Translation is not possible.

የትኛውን ትመርጣለክ #ታዋቂነትን ወይስ #አዋቂነት?………ራሳችንን እንጠይቅ……የትኛው ይሻለናል……በየትኛውስ መንገድ ላይ ነን……ይከብዳል አይደል ታዋቂዎች በበዙበት ዘመን አዋቂ ሆኖ መገኘት……በሰዎች ዘንድ ታውቀህ…ስለ አንተ በየ ቦታው ሲወራ መስማት……በብዙ ሰዎች ውዴታን ማግኘት……ስምህ በየ ቦታው ሲጠራ መስማት……ወሬዎችህ ቁም ነገር ያዘሉ ባይሆኑም በብዙ ሰዎች መደመጥህ እና ሲጨበጨብልህ… …ምን ይሰማሀል ብልህ ደስታ ነዋ ትላለክ በሙሉ እምነት……ግን የእውነት እነዚ ነገራቶች አንድ ሰውን ለማስደሰት በቂ ይሆናሉን……በፈጠረህ ጌታህ ዘንድ ታዋቂነት ሳይኖርህ እሱ በፈጠራቸው ፍጡራኖች መታወቅህ መደነቅህ ሊያስደስትህ ይገባልን?……ታዋቂነትን ሳይሆን አዋቂነትን ምረጥ… …የዛኔ እውነተኛ ደስታን ወደ ሂወትህ ታመጣለክ ከአለም ተደብቀህ……አለም ላይ ያሉ ሰዎች ሳያውቁህ አለምን የፈጠረው ጌታህ ዘንድ ታዋቂነትን ማፍራት አስበው እስኪ……ይሄ የሚሆነው ግን ከታዋቂነት አለም ስትወጣ ወደ አዋቂዎች አለም ስትገባ ነው……እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ… …ስንት አዋቂዎች እና ስንት ታዋቂዎችን እንደምናውቅ… …አዋቂነትን በራስህ ላይ ገምብተህ በጌታህ ዘንድ ታዋቂነትን አፍራ……።

Send as a message
Share on my page
Share in the group