Translation is not possible.

ለምንድነው ተስፋ የምትቆርጠው?……ያሰብከው ስላልተሳካ?አላማህን ስላላገኘክ?ወይስ ህልም ብለክ ያስቀመጥከው ቅዠት ስለሆነ?……ብዙ ሞክረህ ስላልተሳካ?……እና በዚህ ነው ተስፋ የቆረጥከው……አንተ ብቻ አይደለህምኮ……ሁሉም ሰው ይቺን ፈተና ቀምሷል……አልሞ ሳይሳካለት የቀረ……ፈልጎ ያላገኘ……ተመኝቶ ምኞቱ ያልሞላለት……አላማዬ ጋር ደረስኩ ሲል እንደገና ወደኋላ የተመለሰ……በዚ መስመር ማን ያላለፈ አለ ብለክ ነው ወዳጄ?……የውድቀትህ ብዛት 99% " ቢሆንምኳን መልፋትህን፣መሞከርህን እንዳታቆም…አልመክ የነበረውን እንዳትሰርዝ……ወደ አላማህ የሚያደርስህን ሊበር የተነሳውን ክንፍህን……ላይሆንኮ ይችላል፣ ላይሳክም ይችላል……ብለክ በፍርሀት እንዳትሰብረው……ተነስ ክነፍ…ከነ ህልሞችህ… …ከነ አላማዎችህ ብረር…ያንን 99%ኪሳራህን የምታስረሳህ አንዲት እድል ትገጥምህ እና የሂወትህ መለወጫ ቁልፍ 1ዷ ፐርሰንት ላይ ታገኛለህ……ይሄ የሚሆነው አንተ መብረርህን ስታቆም አይደለም……አልሆነልኝም ብለክ ቤትህ ስትውል አይደለም……ወድቆ በመነሳት ውስጥ ናት።……የዛኔ ሁሉም የለፋሀው ልፋት ይረሳና ብሎም ያለፈ ታሪክ የሚል ስያሜ ትሰጠዋለክ……እመነኝ ከአሏህ እገዛ ጋር አንተ ካልሰነፍክ ……አንተ ተስፋ ካልቆረጥክ የፈለክበት አላማ ላይ እንዳትደርስ የሚያደርግህ ነገር የለም።……ጥረታችን ሞክሮ ፣ታግሎ ለመተው ሳይሆን ከሙከራውም፣ከትግሉም፣ከመውደቁም ከሁሉም መሰናክሎች ቡኋላ ከነ አላማችን እንደገ በሁለት እግራችን ቀጥ ብሎ መቆም ነው።……<<በአሏህ እርዳታ ሁሉም ይሆናል>>

Send as a message
Share on my page
Share in the group