UMMA TOKEN INVESTOR

ami_jj shared a
Translation is not possible.

ሥራ ለሌላችሁ፣ ማሻሻል ለምትፈልጉ፣ አዳዲስ ዕውቀቶችን ማግኘት ለምትሹ‼

======================================

(በዚህ ወቅትም ሥራ አጣሁ የሚል ሰው አለ? በትዕግስት ይነበብ!)

(OpenAI ChatGPT፣ MS Bing Chat፣ Alphabet - Google Bard፣ Anthropic - Claude፣ xAI Grok)

*

(ይህ ጽሑፍ በቀጥታ ዲናዊ ሳይሆን ዱንያዊ (አካዳሚክ ነክ) ነው።)

||

✍ ሁላችንም እንደምናውቀው በአሁኑ ወቅት የሥራ አጥ መጠን በዝቷል። የባለፈ አመቱና የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ውጤት ለብዙዎቻችን አነጋጋሪ ሆነ እንጂ አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲው ገብተው ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎችም እጣ ፈንታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ከሆኑ አመታት በፊት ሩቅ ሳንሄድ ያውም በኛ እድሜ አንድ ሰው ድግሪ ካለው ተለምኖ ነበር የሚቀጠረው። በወቅቱ ዲፕሎማ ያለው ሁሉ በሙያው ይቀጠር ነበር። ቀስ በቀስ ዲፕሎማ እየቀረ የዲግሪም ተፈላጊነት እየቀነሰ መጣ። አሁን አሁን ደግሞ ማስተር ያለው ጭምር ሥራ እያፈላለገ ነው። ፕሮፌሰርና ልምድ ያለው ማስተርስ ካልሆነ በስተቀር የቅጥር ነገር እንደምታዩት ነው።

ያን ያክል ሁሉ አመት ዩኒቨርስቲ ውስጥ በአሳይመንት፣ በፕሮጀክትና በፈተና ሲጠገረር የነበረ ተማሪ ገና ሊመረቅ ሱፉን ሲለብስ ደስታው ግማሽ ይሆናል። ሱፉን ካወለቀ በኋላ የት እንደሚቀጠር ሲያስበው፤ ዳግም ቤተሰቡ ጋር ሂዶ መቀመጥን ሲያስበው ይጨንቀዋል። «ሥራ አገኘህ?» የሚለው የዘመድ አዝማዱና ጓደኛው ጥያቄ ያማርረዋል።

የሚያሳዝነው ደግሞ እንደምንም ተብሎ ቅጥር ሲገኝ (ያንኑም ባልተማሩት ፊልድ)፤ በአለቃ መሳቀቁን ተውትና የደመወዙ አለመበርከት። የወር ደመወዝ ወጣ ብለህ ስትደሰት፤ የተበደርከውን ሳትከፍል ያልቃል። አሁንም ለቀጣዩ ወር ተስፋ እንዳደረግክ በዚህ ዑደት ህይዎት ከእጅ ወደ አፍ ሆና ትቀጥላለች። ጭራሽ ልጆችን የምታስተምር፣ የቤት ኪራይና መሰል የቤተሰብ ወጪ ካለብህ'ማ ተወው። ልጆቼ ከአለባበሳቸውና ከሚማሩበት ት/ቤት ጀምሮ ከሌሎች እንዳያንሱ ብለህ ትጥራለህ። ግን…

ስለ ችግሩ ይህቺን ታክል ካነሳሁ፤ ሌላውን ሁላችሁም በየቤታችሁ ስለምታውቁት ልተወው። መንግስት ቅጥር ማቆሙን ባለፈ አሳውቋል። 12ኛ ክፍል ላይ ደርሶ የማያልፈውን ተማሪ ብዛት እያዬን ነው። ተሳክቶላቸው ያለፉትም ከተመረቁ በኋላ የሚቀጠሩበት ቦታ አጥተው የሚሆኑትን እያዬን ነው። ይሄን ይሄን ስንመለከት፤ ከታች የሚማረው የአንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ከላይ እየሆነ ስላለው ነገር አልሰማ ይሆን እንደ? ያስብላል።

