UMMA TOKEN INVESTOR

Medina Ahmed shared a
Translation is not possible.

አንድ ሰው ከአንድ ቤተሰብ የሆነችን ሴት አገባ፤ አንዳንድ የቤተሰቡ አባላት በዘር የሚተላለፍ በሽታ ነበራቸው፤ ይህ ደግሞ በዕድሜ መግፋት የመስማት ችሎታ እያሽቆለቆለ መሄድ ነው!

ባልየው የሚስቱ የመስማት ችሎታ እየደከመ እና እየቀነሰ መምጣቱን ጠረጠረ!!

ይህን የነገረውን የቤተሰብ ሀኪም አማከረ፡- የሚስትህን የመስማት ችሎታ ለማረጋገጥ ቀላል መንገድ አለ እሱም መካከለኛ በሆነ ድምፅ 50 ጫማ ያህል ራቅ ብለክ ትናገራለክ ከዚያም ወደ 40 ጫማ ቀርበህ ትናገራለክ ካልመለሰችልክ ወደ 20 ጫማ ከዚያም ወደ 10 ጫማ ትመጣለህ ካልመለሰች በቃ አጠገቧ ቆመክ ትነግራታለክ በዚህ መልኩ የባለቤትክን የመስማት ችሎታ ጥንካሬ ታረጋግጣለክ።

በእርግጥም ባልየው ወደ ቤት ተመለሰ እናም ሚስቱ ኩሽና ውስጥ ምሳ እያዘጋጀች ነበረ እሱም ከ50 ጫማዋ ርቆ ሄዶ፡- ውዴ ለምሳ ምን እየሰራሽ ነው? አልመለሰችለትም ወደ 40 ጫማ ጠጋ አለና ውዴ ፣ ለምሳ ምን እየሰራሽ ነው?” አልመለሰችለትም ወደ 20 ጫማ ጠጋ ብሎ ጥያቄውን ደገመው እሷ አሁንም አልመለሰችም! ከዚያም ወደ 10 ጫማ ጠጋ ብሎ ጥያቄውን ደገመው አሁንም አልመለሰችለትም!

በመጨረሻም ከኋላዋ ቆሞ፣ ለምሳ ምን እየሰራሽ ነው?” አላት።

ወደ እሱ ዘወር አለችና፡- “ የዶሮ አሩስቶ ” ይህን ስነግርህ ለአምስተኛ ጊዜ ነው!!! አለችው።

ሁልጊዜ አንተ ብቻ ትክክል እንደሆንክ አድርገህ አታስብ ነገሩን በፍትሃዊነት ከተመለከትክ ችግሩ ያንተ እና የአንተ ሊሆን ይችላል❗️❗️❗️

https://t.me/AbuEkrima

https://t.me/AbuEkrima

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Medina Ahmed shared a
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Medina Ahmed shared a
Translation is not possible.

ካነበብኩት...

#ባሏን #የገደለው #መርዝ 🥺😥

ከእለታት በአንድ ቀን አንዲት ውብ የሆነች ልጃገረድ ባገባች በሁለተኛ ዓመቷ ትዳሯ ምርር ስላላት ባሏን ለመግደል ፈለገች።

ይህች ቆንጆ ልጅም ወደ እናቷ ቤት በመሄድ "እናቴ የባሌ ነገር አድክሞኛል የሚያደርጋቸው ነገሮች ሰልቺተውኛል፣ለእኔ አያስብልኝም፣ዞር ብሎ እንኳን አያየኝም እኔንጃ ከሌላ ሴት

ጋር የጀመረው ነገር አለ እርሱን ገድዬ መገላገል እፈልጋለሁ በአንድ በኩል ደግሞ ህግ ያስረኛል ብየ እፈራለሁ እና እባክሽ እርጅኝ?አለቻት።

እናቷም:-እሺ እረዳሻለሁ የእኔ ውድ ልጅ ግን መጀመሪያ የምታደርጊያቸው ነገሮች አሉ አለቻት።

ልጅቷም:አንቺ ያልሽኝን ነገሮች በሙሉ እፈጽማለሁ አለች።

እናትየዋም:-ባልሽ ሞቶ አስከሬኑ ከቤት እስኪወጣ ድረስ ከዚህ በታች ያሉትን 6 ነገሮች በጥንቃቄ ፈጽሜያቸው አለች።

1.የገደለችው እርሶ ናት ብለው እንዳይጠረጥሩሽ ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ፍጠሪ።

2.ሁልጊዜ ውበትሽን ጠብቀሽ ወጣትና ውብ ሁነሽ ታይ።

3.በደንብ አድርገሽ ተንከባከቢው ጥሩ ሁኝለት አበርችው።

4.ትዕግስት አድርጊ ብዙም አትቅኚ፣ብዙ ጊዜ አድማጭ ሁኚ በማክበር ታዘዥው።

5.በእጅሽ ያለውን ገንዘብ አንዲችም በለሽ ሳታስቀሪ እርሱን ለማስደሰት አውይው።

6.ማንም ገድላዋለች ብሎ እንዳያስብ የጭቅጭቅ ድምፅ ከአፍሽ እንዳይወጣ ሰላም እና የፍቅር ቃል ከአፍሽ ይውጣ እስክትገላገይው ድረስ ብቻ።

እናትዮዋ:-በድጋሚ ያልኩሽን ነገሮች ሳታዛንፊ ታደርጊለሽ አለቻት?

ልጅቷም እርሱ ሞቶ ይውጣልኝ እንጂ አንድም ሳላስቀር አደርገዋለሁ ብላ መለሰች።

እናትየዋም አንድ ብልቃጥ አውጥታ ይህን መርዝ ያዥውና ሁሌም ከሚበላው ምግብ ጋር እየጨመርሽ ስጭው መርዙም አመንምኖ ይገድለዋል።

ልጅቷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ተመለሰች።

ልጅቷ:-ከአንድ ወር በኋላ ተመልሳ ወይ ጉድ ሰውየው ወሬውን ሳይሰማ አይቀርም ድሮ አድርጎት የማያውቀውን "ማሬ፣ፍቅሬ፣ወለላዬ፣

ህይወቴ፣ንግስቴ፣በዓለም ላይ አንቺን የምታክል ሴት የለችም ይለኛል እኔ እንጃ ፀባዩ ልውጥውጥ ብሎብኛል።

እናትየዋም:-መርዙን እየሰጠሽው ነው አለቻት?ልጅቷም አይኗ እንባ እያቀረረ

አዎ ግን አሁን ፀባዩ ሸጋ፣አፍቃሪ ባል ኋኖል እና እንዲሞትብኝ አልፈልግም እባክሽ ማርከሻ መድሀኒት ፈልጊልኝ ፀፀቱ ሊገለኝ ነው እማዬ???

እናትየዋም:-ልጄ በብልቃጥ የሰጠሁሽ መርዝ አይደለም የእርድ ዱቄት ነው።ነገር ግን ቀስ በቀስ መጥፎ ባልሽን የገደልሽው "መርዟ አንቺ ነበርሽ" ማለቴ እሱን ማፍቀር ፣መታዘዝ ፣መንከባከብ ፣መታገስ

እና ውብ ሁነሽ ስትገኝ ባልሽን መቀየር ትችያለሽ።

አንቺ ያልሰጠሽውን ነገር እንዴት ከሌላ ሰው ትጠብቂያለሽ? ፍቅር ማለት ሰጥቷ መቀበል ነው።

አስተማሪ ሆኖ ካገኙት 👍

Send as a message
Share on my page
Share in the group