UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
1
Abdulkerim Husen Сhanged his profile picture
7 ай
Татарчага аудару мөмкин түгел.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
7 ай Тәрҗемәсе
Татарчага аудару мөмкин түгел.

ወጣትም ይሞታል የእድሜ መርዘምም ብቻ ዋጋ የለውም!

~

ኢብኑ ባዝ እንዲህ ይላሉ

«እኔ ወጣት ነኝ ቀስ ብዬ እቶብታለሁ አትበል!(ምክንያቱም) ስንትና ስንት ወጣት ሳያረጅ ሞት ወስዶታልና። ስንትና ስንት አዝመራ ሳይታጨድ ጠፍቷል(ልክ እንደዚሁ ወጣትም ሳያረጅ ይሞታል)  ሞትኮ ድንገት ነው የሚመጣው(ነገር ግን) መልካም ስራ ከሰራህ በዱንያም በአኺራም ይጠቅምሀል።»

[መጅሙአል ፈታዋ ሊብኑ ባዝ 24/354]

*አኺል ከሪም! ገና ነኝ እድሜዬ ይረዝማል አትበል! የእድሜህ መርዘም መልካም ስራ ካልሰራህበት በዱንያ ላይ ድካምን መጨመር ሂሳብህን ማብዛት እንጂ ቅንጣት ታክል ጥቅም የለውም! ነገር ግን ስራህ አምሮ እድሜህ ከረዘመ እመነኝ ከሰዎች በበለጠ ምርጡ ሰው ነህ!

📂 አንድ ቀን ሁለት ዘላኖች ወደ መልእክተኛውﷺ ዘንድ መጥተው አንድኛው እንዲህ ሲል ጠየቃቸው

አንቱ ያአላህ መልእክተኛ ሆይ ከሰዎች ሁሉ በላጩ ማነው?

የአላህ መልእክተኛﷺ እንዲህ አሉት

እድሜው ረዝሞ ስራው ያማረ ምንኛ ታደለ! አሉት

ከስራስ በላጩ ምንድነው? አላቸው

ምላስህ አላህን በማውሳት እርጥብ ሁና ዱንያን መለየትህ ነው አሉት።[አስ ሰሂሃህ 4/452]

አዎን! እድሜህ ረዝሞ ስራህ ካማረ ነገ በመልካም ስራህ የጀነት ደረጃን ትጨምራለህ! እድሜ ስጠኝ ብለህ ለምነህ መልካም ስራ ከሌለበት ቁልቁል በእሳት ያሰርግሀል!!

✍️አብዱልከሪም ሁሴን

Send as a message
Share on my page
Share in the group
7 ай Тәрҗемәсе
Татарчага аудару мөмкин түгел.

ሸሪአዊ እውቀት ትልቁ መሳሪያህ ነው!!

~~~~

ሸይኽ አብዱረህማን አስ-ሰእዲ እንዲህ ይላሉ

اعلم هديت أن أفضل المنن....علم يزل عنك الشك والدرن

አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራህና እወቅ! ከፀጋዎች ሁሉ በላጩ ፀጋ ካንተላይ ጥርጣሬንና ቆሻሻን የሚያስወግድልህ (ሸሪአዊ) እውቀት ነው።[መንዙመቱ አል-ቀዋኢድ አል-ፊቅህያህ ሊኢማም አስ-ሰእዲ]

«ከሸሪአዊ እውቀት ባህሪና ሁኔታ ጥርጣሬን የማስወገድ ብዥታን የመከላከል አቅም አለው።

ልክ እንደዚሁ የስሜት ቆሻሻን የማስወገድ አቅምም አለው። ምክንያቱም (በሰውየው ውስጥ) አላስፈላጊ ስሜትን ያዳክማል። ተፈጥሯዊ ስሜቱን ሸሪአ በፈቀደለት ውስጥ እንጂ አይተገብርም።

ስለዚህም ሸሪአዊ እውቀት ለአንድ ሙስሊም(የብዥታንና የስሜትን) ፈተና ከሚከላከልበት መሳሪያዎች ውስጥ ትልቁ መሳሪያ ነው።» [ሸይኽ ሱለይማን አር-ሩሀይሊ ደዋቢጥ ፊልፊትና ከሚለው የሙሀደራ ካሴት የተወሰደ]

✍️አብዱልከሪም ሁሴን(አቡ ሱለይማን)

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group