UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

የትኛውን ትመርጣለክ #ታዋቂነትን ወይስ #አዋቂነት?………ራሳችንን እንጠይቅ……የትኛው ይሻለናል……በየትኛውስ መንገድ ላይ ነን……ይከብዳል አይደል ታዋቂዎች በበዙበት ዘመን አዋቂ ሆኖ መገኘት……በሰዎች ዘንድ ታውቀህ…ስለ አንተ በየ ቦታው ሲወራ መስማት……በብዙ ሰዎች ውዴታን ማግኘት……ስምህ በየ ቦታው ሲጠራ መስማት……ወሬዎችህ ቁም ነገር ያዘሉ ባይሆኑም በብዙ ሰዎች መደመጥህ እና ሲጨበጨብልህ… …ምን ይሰማሀል ብልህ ደስታ ነዋ ትላለክ በሙሉ እምነት……ግን የእውነት እነዚ ነገራቶች አንድ ሰውን ለማስደሰት በቂ ይሆናሉን……በፈጠረህ ጌታህ ዘንድ ታዋቂነት ሳይኖርህ እሱ በፈጠራቸው ፍጡራኖች መታወቅህ መደነቅህ ሊያስደስትህ ይገባልን?……ታዋቂነትን ሳይሆን አዋቂነትን ምረጥ… …የዛኔ እውነተኛ ደስታን ወደ ሂወትህ ታመጣለክ ከአለም ተደብቀህ……አለም ላይ ያሉ ሰዎች ሳያውቁህ አለምን የፈጠረው ጌታህ ዘንድ ታዋቂነትን ማፍራት አስበው እስኪ……ይሄ የሚሆነው ግን ከታዋቂነት አለም ስትወጣ ወደ አዋቂዎች አለም ስትገባ ነው……እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ… …ስንት አዋቂዎች እና ስንት ታዋቂዎችን እንደምናውቅ… …አዋቂነትን በራስህ ላይ ገምብተህ በጌታህ ዘንድ ታዋቂነትን አፍራ……።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#ነፃነትን #ማጣት……ይሄን ትልቅ ፀጋ የሚረዳው ያጣው ሰው ብቻ ነው።…ሌሎቻችንማ ቢነገረንም ተረት፣ወይ ደግሞ ቀላል ነገር ነው ምን ያካብዳል ብለን የምንሳለቅም አንጠፋም……ግን በዱኒያ ላይ እየኖሩ ነፃነትን እንደማጣት ከባድ ነገር የለም……በተለይ ደግሞ ይሄን ፀጋ ያሳጡህ ሰዎች ከሆኑ፣ እንደዚሁም ካለ ምንም ጥፋት እና ወንጀል ሲሆን ህመሙ እጥፍ ይሆናል……አስቡት እስኪ አንድ ሰው… …ለብዙ ወራቶች ካለ ወንጀሉ ታስሮ… …በሂወቱ ብዙ ነገሮች ሲበላሹ ሲጠፉ ……ማሳለፍ ያለበት የደስታም ሆነ የሀዘን ጊዜዎች አራት መአዘን ክፍል ውስጥ ተዘግቶበት ሲያልፉት… የእውነት ይሄ ነገር የማያመው ሰው ይኖር?……በአሁን ሰአት #በሳኡዲ #እስር #ቤት #ካለምንም #ወንጀል ታስረው እየተሰቃዩ ያሉ ወንድም እና እህቶቻችን ብዙ ናቸው……ቤተሰቦቻቸውን አጥተው ሀዘናቸውን ያልተወጡ……በሀገራቸው ሰላም ማጣት ጠዋት ማታ የሚረበሹ……የቤተሰቦቻቸውን ደስታ አብረው ያልተካፈሉ……የእናቶቻችን ልጄ ዛሬ መጣ ነገ እያሉ በጉጉት አይናቸው መንከራተቱ……ስንት ህፃናቶች አባቴ አትመጣም……ቆየህኮ……እናቴ መቼ ነው የምትመጪው……እያሉ በጨቅላ አእምሯቸው የሚናፍቁ ስንት ህፃናት እንዳሉ ቤታችን ይቁጠረው።……አንድ ሰው እንኳን ታስሮ ይቅር እና ለአንድ ቀን እቤቱ ከልጆቹ ከቤተሰቦቹ ጋር ሙሉ ቀን ቤት ቢውል የሆነ ሰአት ላይ ደበረኝ ወደ ውጭ ወጣ ብዬ ልምጣ ሲል እንሰማለን………አስበነዋል ያውም በወዳጆቹ ተከቦ……ታዲያ ካለ ወንጀል ለብዙ ቀናቶች ፣ለብዙ ወራቶች፣ብሎም ለአመታት መታሰር……ይከብዳል የሚለው ቃል ይገልፀው ይሆን?…… በእርግጥም አሏህ ባሮቹን አይበድልም ምናልባትም አንዳንዴ በሆኑ ከባድ ጊዜያቶች ማለፍ ትልቅ ት/ት እንድንማር ያደርጋል…… ግን ያው የሰው ልጅ አይደለን የሆነ ቀን ይሰለቻል……የሆነ ቀን ይመራል……የሆነ ቀን ሰብርም ያልቃል……ከዛም አሏህ ያዘነለት ሲቀር ማማረር ይጀምራል………ተስፋም መቁረጥ ይጀምራል……በቃ ይሄ ነው የኔ መጨረሻ የሚል አስጠሊ ደውል ከአእምሮው ሲደወል ይሰማል……ፈልጎኮ አይደለም ያለበት ሁኔታ አስገድዶት እንጂ።………ምክር እና ቦክስ ለሰጪው አይደል የሚባለው……… እርግጥ ነው የሆነ ሰው ጫማ ላይ ካልቆምን ስሜቱን ሙሉ በሙሉ መረዳት ይከብዳል።……ግን ምንም አይነት ስሜት ቢሰማችሁም እንደ እናንተ ጀግና የለም……እንደዚህም በሚያስጠላ ጊዜ ላይ ሆናቹ ፈገግታቹ ከፊታቹ ሳይለይ እየከፋቹ ሳቃችሁን አሳይታችሁናል……እየወደቃችሁም ለመነሳት ስትጥሩም ተመልክተናል……ስለ ወደፊት በምታስቡት በምታልሙት ሂወት እኛም ከእናንተ ተምረን… ተስፈኛ እንድንሆን አድርጋችሁናል…… በአሁን #ሰአት #በሳኡዲ #እስር #ቤት #ታስራቹ #ያሉቹ #እህት #ወንድሞቻችን #በእርግጥም #እናንተ #ጠንካሮች #ጀግኖች ናችሁ።………ወደ ፊትም አሁን ካላችሁበት እስር ተፈታችሁ የተሻለ ቦታ ላይ በተሻለ ሁኔታ እንደምናያቹ አንጠራጠርም በአሏህ ፍቃድ።……#አሏህ #ካላችሁበት ጭንቅ አውጥቶ ከሚወዷቹ እና የእናንተን መምጥት ከሚጠባበቁት ውድ ቤተሰቦቻቹ ይቀላቅላቹ ።………በደስታችሁም የምንደሰት ያድርገን። #በእርግጥም #ከችግር #ቡኋላ #ምቾት #አለ #ብሎንየለጌታችን አብሽሩ……ይሄም አልፎ አዲስ ተስፋ አዲስ ህልም ይመጣል።……የአሁኑም ጌዜ ታሪክ ይሆናል።……

#በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤት ታስረው እየተሰቃዮ ላሉ ወንድም እህቶቻችን በቻልነው ዱና እናድርግላቸው……አቅሙ ያለንም #ድምፅ እንሁናቸው።………ባረከሏሁ ፊኩም።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ለምንድነው ተስፋ የምትቆርጠው?……ያሰብከው ስላልተሳካ?አላማህን ስላላገኘክ?ወይስ ህልም ብለክ ያስቀመጥከው ቅዠት ስለሆነ?……ብዙ ሞክረህ ስላልተሳካ?……እና በዚህ ነው ተስፋ የቆረጥከው……አንተ ብቻ አይደለህምኮ……ሁሉም ሰው ይቺን ፈተና ቀምሷል……አልሞ ሳይሳካለት የቀረ……ፈልጎ ያላገኘ……ተመኝቶ ምኞቱ ያልሞላለት……አላማዬ ጋር ደረስኩ ሲል እንደገና ወደኋላ የተመለሰ……በዚ መስመር ማን ያላለፈ አለ ብለክ ነው ወዳጄ?……የውድቀትህ ብዛት 99% " ቢሆንምኳን መልፋትህን፣መሞከርህን እንዳታቆም…አልመክ የነበረውን እንዳትሰርዝ……ወደ አላማህ የሚያደርስህን ሊበር የተነሳውን ክንፍህን……ላይሆንኮ ይችላል፣ ላይሳክም ይችላል……ብለክ በፍርሀት እንዳትሰብረው……ተነስ ክነፍ…ከነ ህልሞችህ… …ከነ አላማዎችህ ብረር…ያንን 99%ኪሳራህን የምታስረሳህ አንዲት እድል ትገጥምህ እና የሂወትህ መለወጫ ቁልፍ 1ዷ ፐርሰንት ላይ ታገኛለህ……ይሄ የሚሆነው አንተ መብረርህን ስታቆም አይደለም……አልሆነልኝም ብለክ ቤትህ ስትውል አይደለም……ወድቆ በመነሳት ውስጥ ናት።……የዛኔ ሁሉም የለፋሀው ልፋት ይረሳና ብሎም ያለፈ ታሪክ የሚል ስያሜ ትሰጠዋለክ……እመነኝ ከአሏህ እገዛ ጋር አንተ ካልሰነፍክ ……አንተ ተስፋ ካልቆረጥክ የፈለክበት አላማ ላይ እንዳትደርስ የሚያደርግህ ነገር የለም።……ጥረታችን ሞክሮ ፣ታግሎ ለመተው ሳይሆን ከሙከራውም፣ከትግሉም፣ከመውደቁም ከሁሉም መሰናክሎች ቡኋላ ከነ አላማችን እንደገ በሁለት እግራችን ቀጥ ብሎ መቆም ነው።……<<በአሏህ እርዳታ ሁሉም ይሆናል>>