ወደ መፍትሄው ልምጣ፦ ከላይ ካሉት የቱንም ያክል ተማሪ አላለፈም ቢባል፣ የቱንም ያክል ተማሪ ሥራ አጣ ቢባል ጆሮ ሳትሰጡ ዝም ብላችሁ ተማሩ። ባይሆን ላይ ስትደርሱ ምን መማር እንዳለባችሁ እወቁ።

ወደ ጥቆማዬ ስሄድ፦ መጀመሪያ በአይቲ፣ በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ፣ በኢንፎርሜሽን ሳይንስ፣ በኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግና ከነዚህ ጋር ተያያዥ በሆኑ መስኮች የተመረቃችሁና በፊልዳችሁ ያልተቀጠራችሁ፣ የተቀጠራችሁበት ደመወዝ አርኪ ላልሆነላችሁ፣ ጭራሽ ሥራ ላልያዛችሁ… የምላችሁ ነገር ቢኖር፤ ሥራና በቂ ደመወዝ ያጣችሁት የፊልዱን ስም ብቻ ይዛችሁ ብቃቱን (ስኪሉን) ሳትይቁ ቀርታችሁ ስለሆነ ፈጥናችሁ በራሳችሁ ስኪሉን ያዙና ሥራ በቆንጆ ደመወዝ የት እንደሚገኝ ጠይቁኝ።

ከነዚህና ተያያዥ ፊልዶች ውጭ በሆነና በአሁኑ ወቅት ተፈላጊ ባልሆነ መስክ የተመረቃችሁና እየተማራችሁ ያላችሁ ደግሞ፤ ብትቀጠሩም ባትቀጠሩም ወደነዚህና ተያያዥ መስኮች ሺፍት አድርጉ።

①) መጀመሪያ ስኪሉን የት እንማር፣ እንደት እናግኝ፣ እንደት እንፍጠን?

*

√ ስኪሉ የሌላችሁ የነዚህ የቴክ ፊልዶች ተመራቂዎችና የሌሎች ፊልዶች ተመራቂዎች በአሁኑ ወቅት ለሥራ ብቁ የሚያደርጋችሁን መስክ መማር ከፈለጋችሁ፤ ወደ ኢንተርኔት ጎራ በሉ።

ግን ኢንተርኔት ላይ ብዙ ነገር ስላለ ወደየትኛው ለሚለው ደግሞ ሜንቶር ቢኖራችሁ ጥሩ ነው። አቅጣጫውን የሚያመላክታችሁ ጠቋሚ አካል ማለቴ ነው።

የቴክ ፊልዶቹ ባክግራውንድ ያላችሁ በራሳችሁ ብትማሩ ጥሩ ነው። ምክንያቱም ቲወሪ ፓርቱን ስለምታውቁት ሰርች እያደረጉ ማንበብና ፕራክቲስ በማድረግ ስኪሉን መያዝ ስለምትችሉ።

ሌሎቻችሁ ግን ትንሽ ቻሌንጅ እንዳያደርጋችሁ የምትማሩበት ተቋም ቢኖር ጥሩ ነው። ችግሩ እነዚህን መስኮች የሚያስተምር ተቋም የለም።

ግን እንግሊዝኛ ቋንቋ የምታውቁ ከሆነ የዚህ መስክ ዘርፎች ብዙ ቢሆኑም አንዱን መርጣችሁ ስኪሉን ብትቀስሙ በቀላሉ ትረዱታላችሁ። ደስ የሚለው ነገር ደግሞ በነዚህ መስኮች ኢንተርኔት ላይ በቂ ሪሶርስ አለ። በጣም አክቲቭ የሆነ ኮሚኒቲም አለ።

ግን እንደ ጀማሪ በቀላሉ ከምን ተነስታችሁ ወደ ምን መሄድ እንዳለባችሁ የሚጠቁሟችሁ ቡት ካምፖች ነበሩ። እንደ አለመታደል ሆኖ እኛ ሃገር ግን በብዛት የሉም። የማውቃቸውን ወደዚህ መስክ ዓይናችሁን ከምትገልጡበት መስክ አስጀምረው መሠረት ያሲዟችኋል የምላቸውን ሁለት ቡት ካምፖች ግን ሳልጠቁማችሁ አላልፍም።

