abu meryam murad Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Followers
0
There are no followers
Translation is not possible.

መህዲ ማነው?

‹‹መህዲ›› በመጨረሻው ዘመን ከደጃልና ዒሳ መምጣት አስቀድሞ የሚነሳ ታላቅ ‹‹ኸሊፋ›› ነው። ‹‹መህዲ›› የማዕረግ ስሙ ሲሆን ‹‹ሁዳ›› ከሚለው ቃል የተገኘና

‹‹የተመራ ቅን ኸሊፋ›› ማለት ነው። መጠሪያ ሙሉ ስሙ ደግሞ ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ አል-መህዲ›› ነው።

ስለ መህዲ በቁርኣን የተነገረ ምንም ነገር አናገኝም። መረጃዎቹ በሙሉ ከሐዲስ የተገኙ ሲሆን ከሃያ በላይ የተረጋገጡ ዘገባዎች ይገኛሉ። ብዙ የሱንና ዑለማዎች ስለ መህዲ የፃፉ ሲሆን ቲርሚዚና አቡ-ዳውድ ራሱን የቻለ ምዕራፍ ሰጥተውታል።

ከሁሉም ታዋቂው ሐዲስ አቡ-ዳውድ የዘገቡት ሲሆን ነቢዩ

(ዐሰወ) እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ትንሳኤ ሊቆም አንድ ቀን ቢቀረው እንኳን አላህ ከቤተሰቤ የሆነን፤ ስሙ ከእኔና ከአባቴ ጋር የሚመሳሰል መሪን ሳያስነሳና በበደል የተዋጠችውን ምድር በፍትህ ሳይሞላት አይተዋትም።››

(አቡ-ዳውድ 4282)

ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው መህዲ የነቢዩ (ዐሰወ) ቤተሰብ ነው። ስሙም የነቢዩን (ዐሰወ) እና አባታቸውን የያዘ ሲሆን ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ›› ወይም ‹‹አህመድ ኢብን አብዱላህ›› ነው። የሚመጣውም ዓለም በዙልም በተዋጠችበት በመጨረሻው ዘመን ሲሆን የአላህን ቃል ከፍ በማድረግ ፍትህን ያነግሳል።

ኡሙ ሰላማ (ረዐ) እንደተናገረችው ነቢዩ (ዐሰወ) ‹‹መህዲ በፋጡማ በኩል የሚገኝ ቤተሰቤ ነው።›› ብለዋል። ኢብኑል ቀይም ይሄንን ሐዲስ ሲያብራሩ ‹‹መህዲ የሐሰን ዘር ሲሆን

አል-ሐሰን ለሙስሊሙ አንድነት ሲሉ ኸሊፋነታቸውን አሳልፈው በመስጠታቸው ምክንያት አላህም በመጨረሻው ዘመን ከቤተሰባቸው ታላቅ ኸሊፋ በማስነሳት ክሷቸዋል።››ሲሉ ፅፈዋል።

(አቡ-ዳወድ 11/373)

አቡ-ሰዓድ አልኩድሪ በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ (ዐሰወ) ስለ መህዲ ገፅታ ሲናገሩ ‹‹ቁመቱ ረጂም፣ ትከሻው ሰፊ፣ አፍንጫው አጠፍ ያለ ነው።›› ብለዋል።

(አቡ-ዳውድ 4265)

መህዲ የሚነሳበትን ቦታ በተመለከተ የተለያዩ ዘገባዎች አሉ። ከፊሎቹ ከሻም ከፊሉ ከኹራሳን ሌላው ደግሞ ከመዲና እንደሆነ ይናገራሉ። ኢብን ከሲር የሁሉንም ሐዲሶች

ጥቅል ሀሳብ ሲያስቀምጡ ‹‹የሚነሳው ከምስራቅ ነው። ከዚያም ወደ መካ ይሄዳል። ሰዎችም በከዓባ ዙሪያ ቃልኪዳን ይገቡለታል።›› ብለዋል። እንዲሁም በሌላ መጽሐፋቸው ‹‹በሐዲስ በተጠቀሰው መሰረት ባንዲራው ጥቁር ነው።›› በማለት አብራርተዋል።

(አልቢዳያህ ወልኒያህ 19/63፤ አልፊታን ወልመላሂም

1/49)

ኢማም አህመድ እንደዘገቡት መህዲ መሪነት ሲመረጥ ፍላጎቱም ክህሎቱም አልነበረውም። እናም ‹‹አላህ በአንድ ሌሊት ይመራዋል።›› ብለዋል (ዐሰወ)። ኢብን ከሲር ሐዲሱን ሲያብራሩ፡- ‹‹ይህ ማለት አላህ ይረዳዋል፣ ከዚህ በፊት ያልነበረውን ችሎታም ይሰጠዋል ማለት ነው።›› ብለዋል።

