“የእናት ሀቅ.. መች ይለቅ! ”
(እውነተኛ)-ክፍል አንድ
ፀሀፊ✍፡አብዱልጀባር ፋሪስ
@finding_hubullah
ይህንን ታሪክ የምጽፍላችሁ በቅርቡ አያቴና እናቴ ካካፈሉኝ ነው። እውነተኛ እና እዚሁ ሀገራችን ውስጥ የተከሰተ ጉድ የሚያስብል ነው። በመጀመርያ ቻናሌን ሁሌም Unmute በማድረግና pin to top የሚለውን ተጭነው በቀላሉ መከታተል ይችላሉ። ቻናላችን ፍፁም ከCopy paste የፀዳ ነው። በዚህም አዳዲስ ፅሁፎችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ወሬ ሳላበዛ ታሪኩን ልቀጥል..
ታሪኩ በቅርቡ ከአንድ ወይም ሁለት አመት በፊት የተከሰተ ነው። እናት ከልጆቿ ጋር ኑሮዋን መስርታ መኖር ከጀመረች ሰነባብታለች። የመጀመርያ ትሁን ባይነገረኝም ታላቅ ልጇ ትዳር መስርታ መኖር ጀምራለች። ታድያ ታናሹ ወጣት ልጅሆዬ እናቱ ላይ እንደ ልቡ ይደነፋል። በዚህ ስራው እናት ከልብ ትፈራዋለች። ፍራቻዋ የመነጨው እሱ ለሷ ከሚያሳያት ትዕቢት እንጂ ሌላ አይደለም። ይገርማል የሰው ነገር! ሽንቱን በእጇ ጠርጋ ያሳደገችው እናቱን ግልምጫው አንሶ ሊመታት ይቃጣዋል። ምን ዓይነት ጭንቅላት ነው ይህን ሚቀበለው!!
እናም ከእለታት በአንዱ ቀን ልጅ ለእናቱ የሞባይል ስልኩን ቻርጅ እንድታስደርግለት አስጠንቅቆ ይሰጣታል። ወቸው ጉድ! እናቱን ይልካል.. እናት በትዕዛዙ መሰረት ገበያ ስትወጣ ስልኩን በጡቶቿ መሃል ቋጥራ ከምትይዘው ብር ጋር አያይዛ ታስቀምጠዋለች። ግብይቷን እንደጨረሰችም የልጇን ስልክ ቻርጅ ለማስደረግ ብትመልከት ከቦታው አጣችው። በድንጋጤ በአካባቢዋ ፈለገች።
ስትባክን ውላ ምንም ልታገኝ ስላልቻለች በፍራቻ ወደ ታላቅ ልጇ ቤት አመራች። 9 ወር በሆዳ ተሸክማው፣ 2 ዓመት ያጠባችውና ተንከባክባ ቆንጥጣ ያሳደገችው ልጁን ትፈራዋለች። የሰው ነገርኮ ጉድ ነው ወዳጆቼ! ግና ልጇ ቤት ደርሳ ችግሩን ነገረቻት። ስልኩ ካስቀመጠችበት መጥፋቱንና ልጅየውም እንደሚገላት አስረድታ አብራት እንድትሄድ ተማፀነቻት። ልጅ ምንም ሳይመስላት “ኧረ እማዬ ምንም አያደርግሽም። ይልቅ እመጣለሁ። ሂጂ” ብላ ከነፍርሃቷ አሰናበተቻት። እናት ሁሉ ነገር ጠቦባታል። ቤት ስትደርስ አንዳች ክፋ ነገር እንደሚገጥማት ጠርጥራለች። ከዚህ ስሜት ጋር ቤት ደረሰች። ቤት ስትደርስ አንዳች ክፋ ነገር እንደሚገጥማት ጠርጥራለች። ማይደረስ የለምና ከዚህ ስሜት ጋር ቤቷ ደረሰች። ልጅየው ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ሆኖ ቤት ተቀምጧል። እናት ከበሩ እንደገባች በጥያቄ ጀመራት። “ስልኬን ስጪኝ” ብሎ ከተቀመጠበት ወደሷ ተራመደ። አንዳች ነገር እንዳይደርስባት የሰጋችው እናት ተርበደበደች። ልጇ ከሚያደርስባት ክፋ ነገር ለማምለጥም እንዲህ ብላ የጠፋውን ስልክ እንደምትክሰው ለማሳመን ንግግር ጀመረች..
“ይሃውልህ የኔ ልጅ! እኛ ቤት ያለችውን ላም ከነ ጥጃዋ ወስደህ መሸጥ ትችላለህ። በምታገኘው ብርም የጠፋብህን ስልክ ትተካለህ። ስልክህ ካስቀመጥኩበት ወድቆ ጠፍቷል” አንዳች ነገር እንዳይደርስባት ትንቀጠቀጣለች። ልጅ ይሄንን ንግግር እየጠበቀ ይመስል እናቱን ዘልሎ አንነቃት። ጎሮሮዋን ይዞ ትንፋሽ እስኪያጥራት አንጠራራት።
ውይይ የሰው ጭካኔ!! እናትን አንቆ ለመግደል ይቃጣል። ሊያውም በተልካሻ ምክንያት። ምናለ እንኳን ስልኩን ልጁን እንኳ ብትደግልበት ባይነካት። እኮ! እናት ናት። እሷ ባትወልደው ከየት አባቱ ይገኝና ነው?!! የጠፋበትን ስልክ ዋጋ እጥፍ የሚሆን ንብረትም "ተክተህ ውስድ" ብላ እየተማፀነችው፤ በእንቢተኝነቱ ፀና። እንዳነቃትም እዛው ገደላት። አዎ! እናቱን አንቆ ገደለ።
ያ አላህ! ለተራ ስልክ ብሎ እሱንም ስልኩንም እንዲገኝ የመጀመርያ ሰበብ የነበረችውን እናቱን ገደለ። በድርጊቱ በጣም ነበር ያዘንኩት። እናቴ ይህንን ስትሰማ በጣም ነበር ያለቀሰችው። የሞተችውን ባታውቃትም፤ ሰው ሊያውም እናት በልጇ ታንቃ ስትሞት መስማት ይዘገንናል። ታላቅ እህት ሮጣ ወደ ቤቱ ስትደርስ እናት መሬት ላይ ተዘርራለች። አይኗን ማመን አልቻለችም። ይሄኔ ኡኡታዋን አቀለጠችው...
ልጁ ምን እንደገጠመው በክፍል ሁለት(በመጨረሻው)ይቀጥላል... እባካችሁ ሼር!! በናንተ ምክንያት ብዙ ሰው የእናቱን ክብር ሊያውቅና ሊረዳ ይችላል። ታሪኩ በጣም አሳዛኝ ነው። በዚህ አላበቃም የልጁ ጉዳይ።