1) Evangadi Tech ይሰኛል። አሜሪካ ነው ያሉት። ግን በተለይ እዛው አሜሪካ ያላችሁ ብትማሩባቸው ትጠቀማላችሁ። ለሌሎቻችሁ ደግሞ የነፃ ስኮላርሺፕ አላቸው። ግን ለ30 ሰው ስለሆነ በዛ ቢባል 10 ሰው ብቻ ቢደርሰው ነው። ሃገር ውስጥ ያላችሁት ግን የክፍያውን አትችሉትም ብዬ ነው። አጠቃላይ 1,800$ ዶላር ስለሆነ በኛ በብላክ ብታባዙት ወደ 200 ሺህ ብር ይሆንባችኋል። ድረ ገፃቸው፦ evangadi.com የቴሌግራም አካውንት ያላቸው አይመስለኝም።

2) እዚሁ ሃገር ውስጥ ያለ Mizan Institute of Technology (MiT) የሚባል ቡትካምፕ አለ። የነዚህ ክፍያ ሃገር ውስጥ ካላችሁት ጋር የሚሄድ ይመስለኛል። ኮርሱ ለ9 ወር ነው፤ ክፍያው በየወሩ 5 ሺህ ብር ነው። አቅሙ ያላችሁ ብትማሩ ብዙ አመት ሊፈጅባችሁ የሚችለውን ነገር በአጭር አቅጣጫ መያዝ ትችላላችሁ። ድረ ገፃቸው፦ mizantechinstitute.com

ተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም አካውንታቸው ላይ ታገኛላችሁ። t.me/MizanInstituteOfTechnology

አሁን ላይ በምዝገባ ላይ ስለሆኑ ሳይሞላባችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።

ሁለቱም ተቋማት የሚያስተምሩት ፉል ስታክ ዌብ ዴቨሎፕመንት ሲሆን ሁለቱም በኦንላይን ነው የሚያስተምሩት። ስለዚህ ከግል ሥራችሁ ጋር ሳይጋጭ ቦታ ሳይገድባችሁ እንደፈለጋችሁ መማር ትችላላችሁ።

የእንግሊዝኛ ዕውቀቱ ያላችሁና አቅጣጫውን የምታውቁ ግን፤ በራሳችሁ አንብቡና ቶሎ ወደ ሥራው ግቡ።

በነዚህ መስኮች ላይ ዕውቀቱ ኖሯችሁ በበፊቱ አድካሚ በሆነው መንገድ እየለፋችሁ ያላችሁ ካላችሁ ደግሞ፤ ምናልባት ካላወቃችሁ ከላይ መግቢያዬ ላይ የዘረዘርኳቸውን ቻትቦቶች ተጠቀሙ። እጅግ በጣም ሥራችሁን ያቃልሉላችኋል። በብዙ እጥፍ ፍጥነታችሁን ይጨምሩታል። ባይሆን የተሳሳተ ምላሽ እንዳላቸውም እወቁ። እያንዳንዳቸውም የራሳቸው ጠንካራና ደካማ ጎን ስላላቸው ማንን ለምን ጉዳይ መጠቀም እንዳለባችሁ ለዪ። ምንም ግንዛቤው በሌላችሁ ነገር ላይ አታዋሯቸው፤ የተሳሳተ ነገር ሲመልስሏችሁ ትክክል ነው ወይንስ አይደለም ብላችሁ የምትለዩበት ግንዛቤ ሊኖራችሁ ይገባል። ያንን መለየት ከቻላችሁ ላይፋችሁን ያቀሉታል።

ቻትጂፒቲ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ስልክ ቁጥር መክፈት ስለሚቻል አካውንቱ ክፈቱና ያለ ቪፒኤን ተጠቀሙበት። የቢንግን ቻት በራሳቸው በኢጅ ብሮውዘር ማግኘት ትችላላችሁ። የቻትጂፒቲን GPT-4 ሞደል ኢንተግሬት አድርገውት ነው። ከቢንግ ሰርች ኢንጂን ጋር ስለተያያዘም፤ ከቻትጂፒቲ በላይ ከ2021 ወዲህ ያሉ የቅርብ ጊዜ መረጃዎችንም ያካትታል። በተጨማሪም DALL·E 3 ጋር ስላላያያዙት ኢሜጅ ጀነሬት ማድረግ ይችላል።