(አህመድ 2/58/ አልፊታን ወልመላሂም 1/29)

መህዲ ኸሊፋነትን ከተረከበ በኋላ ሙስሊም አገራትን በአንድ በማፅናት በቀደመው ኢስላማዊ አስተዳደር ስር ያስገባቸዋል። ከዚያም በቡኻሪ እና ሙስሊም (2897)

እንደተዘገበው ከሮማውያን ጋር የመጨረሻው ታላቁ ጦርነት

‹‹አል-መልሃማ አል-ኩብራ›› ይካሄዳል። ሙስሊሞችም ዳቢቅ ላይ ድል ደርጋሉ። ከዚህ በፊት ያልተከፈቱ አገራትንም

ይከፍታሉ። ከዚያ በኋላ ሙስሊሞች በየትኛውም ኃይል አይሸነፉም። አላህ አማኞችን ከፍተኛ የሀብት መትረፍረፍ ይባርካቸዋል።

ሸይህ ዑመር ሱለይማን አል-አሽቀር ሐዲሱን መሰረት በማድረግ እንደተናገሩት ‹‹ይህ ጦርነት ከባድ ውድመትን ስለሚያስከትል ዓለም አሁን ካለችው ስልጣኔ ወደኋላ በመመለስ እንደ ጥንቱ በጦር በጋሻ በፈረስ መጠቀም ይጀምራሉ።›› ብለዋል።

(አል-ቂያማህ አስ-

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እነዚህ በቱርክ በኢራን በፓኪስታን እጅ የሚገኙ የዘመኑ የጦር መሳሪያዎች ናቸው ግን ለራሳቸው ጥቅም እንጂ ለፍልስጤም ምንም አይፈይዱም::

ዱኒያ ከምናስበው በላይ ተወሳስባለች የሚወድህም ሊረዳህ አይችልም የራሱ ጠላት ከጎኑ ተቀምጦለታል ለፓኪስታን ህንድ ለኢራን አሜሪካ ለቱርክ ግሪክ በቃ ራስ ወዳድነት እንጂ የሙስሊም ልቦናን አጥተናል::

image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

"ዓቂቃ"

አቂቃ ማለት አዲስ ለተወለደ ህፃን ልጅ የሚታረድ መስዋእት

የሚደረግ እርድ ነው። የተወደደ እና የተፀና የተከበደ ነቢያዊ ፈለግ

እርድ ነው።

“ዐቂቃ ማረድ በጣም የጠበቀ እና የተወደደ ሱና (ሱና ሙአከዳ)

ነው።

ምክንያቱም ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል

"ማንኛውም ልጅ በ7ኛው ቀን በሚታረድለት ዐቂቃ የተያዘ ነው ።

ይህም ማለት ዐቂቃ የሚታረድለት ሕፃን ለወላጆቹ በቂያማ ቀን

ሸፈዐ ይሆናል ።ስሙ የሚወጣለትም ራሱንም (ፀጉሩን)

የሚላጨው በዛን ዕለት ነው።" ሲሉ መናገራቸውን ነው

(አቡዳውድ እና ነሳኢ) ዘግበውታል።

የዐቂቃ ዓላማው (የተደነገገበት) ምክንያት ለአላህ ሱብሃነሁ

ወተዓላ ምስጋና ለማድረስ ነው። ይህም አንድ ሰው ልጅ

ስለተወለደለት በመደሰት በ 7ኛው ቀን ደስታውን ለመግለፅ እና

ይህንንም ደስታውን ሰዎች እንዲያውቁት ለማድረግ እና

የተወለደውም ልጅ የማን እንደሆነ ለማሣወቅ ነውና አላህ ደግሞ

ልጁን እንደሚጠብቀው፣ሷሊህ ልጅ እንዲሆንለት ምክንያትም

እንዲሆነው የሚደረግ አርዶ ሰውን የማብላት ስርኣት # አቂቃ

ይባላል።

በአብዛኞቹ ሙስሊም ምሁራን እንዳሉት ዐቂቃ መደረግ ያለበት

ትልቅ ሱና (ሱና ሙአከዳ) ነው። እንደ አንዳንድ ምሁራን ደግሞ

ዐቂቃ ማድረግ ዋጅብ (ግዴታ) ነው የሚሉ ዑለማዎችም አሉ።

በላጩና የተመረጠው የዐቂቃ ማውጫ ጊዜም ልጅ በተወለደ

በሰባተኛው (7ኛው) ቀን ነው የሚሆነው።

☞ ወላጆች (እናትና አባት) አሊያም አያቶች ማለትም የወላጅ

አባት እና እናት ለልጃቸው አሊያም ለልጅ ልጃቸው ዐቂቃ

ማውጣት አለባቸው፣ይችላሉም።

የተወለደው ልጅ ወንድ ከሆነ ሁለት በግ(ፍየል) ሴት ከሆነች

ደግሞ 1 በግ(ፍየል) ሊታረድ ይወደዳል ።

ምክንያቱም ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የአሊይ(ረዐ)

