ወጣትም ይሞታል የእድሜ መርዘምም ብቻ ዋጋ የለውም!
~
ኢብኑ ባዝ እንዲህ ይላሉ
«እኔ ወጣት ነኝ ቀስ ብዬ እቶብታለሁ አትበል!(ምክንያቱም) ስንትና ስንት ወጣት ሳያረጅ ሞት ወስዶታልና። ስንትና ስንት አዝመራ ሳይታጨድ ጠፍቷል(ልክ እንደዚሁ ወጣትም ሳያረጅ ይሞታል) ሞትኮ ድንገት ነው የሚመጣው(ነገር ግን) መልካም ስራ ከሰራህ በዱንያም በአኺራም ይጠቅምሀል።»
[መጅሙአል ፈታዋ ሊብኑ ባዝ 24/354]
*አኺል ከሪም! ገና ነኝ እድሜዬ ይረዝማል አትበል! የእድሜህ መርዘም መልካም ስራ ካልሰራህበት በዱንያ ላይ ድካምን መጨመር ሂሳብህን ማብዛት እንጂ ቅንጣት ታክል ጥቅም የለውም! ነገር ግን ስራህ አምሮ እድሜህ ከረዘመ እመነኝ ከሰዎች በበለጠ ምርጡ ሰው ነህ!
📂 አንድ ቀን ሁለት ዘላኖች ወደ መልእክተኛውﷺ ዘንድ መጥተው አንድኛው እንዲህ ሲል ጠየቃቸው
አንቱ ያአላህ መልእክተኛ ሆይ ከሰዎች ሁሉ በላጩ ማነው?
የአላህ መልእክተኛﷺ እንዲህ አሉት
እድሜው ረዝሞ ስራው ያማረ ምንኛ ታደለ! አሉት
ከስራስ በላጩ ምንድነው? አላቸው
ምላስህ አላህን በማውሳት እርጥብ ሁና ዱንያን መለየትህ ነው አሉት።[አስ ሰሂሃህ 4/452]
አዎን! እድሜህ ረዝሞ ስራህ ካማረ ነገ በመልካም ስራህ የጀነት ደረጃን ትጨምራለህ! እድሜ ስጠኝ ብለህ ለምነህ መልካም ስራ ከሌለበት ቁልቁል በእሳት ያሰርግሀል!!
✍️አብዱልከሪም ሁሴን