የጎግል ባርድንም በቪፒኤን መጠቀም ትችላላችሁ። ከጎግል ሰርች ኢንጂን ጋር መያያዙም ዳታውን የተገደበ አያደርገውም። አዳዲስ መረጃዎችን ያካትታል

ክላውድንም እንደዛው፤ ግሮክ ግን ገና እየተጀመረ ስለሆነ ለጊዜው እኛ ሃገር የለም። ለወደፊቱ ግን ከትዊተር (ኤክስ) ጋር ስላጣመሩት በ2024 ከቶፕ ሦስቱ ቻትቦቶች መካከል ይመደባል ተብሎ ይጠበቃል። የኦፕን ኤአይን GPT-3&4 ሞደል ኢንተግሬት ያደረጉ በርካታ የኤይ ቱሎችንም ስለምታገኙ፤ ከፊሉ ለሪሰርች፣ ከፊሉ ለኮዲንግ… እንደየፍላጎታችሁ መጠቀም ትችላላችሁ። በርግጥ ራሱ ኦፕንኤአይም GPT-4 Turbo አዲስ ሞደል እስከ አፕሪል 2023 ድረስ ያሉ fixed dataset (curated and pre-processed) የያዘ አስተዋውቋል። ግን አመቱ ሲጨምር ይሄም ወደ ኋላ ይቀራል። ለዛም ነው እነ ባርድና ቢይንግ ቻት የራሳቸው ብሮውዘር ስላላቸው እንዲሁም የወደፊቱ ግሮክ ኤክስ ስላለው አዳዲስ መረጃ ማካተት የሚችሉበት መንገድ መኖሩ የሚጠቅማቸው።

②) ስኪሉን ከያዝን በኋላ የት እንሥራ?

ስኪሉን ከያዛችሁ በኋላ ሃገራችን አሁን ካለችበት እድገት አንፃር የናንተን ስኪልን የሚመጥን መቀጠሪያ ቦታ ላታገኙ ትችላላችሁ። ግን ደግሞ ስኪሉ በደንብ የገባው ሰው በርካታ ፕሮብለሞች ያሉት በእንደዚህ አይነቱ ባላደጉ ሃገራት ውስጥ ነውና ያንን ችግር የሚፈታ መፍትሄ በዕውቀትህ ታግዘህ ካመጣህ መንግስት ራሱና ጠካቶችህ ሳይቀሩ ይቀበሉሃል።

ይሄን ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ ከያዝከው ስኪል ጋር የሚሄድ ቆንጆ ፕሮፋይል ታዘጋጅና ወደ LinkedIn,Turing እና UpWork አካውንት ከፍተህ ጎራ በል። ያኔ ራስህን ለሥራ ክፍት መሆንህ አሳውቅ፤ ከአራቱም የዓለም አቅጣጫ በዶላርና በዩሮ የሚከፍልህ ይመጣልሃል። ያንን በኢትዮ ብር እየመነዘርክ ፈተና ብለህ መኖር ነው። ጭራሽ የተወሰኑ ልምዶችን ስታካብት ስትፈልግ Freelancer ሆነህ፣ ስትፈልግ ሪሞትሊ ተቀጥረህ ትሠራለህ። ቋሚ ሠራተኛ እንዳይቀጥሩ እንዲሠራላቸው የሚፈልጉት ነገር ጊዚያዊ ነገር የሚሆንባቸው አሉ። እነርሱ እንዲህ አይነት ሥራ የሚሠራልን ብለው የሥራ ማስታወቂያ ሲለቁ ከአንተ የሚጠበቀው አለሁ ማለት ብቻ ነው። የማገናኘቱን ሥራ ፕላትፎርሞቹ በራሳቸው ይሠሩልሃል።

