UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

አረቢያ በጠቅላላ ተሰባስባ 6 ቀን በላይ መታገስ አልቻለችም ነበር። አንዲት ገዛ የተሰኘች የምርጦች ከተማ ግን ከመከራውና ግፉ ጋር ብዙ ድሎችን ተሸክማ 45 ቀናት ሞላት።

ምድር ካፈራችው ሁሉ ነጃሳና ወራዳ ለሆነው የ "ነቲን ያሁ" ስብስብ ያጎነበሰ አዛውንት፣ እጅ የሰጠች ሴት አልያም የተማረከ ህፃን የለም። በአላህ ፈቃድም አይኖርም!

ከዚህ ጀርባ ብዙ የፅናት ምንጮች አሉ።

1★ ቁርኣን የፅናት ምንጫቸው ነው። በዛች ምድር በቃልም በተግባርም ቀንና ለሊት ሳያቋርጥ የሚነበበው የአላህ ቃል ቁርኣን!

አላህም አለ።

« قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ لِيُثَبِّتَ الَّذِينَ آمَنُوا وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ »

« እነዚያን ያመኑትን ሊያፀናና ሙስሊሞቹንም ሊመራና ሊያበስር (ቁርኣንን) ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው በላቸው፡፡ » ሱረት ነህል 102

2★ የማይነቃነቅ ኢማን የፅናት ምንጫቸው ነው። የሚያዩት፣ የሚሰሙት፣ እየኖሩት ያለው የመከራ ክምር ከተሸከሙት ከተራራ የፀና ኢማን አንፃር ምንም ነው። እኛም የምንመሰክረው ይህንኑ ነው።

አላህም እንዲህ አለ።

« إِذْ يُوحِي رَبُّكَ إِلَى الْمَلَائِكَةِ أَنِّي مَعَكُمْ فَثَبِّتُوا الَّذِينَ آمَنُوا...»

« ጌታህ ወደ መላእክቱ ባወረደ ጊዜ (ያለውን አስታውስ) «እኔ (በእርዳታዬ) ከእናንተ ጋር ነኝ። እነዚያን ያመኑትን አጽኗቸው፡፡… » ሱረት አንፋል 12

3★ የማያቋርጥና በመተናነስ የታጀበው ዱዓእ የፅናት ምንጫቸው ነው። የመከራ መነሳት፣ ትእግስትና መረጋጋት፣ ድልና አሸናፊነት ከአላህ ብቻ እንደሆኑ የሚያምኑት ገዛውያን ቀንና ሌሊት ጌታቸውን በፍፁም እምነት ውስጥ ሆነው ይጠሩታል። ዱዓእ!

አላህም እንዲህ አለ።

« وَلَمَّا بَرَزُوا لِجَالُوتَ وَجُنُودِهِ قَالُوا رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَانصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ »

« ጎልያድና ሠራዊቱን (ሊጋደሉ) በተሰለፉም ጊዜ፡-

«ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ፤ እግሮቻችንንም አፅና (በትግሉ ላይ) ፤ በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ ድልን ስጠን » አሉ፡፡ » ሱረት አል በቀራህ 250

4★ ግፍን የተሻገረው፣ መከራ ያልሸፈነው፣ ሞትና ሰቆቃ ያላዘነበለው በክስተቶቹ ውስጥ ሁሉ ያለ አላህን ማስታወስ የፅናት ምንጫቸው ነው። በአላህ ውሳኔ ላይ ያለ ያልተዛነፈ እምነታቸው በችግራቸው ውስጥ ከአላህ ጋር መኖርን ችሯቸዋል። ዚክር የፅናት ምንጫቸው ነው!

አላህም እንዲህ አለ።

« يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا لَقِيتُمْ فِئَةً فَاثْبُتُوا وَاذْكُرُوا اللَّهَ كَثِيرًا لَّعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ»

« እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (የጠላት) ሰራዊትን በገጠማችሁ ጊዜ ፅኑ፤ (መክቱ)፡፡ አላህንም በብዛት አውሱ፤ በእርግጥም ትድናላችሁና፡፡ » ሱረት አንፋል 45

5★ ለዚያ የሻም ምድር እንቁዎች የፅናት ምንጭ የአላህ እርዳታ ነው። አላህ በመንገዱ ከታገሉት ጋር ነው። ቁርኣን ሰውን ሊሰራ የመጣ ነው። እነዚህን የተሰሩ ሰዎች ሁሉ ደግሞ የአላህ እርዳታ አብሯቸው አለ። የጌታቸው እርዳታ በመንገዱ ለመፅናታቸው ምክንያቱ ነው። መዒየቱላህ!

