Translation is not possible.
አንገብጋቢ እውነታ…❗️
 
▫️ዱዓ ለችግር ጊዜ ና ለጭንቅ መገላገያ መንገድ ብቻ የምናደርገው መሆን የለበትም።
 
◾️ይህች ዱንያ የፈተና አለም ነች ። እኛም ወደሷ  የመጣንበት  ምክንያት ለ አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ አምልኮን ለመፈፀም ነው ።
 
ስለዚህ ዱአ የምናደርገው  አላህን ለመገዛትም መሆን ይኖርበታል   ። ረሱልም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ፦
 
"الدعاء هو العبادة "
" ዱዓ እሱ ራሱ አምልኮት ነው "
 
▫️ ለአላህም ትክክለኛ ባሪያ መሆን  ከፈለክ ይህን ነገር በቀንም በማታም  ሁሌም አስታውሰው ......
 
◾️አላህን በ ልቅናው ፣ በውበቱ ፣ በታላቅነቱ ፣ በሀያልነቱ ፣ በችሮታው እና በለጋሽነቱ ተዋወቀው ። ይህም እዝነቱን ተስፋ በማድረግ ፤ ትሩፋቱን በመፈለግና  ቅጣቱን  በመፍራት  እንድትገዛው ይረዳሃል።
 
✔️  ዱዓ የምታደርገው ጌታህ እንድትጠይቀው ስለሚፈልግና እሱም ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ኢባዳ ስለሆነ  ነው ።
 
✔️ዱዓ የምታደረገው  አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ ሊጠየቅና ሊለመን የሚገባው ጌታ ስለሆነ ነው ።
 
✔️ዱዓ የምታደርገው የአላህን ችሮታ ፈልገህና እሱን ለማመስገን ፣ ለማላቅና   በብቸኝነት ለመገዛት መሆን አለበት ።
 
🔘ለአላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ያለህን ተገዢነት ማረጋገጥን አላማህ አድርግ ። ዱዓን የራስህን የግል ፍላጎት ማሟያ ብቻ አደርገህ እንዳታስበው ። እንዲሁም ለሆነ ጥበብ ምክንያት አላህ ምላሹን ያዘገየበህን ጥያቄህ አላህን ከመለመን ሊከለክልህ አይገባም ።
 
🔘በአላህ እዝነት ፣ ጥበብ ፣ ፍትሐዊነትና ለጋሽነት ያለህ እምነት ሕይወትህን በአጠቃላይ የሚሞላ መሆን አለበት እንጂ ለጊዜያዊ ፍላጎትና ዱንያዊ አላማዎችህ ለማሳካት  ብቻ መሆነ የለበትም።
 
▫️ሕይወት ሲባል የዚህችን አጭር ሀያት ዱንያ ብቻ አደርገህ እንዳታስብ ። ሕይወት ሲባል ከዚህ ጠባብ ትርጉም እጅጉኑ የሰፋ ሲሆን የቀብርንና የ አኼራን ሃያት አጠቃሎ ይይዛል።
 
◾️ስለሆነም በሁሉም የሕይወትህ ክፍል ዘላቂን ደስታን የምታገኘው የዱንያ ሀያትህ ብቻ ስለተሟላልህ እንዳልሆነ ማስታወስ ይኖርብሃል። ምክንያቱም ዱንያ አንተ ሳትፈልጋትም ልትመጣለህም ትችላለች ወይም አላህ ከተወሰኑ ትሩፋቶቿ   ከልክሎህ ላንተው ለ አኺራህ ሊያስቀምጥልህ ይችላል።
 
አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ ቸር መሆኑን አትዘንጋ  ። ጠያቂውን አይመልስም። ወይ በጠየቀው ዱአ ሊመጣበት ያለን ችግር  ይመልስለታል ። አልያም ደግሞ ለአኼራው ያስቀምጥለታል ።
 
✔️ስናጠቃለለውም ዘላለማዊ የሆነን ደስታ የሚፈልግ ሰው  የባርነትን ደጃፍ ያንኳኳ !!!
 
ፅሁፍ✍ : ፈውዝ ቢንት አበዱለጢፍ ኩርዲ
ትርጉም : ቢንት አብደላህ
 
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
 
https://ummalife.com/ReshadMuzemil
 
┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓
       ©️ Toleha Ahmed
┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛
Send as a message
Share on my page
Share in the group