እና ሥራ ማለት ይህ አይደል? ወይንስ ሥራ ማለት ለአንተ በአንድ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ መታዘዝ ነው? ያንኑም ላልረባ ደመወዝ! ያንኑም አለቃህ እንዳያባርርህ ሁሌ ተሳቀህ! ካባረረህ ደግሞ አስበው ድጋሜ ሌላ ቅጥር እስክታገኝ ድረስ የምትሆነውን! በተለይ ቤተሰብ አስተዳዳሪ ከሆንክ! ሌላ ሥራ እስኪገኝ ያጠራቀምኩትን ገንዘብ እጠቀማለሁ እንዳትል እንኳ፤ ያ የማይረባ ደመወዝ እንኳን የሚጠራቀም ሊተርፈው እዳህንም ጨርሶ አልከፈለ!

እኔ በእንደዚህ አይነት መልኩ በአጭር ጊዜ የተቀሩ በአካል ጭምር የማውቃቸው ወንድሞች አሉ። አውቃለሁ! ብዙዎቻችሁ መረጃው ስለሌላችሁ ነው። ይሄው ነግሪያችኋለሁ፤ ዛሬ ነገ ሳትሉ ስኪሉን ያዙና ጎራ በሉ። ስኪሉ ኖሯችሁ ይሄን የማታውቁ ካላችሁ ደግሞ ተጠቀሙበት። ግን አብዛሃኛው ስኪሉ ያለው ሰው እነዚህን ነገሮች ጠንቅቆ ያውቃል።

ሌላ ጊዜ ደግሞ በሌሎች ነጥቦች ጎራ ለማለት እሞክራለሁ። ጊዜ ካገኘሁ ደግሞ እኔም በነዚህ መስኮች ላይ አንዳንድ የነፃ ሰርቪሶችን ላካፍላችሁ እሞክራለሁ።

የበርካታ ወንድምና እህቶችን ህይዎት ሊቀይር ስለሚችል መልዕክቱን ከተጋራችሁት ለሌሎችም ሼር አድርጉት።

እስከዛው መዓኩም ሰላሙ-ል'ሏህ!

||

t.me/MuradTadesse

ummalife.com/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
ami_jj shared a
Translation is not possible.

በአንድ ወቅት በአውሮፓ አየር መንገድ የመጀመሪያ ደረጃ ክፍል

(Buisness Class) ውስጥ የተቀመጠ አንድ ሙስሊም ወጣት

ተሳፋሪ ነበር፡፡

በጉዞ ላይ ሳለ ከአውሮፕላኑ አስተናጋጆች አንዷ ለዚህ ሙስሊም

ወጣት የነፃ መጠጥ ይዛለት መጣች፡፡

መጠጡ የአልኮል መጠጥ ስለነበረ ሙስሊሙ ወጣት

አልተቀበለም፡፡

አስተናጋጇም ከመጠጫው ችግር ይሆን በሚል በሚስብና

በሚያምር ዲዛይን በተሰራ የመጠጥ ማቅረቢያ በድጋሚ ይዛለት

መጣች፡፡

ሙስሊሙ ወጣት የአልኮል መጠጥ እንደማይጠጣ በመናገር

አሁንም አልተቀበለም፡፡

አስተናጋጇ ጉዳዩ አሳሰባትና ለአውሮፕላኑ ማናጀር አሳወቀች፡፡

ማናጀሩ ይበልጥ ባሸበረቀ እቃ መጠጡን ይዞ መጣና ቀርቦ

ያናግረው ጀመር

“ወንድም በአገልግሎታችን ላይ ችግር አለ ወይ ሲል ጠየቀውና

ይህ ነፃና የጉዞ መክፈቻ መጠጥ ነው፤ እባክህ ጠጣ እንጂ” ሲል

ጠየቀው

ወጣቱ ሙስሊም “እኔ ሙስሊም ነኝ አልኮል መጠጥ አልጠጣም”

በማለት መለሰ፡፡

ማናጀሩ መጠጡን እንዲወስድ አሁንም መወትወቱን ቀጠለ. . .