አላህም እንዲህ አለ።

« وَلَوْلَا أَن ثَبَّتْنَاكَ لَقَدْ كِدتَّ تَرْكَنُ إِلَيْهِمْ شَيْئًا قَلِيلًا »

« ባላፀናንህም ኖሮ ወደነሱ ጥቂትን (ዝንባሌ) ልትዘነበል በእርግጥ በተቃረብክ ነበር፡፡ » ሱረት ኢስራእ 74

6 ★ የፅናት ምንጫቸው የሚያስፈልገውን ዋጋ ሁሉ መክፈላቸው ነው። ሀብት፣ ንብረት፣ ገንዘብና ነፍሳቸውን ከፈሉ። እነርሱ ዘንድ ምንም ትልቅ የሚባል ነገር የለም። ሁሉም ለአላህ ከሚከፍሉት አንፃር ትንሽ ነው። እነርሱ ዘንድ ሞትና ህይወት እኩል ሆኗል። ስለዚህም አላህም አፀናቸው።

አላህም እንዲህ አለ።

« وَمَثَلُ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمُ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ وَتَثْبِيتًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ ... »

« የእነዚያ የአላህን ውዴታ ፈልገው እና ለነፍሶቻቸው (እምነትን) ለማፅናት ገንዘቦቻቸውን የሚለግሱ ሰዎች… » ሱረት አል በቀራህ 265

በእነዚህ መሰል የአላህ አንቀፆች ውስጥ እየኖሩ ያሉ ሰዎች መፅናታቸው የግድ ነው። ቁርኣን የሰራቸውን ሰዎች መመልከት ከፈለግክ ወደነርሱ ተመልከት።

“ጌታዬ ሆይ በፅናታቸው ላይ ፅናትን ለግሳቸው።”

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ምዕራቡ አለም በብሪቴይን እርግዝና በፈረንሳይ አዋላጅነት በጥቅመኛ አረቦች አጨብጫቢነት የወለዷትን የግፍና የበደል ልጅ መጠበቅ ላይ መተባበር መያዛቸው ብዙ አያስገርምም። ታማኝነት አልባ፣ የሁለት ሚዛን ባለቤት ከሆኑት የግፍ መሪዎችና ልሂቃን ስብስብ ከዚህ የተለየ መጠበቅም የዋህነት ነው። ቅሉ ሁሉም ነገር ማብቂያ አለው፤ ሁሉም ነገር መጠናቀቂያ አለው።

★ ማብቂያውም ፍትህን ለተነፈጉት ሁሉ ብርሃን መሆኑ ነው። ወላዱም፣ ያዋለደውም፣ ያጨበጨበውም፣ የተወለደውም የበደልና የግፍ ልጅም መዋረዳቸው አይቀርም። በነፍሶቻቸው ውስጥ የነገቡት የበላይነትና ሁሉን አድራጊነት መንፈስ ቅዠት መሆኑ አይቀርም። የአላህ ቃል እንዲህ ይላል።

« إن الذين كفروا ينفقون أموالهم ليصدوا عن سبيل الله فسينفقونها ثم تكون عليهم حسرة ثم يغلبون… »

« እነዚያ የካዱት ሰዎች ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘባቸውን ያወጣሉ። በእርግጥም ያወጣሉ። (ካወጡም በኃላ) ፀፀት ትሆንባቸዋለች። ከዚያም ይሸነፋሉ። የካዱት ሰዎች ወደ ገሀነምም ይሰበሰባሉ።»

እንዲህም ይላል።

« …عسى الله أن يكف بأس الذين كفروا والله أشد بأسا وأشد تنكيلا »

« … አላህ የካዱትን ሰዎች ኃይል ሊከለክልልህ ይከጀላል (ይከለክልልሃል)። አላህም በኃይል ሲይዝ የበረታ፤ ቅጣቱም እጅግ ጠንካራ ነው። »

★ በተቃራኒው በበደል ውስጥ በትግልና በትእግስት፣ በትእግስትና በትግል ያለፉት ሁሉ የአላህ እርዳታ እየጨመረላቸው፤ እዝነቱንና እገዛውን እያሰፋላቸው፤ የድልን ካባ እንደሚያጎናፅፋቸው እርግጥ ነው።

ለተወዳጁ መልእክተኛው (ሰዐወ) አላህ እንዲህ ይላቸዋል።

« …فسيكفيكهم الله وهو السميع العليم »

« … ከእነርሱም (ከከሃዲያኑ) አላህ ይበቃሃል። እርሱ ሰሚና ዐዋቂው ነው። »

እንዲህም ይላል።

« أليس الله بكاف عبده ويخوفونك بالذين من دونه… »

« አላህ ለባሪያው በቂ አይደለምን? ከእርሱ ውጪ (በታች በሆኑት ጣኦቶቻቸው) በሆኑት ነገሮች ያስፈራሩሃል። … »

اللهم افرغ على المجاهدين الصابرين الصبر وانصرهم على الظالمين الغاصبين

#الأقصى حياتنا

والموت في سبيلها اسمى امانينا

Send as a message
Share on my page
Share in the group
ibro hulgicho Сhanged his profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

« ይህች ኡማ (ህዝብ) ከባድ የመከራ ምጥን እያሳለፈች ነው። ለሁሉም ምጥ ደግሞ ልጅ አለው። ለሁሉም ልጅ ደግሞ ጩኸትና ህመም አለው። »

ሸሂድ (በአላህ ፈቃድ) ሰይድ ቁጥብ (ረህመቱላሂ ዐለይሂ)

ይህ የመከራ ምጥ በነዚህ ልጆች ልብ ውስጥ የሚፈጥረው ልጅ ይናፍቀኛል። አንረሳህም! አንረሳውም!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
ibro hulgicho Сhanged his profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group