጤም ልጆች የኔን ሀይማኖት አይከተሉም ይሆናል..የኔን ቋንቋ አይናገሩም ይሆናል..የቆዳ ቀለማችንም አይመሳሰልም ይሆናል..ግን የሰው ልጆች ናቸው። እኛ በአፓርታይድ ያየነውን መከራ የትኛውም የሰው ልጅ እንዲያይ መፍቀድ የለብንም። ቃል ኪዳን የገባንለት ሕገ መንግስታችንም ለአለማቀፍ ወንድማማችነት፣ ነፃነት እና ለሰብዓዊ ክብር እንድንቆም ያስገድደናል ...አሉ አሁንም ቀጠሉ...እኔን የበለጠ የገረመኝን ነገር ተናገሩ..

እስራኤል አለማቀፍ ህጎችን ጥሳለች። በመሆኑም ጠ/ሚ/ር ቤንጃሚን ኔታናሁን ጨምሮ የእስራኤል ቁልፍ አመራሮች በአለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) መጠየቅ አለባቸው አሉ። እንዳውም አሁኑኑ የእስር ማዘዣ ልወጣባቸው ይገባል ብሎ በመናገር ይበልጥ አስደመሙኝ። እምዬ ፓንዶር ለእንደርሰዎ አይነት ብርቱ፣ቆራጥ፣ልባም፣ የመርህ ሰው ከፍ ያለ አድናቆት አለኝ🙏

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group