ወጣቱ ሙስሊም “ማናጀር መጠጡን መጀመሪያ ለአውሮፕላን

አብራሪው ስጡት” አለ፡፡

ማናጀሩ “እንዴት አብራሪ እያበረረ አልኮል ይጠጣል? እሱኮ

ተልዕኮ ላይ ነው፡፡ አውሮፕላኑ እንዲከሰከስ ትፈልጋለህ ወይ ሲል

ጠየቀው ?” ወጣቱ ሙስሊም ረጋ ባለ አነጋገር “እኔ ሙስሊም ነኝ

ሁሌም ተልዕኮ ላይ ነኝ፡፡

ኢማኔን የመጠበቅ የሁልጊዜም ተልዕኮዬ ነው፡፡ ከጠጣሁ

የዚህንም የመጪውንም ሀገሬን ነው ማበላሸው” የሚል

የማያዳግም ምላሽ ሰጠው፡፡

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
ami_jj shared a
Translation is not possible.

«በአዛን ውስጥ ያሉ አስደናቂ ተአምራት»

አዛን የተዋቀረበት የቃላት ብዛት

« አላሁ አክበር ከሚለው መጀመሪያ እስከ ላ ኢላሀ ኢለሏህ» እስከሚለው መጨረሻ የቃላት ብዛት 50 ናቸው።

ቁርአን 6:160 እንደሚነግረን

በአንድ በጎ ተግባር አላህ የሰው ልጅ አስር ሀሰና ይሰጠዋል።

በአምስት አውቃት ሰላት ስንሰግድ የአምሳ ሶላት ያህል እንደ የምናገኘው የሀሰናት መጠን ጋር ቃላቶቹ ጋር እኩል ናቸው።

ሌላም ልቀጥል የአረበኛ ፊደላት ብዛታቸው 28 ናቸው ።

ከነዚህ ውስጥ አስገራሚው ነገር አዛን የሚባልባቸው ፊደላት ብዛት 17 ናቸው ።

ከታች ፊደላትን ቁጠሩ እስኪ

ا ل ه ك ب ر ش د ن م ح س و ي ع ص ف

እነዚህ 17 ፊደላት በቀን ውስጥ ከምንፈፅመው ረከአ ጋር እኩል ናቸው።

ሱብሀነላህ ጥራት ይገባህ ጌታየ!

ይቀጥላል ፣

አንድ አመት አስራ ሁለት ወር ነው ቁርአንን ይህን ያረጋግጥልናል አል_ተውባህ 36 ኛው አንቀፅ ላይ ይናገራል።

እዚህ ላይ ምን ያስገርማል ካላችሁ የአዛን ንግግሮች 12 አረፍተ ነገር ናቸው ።

الله اكبر الله اكبر1

الله اكبر الله اكبر2

اشهد ان لا اله الا الله3

اشهد ان لا اله الا الله 4

اشهد ان محمد رسول الله 5

اشهد ان محمد رسول الله 6

حى على الصلاة7

حى على الصلاة8

حى على الفلاح9

حى على الفلاح10

الله اكبرالله اكبر11

لا اله الا الله12

12 አረፈተ ነገር ብቻ መሆናቸው ሳይሆን የአዛን ድምፅ በነዚህ ወሮች ለደቂቃዎች ለሰከንድ ጥሪው በአለም አይቁያረጥም።

በቅርቡ ሳይንስ ይህን አረጋግጡዋል ።

በመሆኑም ምድራችን ዙሪያዋ 360° ሲሆን እያንዳንዱ ዲግሪ ማሐል የ4 ደቂቃ ልዩነት ቢኖርም አዛን ለአንድ ደቂቃ እንኳን ሳይቋረጥ መሰማቱ እጅግ አስገራሚ ነው።

የአንድ እለት 24 ሰዓት ማለት ምድር በምድር ወገብ 360 ድግሪ አንዴ የምትዞረበት ጊዜ ማለት ነዉ፡፡

በቅድሚያ ድግሪ ማለት የምድር ወራጅ መስመር እና ገዳሚ መስመር የሚገናኙበት ነጥብ ማለት ነዉ፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ የምድር ወራጅ መስመር እና ገዳሚ መስመር የሚገናኙበት 4 የተለዩ ነጥቦች አላቸዉ፡