ልጅ ሐሰን በተወለደበት ጊዜ ሁለት በግ አርደዋል ።

(ቲርሚዚ ዘግበውታል)

እንዲሁም ስሙን ደህና ኢስላማዊ ስም በመምረጥ ሊጠራው

ይገባል።

ለምሳሌ ወንድ ከሆነ አብዱረህማን, አብዱላህ፣ሙሀመድ ወዘተ

....... ሴት ከሆነችም ደግሞ አሲያ፣ መሪየም፣ ኸዲጃ፣ ፈጢማ

ወዘተ......ብሎ ስም ቢያወጣላቸው ይወደዳል።

ሰባተኛው ቀን ያልታረደ እንደሆነ በ14ኛው ቀን ሊታረድ ይችላል

ያም ካልሆነ በ 21ኛው ቀን ቢያወጣ ችግር የለውም ይላሉ

ኡለማዎች፣

በአጠቃላይ አንድ ልጅ እስኪጎረምስ ድረስ አቂቃ ማውጣት

ይችላል የሚሉ ኡለማዎችም አሉ፣ እናም ቀኑ አልፎዋል ብለን

ይህን የጠበቀና የተወደደ የረሱል(ሰአወ) ሱና ከመተግበር

አንዘናጋ።

ምን አልባት ህፃኑ ሰባት ቀን ሳይሞላው የሞተ እንደሆነ ዐቂቃ

ማረዱ አስፈላጊ አይሆንም ብለዋል ኡለማዎች።

አንድ ሰው በህፃንነቱ ወላጆቹ አቂቃ ካላወጡለትና ትልቅ ሰው

ከሆነ በሁዋላ ና አቅሙ ካለው ጓደኞቹን ሰብስቦ አላማውን

ነግሯቸው(ዐቂቃ እንደሆነ ነግሯቸው) አቂቃ ማውጣት ይችላል

ብለዋል።( ኢብን ባዝ ረሂመሁላህ)

ስለዚህ እድሜያችን የፈለገ ያህል ቢሆንም አቂቃን ነይተን

ማውጣት እንችላለንና አንዘናጋ

የታረደው እንሠሣ ሥጋው በዒድ አል-አድሃ በዓል እንደሚደረገው

ሁሉ ሦስት ቦታ መከፈል አለበት። አንድ ሦስተኛው- ለድሃ፣ አንድ

ሦስተኛው- ለጓደኞች እና አንድ ሦስተኛው ደግሞ ለቤተሰብ

ይሠጣል።

አንድ ሰው የታረደውን ሥጋ ሁሉንም ለድሆችና ችግረኛ ሰዎች

መስጠት ይችላል።

ልጆች የአላህ ስጦታ ናቸው። እናም ይህን ታላቅ ፀጋ የሠጠንን

አላህን ማመስገን ይኖርብናል። ልጆችንም ገና ከህፃንነታቸው

ጀምሮ ልንንከባከባቸውና በኢስላማዊ አስተዳደግ እና ትምህርት

ያድጉ ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ልናደርግላቸው ይገባል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አስቸኳይ | በጋዛ የሚገኘው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፡ ወረራ ባለፉት ሰዓታት 56 ጭፍጨፋ ፈጽሟል፣ የ302 ሰዋች ህይወት የቀጠፈ ሲሆን አብዛኞቹ ሰዋች ደግሞ ተፈናቅለዋል።

አስቸኳይ | በጋዛ የሚገኘው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፡ ወረራው ሆን ተብሎ ቤተሰቦች ለሰይ ያነጣጠረ ሲሆን የጠፉት ቤተ ሰቦቭ ብዛት ቁጥር 881 ደርሷል።

አስቸኳይ | የጋዛ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፡ በጋዛ የተገደሉት ሸሂዶች ቁጥር 8,005 ደርሷል ከእነዚህም መካከል 3,342 ህጻናቶች እና 2,062 ሴቶች ሲሆኑ 460 አረጋውያን ናቸው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group