Translation is not possible.

#ነፃነትን #ማጣት……ይሄን ትልቅ ፀጋ የሚረዳው ያጣው ሰው ብቻ ነው።…ሌሎቻችንማ ቢነገረንም ተረት፣ወይ ደግሞ ቀላል ነገር ነው ምን ያካብዳል ብለን የምንሳለቅም አንጠፋም……ግን በዱኒያ ላይ እየኖሩ ነፃነትን እንደማጣት ከባድ ነገር የለም……በተለይ ደግሞ ይሄን ፀጋ ያሳጡህ ሰዎች ከሆኑ፣ እንደዚሁም ካለ ምንም ጥፋት እና ወንጀል ሲሆን ህመሙ እጥፍ ይሆናል……አስቡት እስኪ አንድ ሰው… …ለብዙ ወራቶች ካለ ወንጀሉ ታስሮ… …በሂወቱ ብዙ ነገሮች ሲበላሹ ሲጠፉ ……ማሳለፍ ያለበት የደስታም ሆነ የሀዘን ጊዜዎች አራት መአዘን ክፍል ውስጥ ተዘግቶበት ሲያልፉት… የእውነት ይሄ ነገር የማያመው ሰው ይኖር?……በአሁን ሰአት #በሳኡዲ #እስር #ቤት #ካለምንም #ወንጀል ታስረው እየተሰቃዩ ያሉ ወንድም እና እህቶቻችን ብዙ ናቸው……ቤተሰቦቻቸውን አጥተው ሀዘናቸውን ያልተወጡ……በሀገራቸው ሰላም ማጣት ጠዋት ማታ የሚረበሹ……የቤተሰቦቻቸውን ደስታ አብረው ያልተካፈሉ……የእናቶቻችን ልጄ ዛሬ መጣ ነገ እያሉ በጉጉት አይናቸው መንከራተቱ……ስንት ህፃናቶች አባቴ አትመጣም……ቆየህኮ……እናቴ መቼ ነው የምትመጪው……እያሉ በጨቅላ አእምሯቸው የሚናፍቁ ስንት ህፃናት እንዳሉ ቤታችን ይቁጠረው።……አንድ ሰው እንኳን ታስሮ ይቅር እና ለአንድ ቀን እቤቱ ከልጆቹ ከቤተሰቦቹ ጋር ሙሉ ቀን ቤት ቢውል የሆነ ሰአት ላይ ደበረኝ ወደ ውጭ ወጣ ብዬ ልምጣ ሲል እንሰማለን………አስበነዋል ያውም በወዳጆቹ ተከቦ……ታዲያ ካለ ወንጀል ለብዙ ቀናቶች ፣ለብዙ ወራቶች፣ብሎም ለአመታት መታሰር……ይከብዳል የሚለው ቃል ይገልፀው ይሆን?…… በእርግጥም አሏህ ባሮቹን አይበድልም ምናልባትም አንዳንዴ በሆኑ ከባድ ጊዜያቶች ማለፍ ትልቅ ት/ት እንድንማር ያደርጋል…… ግን ያው የሰው ልጅ አይደለን የሆነ ቀን ይሰለቻል……የሆነ ቀን ይመራል……የሆነ ቀን ሰብርም ያልቃል……ከዛም አሏህ ያዘነለት ሲቀር ማማረር ይጀምራል………ተስፋም መቁረጥ ይጀምራል……በቃ ይሄ ነው የኔ መጨረሻ የሚል አስጠሊ ደውል ከአእምሮው ሲደወል ይሰማል……ፈልጎኮ አይደለም ያለበት ሁኔታ አስገድዶት እንጂ።………ምክር እና ቦክስ ለሰጪው አይደል የሚባለው……… እርግጥ ነው የሆነ ሰው ጫማ ላይ ካልቆምን ስሜቱን ሙሉ በሙሉ መረዳት ይከብዳል።……ግን ምንም አይነት ስሜት ቢሰማችሁም እንደ እናንተ ጀግና የለም……እንደዚህም በሚያስጠላ ጊዜ ላይ ሆናቹ ፈገግታቹ ከፊታቹ ሳይለይ እየከፋቹ ሳቃችሁን አሳይታችሁናል……እየወደቃችሁም ለመነሳት ስትጥሩም ተመልክተናል……ስለ ወደፊት በምታስቡት በምታልሙት ሂወት እኛም ከእናንተ ተምረን… ተስፈኛ እንድንሆን አድርጋችሁናል…… በአሁን #ሰአት #በሳኡዲ #እስር #ቤት #ታስራቹ #ያሉቹ #እህት #ወንድሞቻችን #በእርግጥም #እናንተ #ጠንካሮች #ጀግኖች ናችሁ።………ወደ ፊትም አሁን ካላችሁበት እስር ተፈታችሁ የተሻለ ቦታ ላይ በተሻለ ሁኔታ እንደምናያቹ አንጠራጠርም በአሏህ ፍቃድ።……#አሏህ #ካላችሁበት ጭንቅ አውጥቶ ከሚወዷቹ እና የእናንተን መምጥት ከሚጠባበቁት ውድ ቤተሰቦቻቹ ይቀላቅላቹ ።………በደስታችሁም የምንደሰት ያድርገን። #በእርግጥም #ከችግር #ቡኋላ #ምቾት #አለ #ብሎንየለጌታችን አብሽሩ……ይሄም አልፎ አዲስ ተስፋ አዲስ ህልም ይመጣል።……የአሁኑም ጌዜ ታሪክ ይሆናል።……

#በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤት ታስረው እየተሰቃዮ ላሉ ወንድም እህቶቻችን በቻልነው ዱና እናድርግላቸው……አቅሙ ያለንም #ድምፅ እንሁናቸው።………ባረከሏሁ ፊኩም።

Send as a message
Share on my page
Share in the group