#በህይወት ውጣ ውረድውሰጥ ስትኖር የሚጠቅሙህ እና ልብ ልትላቸው የሚገቡ #8 ነጥቦች
*****
1. #ያለፈ #ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!
ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፣
ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር፣
ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም።
2.#የሰዎች ሃሳብ #የአንተን ማንነት አይገልፅም!
ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፣
መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ
(ጉዞ) ይለያያል ፣ ለሁሉም ጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና።
3. #ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ #ለሀዘናቸው መንስዔ አትሁን!
►በሰዎች ደስታ→ደስ ይበልህ!
►ለሰዎች→ክፉ አትመኝ፣
►በሃዘናቸውም→አብረህ እዘን፣
►ሰዎች ሲያዝኑ→አትደሰት፣
►ሰው ከሆንክ→የሰው ነገር ይሰማህ፣
ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት
አይደለም። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋ ሁን፣ አስተውል።
4. #በጊዜ ስራ እንጂ #ጊዜ ባንተ ላይ አይስራ!
ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም። አንተንም ጊዜውይ ቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት፣ በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን
5.''ሰው #የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን አባባል #አስታውስ፣
የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው
ይገጥምሃል። ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ ራስህን አትሸውድ።
ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ፣ ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ
እንደሚያጭድ ሁሉ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።
6. #ለራስህ ስትል #መልካም ሁን፣ በጎውንም አስብ!
ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም።
7. #መልካም ጓደኛ ከፈጣሪ የሚሰጥ ጸጋ መሆኑን አትርሳ
√የጓደኛህን ስሜት ለመራዳት ሞክር!
√መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት
√አበረታታው
√እንደማይጠቅም አትንገረው
√ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክኒያት ሁን
√ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን
8. #መልካም ጓደኛ ሁን!
#መልካም ጓደኛ፦ የማይቀና አሳቢና መካሪ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ታድለሃል።
ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ።