UMMA TOKEN INVESTOR

Halima Seid shared a

☝️እቺን መልዕክት ወላሂ ሼር አደርገዋለሁ እርግጠኛ ነኝ ሼር ልታደርገው ነው

ምክንያቱም ወላሂ ብለሀል!!

▪️ስትወለድ ከእናትህ ሆድ ማህፀን ያወጣህን ፈፅሞ አታውቅም

▪️ስትሞት ማን ወደ ቀብርህ እንደሚያስገባህ ፈፅሞ አታውቅም

▶️የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ

▪️ስትወለድ ትታጠባለህ ትፀዳለህ ስትሞት ትታጠባለህ ትፀዳለህ

▪️ስትወለድ ማን እንዳዘነና ማን እንደተደሰተ አታውቅም

▪️ስትሞትም ጊዜ ማን እንደሚያለቅስልህ ማን እንደሚቀብርህ አታውቅም

የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ

▪️በእናትህ ሆድ ውስጥ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ነበርክ

▪️ስትሞት ጊዜ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ትሆናለህ።

የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ

▪️ስትወለድ በጨርቅ ትጠቀለላለህ ሊሸፍኑህ ስትሞት በከፈን ይጠቀልሉሃል ሊሸፍኑህ

▶️የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ

▪️በተወለድክና በአደክ ጊዜ ሰዎች ምስክር ወረቀት ስለሙያህ ይጠይቁሀል

▪️በሞትክም ጊዜ በመላኢካዎች ስለመልካም ስራህ ይጠይቁሀል

_ለመጨረሻው ሀገርህ ምን አዘጋጀህ❗️❓

〽️ከልብህ ይህቺን ቃል ለመናገር ሞክር

▪️ከአላህ ሌላ በፍፁም የሚመለክ አምላክ እንደሌለ መስክር እንዲሁም ሙሀመድﷺ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መስክር

ይህቺን መልእክት ፍፁም ሳታነባት እንዳትልካት

قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ اللَّهُ الصَّمَدُ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ

(#ሱረቱ_አል_ኢኽላስ)

((በል እርሱ አላህ አንድ ነው አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው አልወለደም አልተወለደምም ለእርሱ አንድም ብጤ የለውም))

መልዕክቱን ሼር አድርገው በአንተ ሠበብ የቁርአን አንድ ሶስተኛውን ይቀራሉ ያነባሉ ነፍስህን አጅር አትከልክላት!!

እርግጠኛ ነኝ አንድም ቀን አስበህው ምታውቅ አይመስለኝም

እባኮ በማያልቀው የአላህ አጅር ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Halima Seid shared a
Translation is not possible.

እስራኤል በጘ-ዝ'ዛ ከተማ ላይ በፈጸመችው የአየር ድብደባ፦

√ 47 መስጂዶች፣

√  7 ቤተ ክርስቲያኖች፣

√ 220 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን የያዙ 32 ሺህ ህንጻች፣

√ 203 ትምህርት ቤቶች፣

√  80 የመንግስት መስሪያ ቤት ህንጻች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

በተጨማሪም፦

√ ከ8 ሺህ በላይ ንጹሐን (ከ3342 በላይ ህፃናትና ከ2 ሺህ በላይ ሴቶች) ተገድለዋል፣

√ ከ20 ሺህ በላይ የሚሆኑት ቆስለዋል፣

ከ15 በላይ የሚሆኑት ተፈናቅለዋል።

አላሁ-ል-ሙስተዓን! አላህ በቃችሁ ይበላቸው። ወራሪ'ዋንም ከነ አጋሮቿ ቀኗን ያቅርብልን።

https://ummalife.com/Mamekamil

Mohammed Kamil | UmmaLife

Mohammed Kamil | UmmaLife

Mohammed Kamil: Mohammed Kamil. Nikname: @Mamekamil | One Ummah — One Network - was created as a response to the Internet technology needs of Muslims and all adherents of traditional value
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Halima Seid shared a
Translation is not possible.

ያስፈልገዎታል!!

ጀናባን የሚመለከቱ ህግና ደንቦች

የቃላት መፍቻ፡-

1. መኒይ (የዘር ፈሳሽ)፡-

- በስሜት ተስፈንጥሮ ከእርካታ ጋር የሚወጣ ፈሳሽ ነው፡፡

- ለወንድ ወፍራምና (ወደ ቢጫነት የሚያደላ) ነጭ ፈሳሽ ሲሆን ለሴት ደግሞ ቀጭንና ቢጫ ነው፡፡ [ሙስሊም፡ 311] ሽታው ወደሊጥ ሽታ የቀረበ ነው፡፡ በሆነ ምክንያት እነዚህ መታወቂያዎች ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡

- ከወጣ በኋላ የሰውነት መቀዝቀዝ ዘና ማለት (ፉቱር) ይከተላል፡፡

- ፈሳሹ ሚዛን በሚደፋው የዑለማእ እይታ ጦሀራ እንጂ ነጃሳ አይደለም፡፡ ይህን የሚደግፉ ሶሒሕ ማስረጃዎች መጥተዋል፡፡ [ሙስሊም፡ 694] [አልኢርዋእ፡ 1/197]

- በውንም ይሁን በህልም ከወጣ ገላን መታጠብ ግዴታ ነው፡፡

2. መዚይ፡-

- ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግ (የሚያጣብቅ)፣ ቀለም አልባ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡

- አወጣጡ ከእርካታ ጋር አይደለም፡፡ ተስፈንጥሮ ስለማይወጣ መውጣቱ ላይስተዋል ይችላል፡፡

- ነጃሳ ስለሆነ የነካውን አካል ማጠብ ይገባል፡፡ ልብስን ግን የነካው ቦታ ላይ ውሃ በመርጨት ማፅዳት በቂ ነው፡፡

- የነካውን ቦታ እንጂ ገላን መታጠብ ግን ግዴታ አይደለም፡፡ ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡

3. ወዲይ፡-

- ከሽንት በኋላ የሚወጣ ነጭ ሽታ አልባ ፈሳሽ ነው፡፡

- የሚያጣብቅ አይደለም፡፡

- ብይኑ ከሽንት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

4. ከሴቶች ብልት የሚወጣ ፈሳሽ፡-

- ከማህፀን የሚወጣ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡ መጠኑ ከሴት ሴት ይለያያል፡፡

- ሴቷ መውጣቱንም ላታስተውለው ትችላለች፡፡

- አካልንም ልብስንም ቢነካ አይነጅስም፣ ጦሃራ ነው፡፡

- ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡ ከሁለቱም መፀዳጃዎች በኩል የሚወጣ ነገር ውዱእ ያፈርሳልና፡፡ አወጣጡ ቋሚ ከሆነ ግን ለያንዳንዱ ሶላት ወቅቱ ከገባ በኋላ ውዱእ እያደረገች መስገድ ይገባል፡፡ ውዱእ ካደረገች በኋላ ቢወጣ ቦታም አይሰጠውም፡፡

ገላን መታጠብ ግዴታ የሚሆነው መቼ ነው?

1. በውኑ ግንኙነት ከተፈፀመ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) #ቢፈስም_ባይፈስም ትጥበት ግዴታ ነው፡፡

2. ግንኙነት #ባይፈፀምም የዘር ፈሳሽ (መኒይ) #ከእርካታ ጋር ከወጣ ትጥበት ግዴታ ነው፡፡

3. በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካገኘ በማያሻማ መልኩ መታጠብ ግዴታ ነው፡፡

4. በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ ነገር ግን ሲነቃ ምንም አይነት የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካላገኘ በማያሻማ መልኩ የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ ኡሙ ሱለይም የተባለችዋ ሶሐቢያህ ረዲየላሁ ዐንሃ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንዲት ሴት ኢሕቲላም ከሆነች (በህልሟ ግንኙነት ስትፈፅም ካየች) የመታጠብ ግዴታ አለባትን?” ብላ ስትጠይቅ “ፈሳሽ ካየች አዎ” ሲሉ መልሰውላታል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]

5. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካገኘ በማያሻማ መልኩ የመታጠብ ግዴታ አለበት፡፡

6. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ ፈሳሽ አገኘ፡፡ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) እንዳልሆነ እርግጠኛ ከሆነ የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ የነካውን ግን ሊያጥብ ይገባል፡፡ ብይኑ የሽንት ብይን ነውና፡፡

7. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን #መለየት_ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘ በ ሽታ ወይም በቻለው መንገድ ለመለየት ይሞክርና ጥርጣሬው መኒይ ወደመሆኑ ካደላ ይታጠብ፡፡ ጥርጣሬው መዚይ ወደመሆኑ ካደላ ግን በተለይም ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት አስቦ ከነበር እንደ መዚይ ይቁጠረውና የነካውን ቦታ ብቻ ይጠብ፡፡ ገላውን የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡

8. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን #መለየት_ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘና ግምቱ ወደየትኛውም ካላደላ፣ ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት #ያላሰበ ከሆነ ጉዳዩ አወዛጋቢ ቢሆንም ትክክለኛው ትጥበት የለበትም የሚል ነው፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡ [ፈታዋ ኢብኑልዑሠይሚን፡ 11/161]

የጀናባ አስተጣጠብ ሁለት አይነት ነው፡፡

1. የሚያብቃቃ ማለትም ግዴታውን ለማውረድ የሚጠበቅ ሲሆን እሱም ሙሉ አካልን በውሃ ማዳረስ ነው፡፡ ባይሆን መጉመጥመጥና በአፍንጫ ውሃ መሳብ (ኢስቲንሻቅ) እንዳይረስ፡፡ ለትጥበት ኒያ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ አንድ ሰው ጀናባ ማውረድን ሳያስብ እንዲሁ ውሃ ውስጥ ዋኝቶ ቢወጣ መላ አካላቱ ውሃ መንካቱ ብቻ ጀናባው ለመውረዱ በቂ አይሆንም፡፡ ይስተዋል! ይህን ትጥበት ካደረጉ በኋላ ውዱእም ባያደርጉ መስገድ ይቻላል፡፡ ባይሆን ከትጥበቱ መሀል ውዱእ የሚያፈርስ ነገር መፈፀም የለበትም፡፡

2. ሌላኛውና በላጩ ግን በቅድሚያ ሁለት እጆችን መታጠብ፡፡ ከዚያም ኢስቲንጃእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ውዱእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ከእራስ ጀምሮ ቀሪ አካላትን ውሃ ማዳረስ፡፡ እግርን ከውዱእ ጋር ማጠብም ይቻላል፤ መጨረሻ ላይ ማጠብም ይቻላል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]

ማሳሰቢያ፡-

ሴቷ ለትጥበት ስትል የፀጉር ጉንጉኗን የመፍታት ግዴታ የለባትም፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም: ኡሙ ሰለማህ ለጀናባህ ወይም ለሐይድ ትጥበት ፀጉሯን “ልፍታው ወይ?” ብላ ስትጠይቃቸው “አይ! የሚበቃሽ ከእራስሽ ላይ ሶስት ጊዜ ውሃ ማፍሰስ ብቻ ነው” ብለዋታል፡፡ [ሙስሊም] ስለዚህ ፀጉር ሳይፈታ ውሃ መድረስ ከቻለ መፍታት አይጠበቅም፡፡

ለማጣቀሻነት የተጠቀምኩት

1. ፈታዋ ኢብኑልዑሠይሚን

2. ፈትሑልዐላም ፊ ዲራሰቲ አሓዲሢ ቡሉጊልመራም እና ሌሎችም

ሼር ማድረግ እንዳይረሱ፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር 8/2008)

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አልሀምዱሊላህ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Halima Seid Changed her profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group