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

መሸሽ……መደበቅ!……አያምርህም? አዎ መደበቅ ልክ ህፅን ልጅ ወደ እናቱ ውሽቅ እንደሚለው……ሴት ልጅ የተበደለች ሲመስላት ወደ አባቷ እቅፍ እንደምትሮጠው……ሲበርድህ፣ሲሞቅህ፣ ሲደክምህ ፣ለማረፍ ወደ ቤትህ እንደምትሸሸው……በወንጀል ጭምልቅልቅ ብለክ ለመፅዳት በጌታህ ፊት ግንባርህን ለመድፋት ወደ ጌታህ እንደምትሮጠው……ይሄንን መሸሽ…ይሄንን መታቀፍ……የማይፈልገው ሰው ይኖር ይሆን።ሁላችንም ከለቅሶ፣ከስብራት፣ ከሀዘን፣ ብሎም ከደስታ,ቡሀላ መታቀፍን፣ ወደ ሆነ አካል መሸሽን የማይፈልግ ሰው ይኖር ይሆን?የለምኮ።ከጎንህ ያለውን ሰው መርዳት ከፈለክ በምንም ከማገዝህ በፊት……እቅፍህ ውስጥ ውሽቅ አድርገህ አብሽ ወንድሜ ያልፋል፣አብሽሪ እህቴ ያልፋል ከማለት የበለጠ እርዳታ የለም።እናማ ከጎናቹ ላለው ሰው መሸሸጊያ ሁኑ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

……መታጠብ አያምርህም?……ከቆሸሽክ ቡኋላ…ከድካምህ ቡኋላ……ሁሉም ነገራቶች ከተጠናቀቁ ቡኋላ…መፅዳት፣ መታጠብ አያምርህም?…ልክ ነው ሁሉም ሰው ይሄን ፅዳት ይፈልገዋል…ሰው ስራ ውሎ ሲለፋ የዋለበትን ልብስ፣ድካም፣ላቡን በመታጠብ ሊያስወግደው ይፈልጋል……ግን የጅስምህ፣የልብስህ፣ፅዳት እንደዚ የሚያሳስብህ ከሆነ፣ኖርማል እንቅልፍ እንድትተኛ የሚረዳህ ከሆነ……ትልቁን መቋሸሽ ……ትልቁን መታጠብ ለምን ረሳህ…የቱን?ነው ያልከኝ:ነገ ቀብርህ የተመቻቸ የሚያደርግልህ ነዋ……ሙሉ ቀን… አንዴ በምላስህ ሰዎችን ስታብጠለጥል የዋልክበትን……እጆችህ መጥፎ እንድትሰራ ያደረጉህን……እግሮችን ወደ ወንጀል የወሰዱህን……ወንጀል የተባሉትን እንድትመለከት ያደረጉህን አይኖችህን……እንዴት ከዚህ ሁላ መቆሸሽ ቡኋላ ማጠብ ማፅዳት አያምርህም……ምናልባት የቆሻሻው መጠን አልታየክ ይሆን?ልክ ነው ድሮምኮ ውስጣዊ ቆሻሻዎች ከጎዱ ቡኋላ ነው የሚያስታውቁት አሏህ ያዘነለት ሲቀር……እናም ወዳጄ ወደ አልጋህ ስትሄድ ከላይ የቆሸሸውን ብቻ ሳይሆን በወንጀል የተጨማለቀውን ማንነትህን ሳታፀዳ ጎንህን ለመኝታ አታሳርፈው……ማን ያውቃል የዛች ቀን ለሊት የዱኒያ ላይ የመጨረሻዋ ቆይታህ ልትሆንም ትችላለችኮ……እናማ ቆሽሻለው ፣አልፀዳም ፣የኔ ነገር አብቅቷል አትበል……አንተ ብቻ ከነ ቆሻሻህ ከነ ወንጀልህ ከነ ብዙ ጥፋቶችህ ወደ ጌታህ ተጎተት እመን ካንተ መጎተት በፈጠነ መልኩ ጌታህ ወደ አንተ ሲቀርብ ይታወቅሀል……የሰራከው ወንጀል ከተውበት እንዳያርቅህ……ተስፋ እንዳያስቆርጥህ……ከወንጀሉ የከበደው ይሄ ስለሆነ……እናም ወደ ጌታህ ሂድ…አብሽር ሁሉም የራሱ የሆነ መፅጃ አለው።#ወንጀልም #በተውበት ይፀዳል።

لَلَّهُ أَشَدُّ فَرَحًا بِتَوْبَةِ عَبْدِهِ حِينَ يَتُوبُ إِلَيْهِ،

Send as a message
Share on my page
Share in the group