አንገብጋቢ እውነታ…❗️
▫️ዱዓ ለችግር ጊዜ ና ለጭንቅ መገላገያ መንገድ ብቻ የምናደርገው መሆን የለበትም።
◾️ይህች ዱንያ የፈተና አለም ነች ። እኛም ወደሷ የመጣንበት ምክንያት ለ አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ አምልኮን ለመፈፀም ነው ።
ስለዚህ ዱአ የምናደርገው አላህን ለመገዛትም መሆን ይኖርበታል ። ረሱልም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ፦
"الدعاء هو العبادة "
" ዱዓ እሱ ራሱ አምልኮት ነው "
▫️ ለአላህም ትክክለኛ ባሪያ መሆን ከፈለክ ይህን ነገር በቀንም በማታም ሁሌም አስታውሰው ......
◾️አላህን በ ልቅናው ፣ በውበቱ ፣ በታላቅነቱ ፣ በሀያልነቱ ፣ በችሮታው እና በለጋሽነቱ ተዋወቀው ። ይህም እዝነቱን ተስፋ በማድረግ ፤ ትሩፋቱን በመፈለግና ቅጣቱን በመፍራት እንድትገዛው ይረዳሃል።
✔️ ዱዓ የምታደርገው ጌታህ እንድትጠይቀው ስለሚፈልግና እሱም ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ኢባዳ ስለሆነ ነው ።
✔️ዱዓ የምታደረገው አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ ሊጠየቅና ሊለመን የሚገባው ጌታ ስለሆነ ነው ።
✔️ዱዓ የምታደርገው የአላህን ችሮታ ፈልገህና እሱን ለማመስገን ፣ ለማላቅና በብቸኝነት ለመገዛት መሆን አለበት ።
🔘ለአላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ያለህን ተገዢነት ማረጋገጥን አላማህ አድርግ ። ዱዓን የራስህን የግል ፍላጎት ማሟያ ብቻ አደርገህ እንዳታስበው ። እንዲሁም ለሆነ ጥበብ ምክንያት አላህ ምላሹን ያዘገየበህን ጥያቄህ አላህን ከመለመን ሊከለክልህ አይገባም ።
🔘በአላህ እዝነት ፣ ጥበብ ፣ ፍትሐዊነትና ለጋሽነት ያለህ እምነት ሕይወትህን በአጠቃላይ የሚሞላ መሆን አለበት እንጂ ለጊዜያዊ ፍላጎትና ዱንያዊ አላማዎችህ ለማሳካት ብቻ መሆነ የለበትም።
▫️ሕይወት ሲባል የዚህችን አጭር ሀያት ዱንያ ብቻ አደርገህ እንዳታስብ ። ሕይወት ሲባል ከዚህ ጠባብ ትርጉም እጅጉኑ የሰፋ ሲሆን የቀብርንና የ አኼራን ሃያት አጠቃሎ ይይዛል።
◾️ስለሆነም በሁሉም የሕይወትህ ክፍል ዘላቂን ደስታን የምታገኘው የዱንያ ሀያትህ ብቻ ስለተሟላልህ እንዳልሆነ ማስታወስ ይኖርብሃል። ምክንያቱም ዱንያ አንተ ሳትፈልጋትም ልትመጣለህም ትችላለች ወይም አላህ ከተወሰኑ ትሩፋቶቿ ከልክሎህ ላንተው ለ አኺራህ ሊያስቀምጥልህ ይችላል።
አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ ቸር መሆኑን አትዘንጋ ። ጠያቂውን አይመልስም። ወይ በጠየቀው ዱአ ሊመጣበት ያለን ችግር ይመልስለታል ። አልያም ደግሞ ለአኼራው ያስቀምጥለታል ።
✔️ስናጠቃለለውም ዘላለማዊ የሆነን ደስታ የሚፈልግ ሰው የባርነትን ደጃፍ ያንኳኳ !!!
ፅሁፍ✍ : ፈውዝ ቢንት አበዱለጢፍ ኩርዲ
ትርጉም : ቢንት አብደላህ
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓
©️ Toleha Ahmed
┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