በያአንዳንድ ዲግሪ ርቀት መካከል የ4 ደቂቃ ልዩነት አዛን ይደረጋል ይህም 360° × 4 ደቂቃ= 1440 ደቂቃ = 24 ሳአት ይሆናል ። ሱብሃነላህ

የመጨረሻው የአዛን ቃላት ላኢላሀ ኢለላህ የሚለው አረፍተ ነገርም የፊደሎቹ ብዛት 12 ነው።

ሙሐመድ ረሱሉላለህ የሚለውም የፊደል ብዛት እንዲሁ 12 ነው።

ሱብሀአነላህ

ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ" لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ "ከአሏህ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ማለት ነው፣

እነዚህ ቃላቶች الله ከሚለው ሶስት ፊደሎች ብቻ የተዋቀሩ ናቸው ።

لا إله إلا الله

«ማንኛውም እዚህ ዩንቨርስ ያለ አካል የራሱን ስም የተፃፈበትን ፊደላት በመጠቀም ስለማንነቱ መልሶ በነዚያው ፊደላት ለሌላው መግለፅ የሚችል ከአላህ በቀር ወይም ከዚህ ከላኢላኢለላህ ከሚለው ቃላት በቀር ሌላ ቃላት የለም ወደፊትም መፍጠር አይቻልም ።

እንቀጥል ሌላ ተአምር

አዛን አላህ አክበር ብሎ «አላህ»ብሎ በአላህ ስም ይጀምራል ላኢላሀኢለላህ ብሎ በ «አላህ» ስም አዛኑ ያልቃል ። አዛን ላይ የሚደጋገመሙ ብዙ ቃላቶች አላህ የሚለው ነው።

በብዛት የተደጋገሙ ቃላቶችችም እነዚህ የአላህ ስም የተገለፀባቸው ቃላቶች ናቸው ።

አዛን ውስጥ ብዛት ያለው ቃል አላህ የሚለው አስር አንድ ግዜ ተጠቅሱዋል።

11 ቁጥር በባህሪው እኩል መካፈል የሚችለው ለአንድ ብቻ እና ብቻ ነው ።

ሱብሀነላህ

በአዛን ውስጥ አሊፍ የሚለው ፊደል 47 ጊዜ ተጠቅሱዋል ።

ላም የሚለው ፊደል 45 ግዜ ይነሳል ።

ሀ የሚለው ፊደል 20 ግዜ ተጠቅሱዋል የነዚህ ፊደላት ድምር = 112 ፊደላት ናቸው።

አስገራሚው ነገር ይህ ቁጥር የአላህ ስም ከሱረቱል ፋቲሀ እስከ ሱረቱል ኢኽላስ ባለው ምዕራፍ መካከል ተገልፁዋል ግን በመጨረሻዎቹ ፈለቅ እና ናስ በሚባሉ ሁሉት ሱራዎች ላይ የአላህ ስም የለም ።

ሱብሀነ አላህ

አዛን በአመት ከ1800 ግዜ በላይ እንሰማለን ይህ ሁሉ ተአምር እንደያዘ አስተውለን ይሆን?

ምንም አማራጭ የለንም አልሀምዱሊላህ አላ ኒእመተል አዛን አልሀምዱሊላህ አላኒዕመተል ኢስላም ከማለት ውጭ አላህ ታላቅ ነው።

ኢስላምን ተረድተው ከሚያስረዱት አድርገን ያረብ ልቤን አታድረቅብኝ ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
ami_jj shared a
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
ami_jj shared a
Translation is not possible.

«በአዛን ውስጥ ያሉ አስደናቂ ተአምራት»

አዛን የተዋቀረበት የቃላት ብዛት

« አላሁ አክበር ከሚለው መጀመሪያ እስከ ላ ኢላሀ ኢለሏህ» እስከሚለው መጨረሻ የቃላት ብዛት 50 ናቸው።

ቁርአን 6:160 እንደሚነግረን

በአንድ በጎ ተግባር አላህ የሰው ልጅ አስር ሀሰና ይሰጠዋል።

በአምስት አውቃት ሰላት ስንሰግድ የአምሳ ሶላት ያህል እንደ የምናገኘው የሀሰናት መጠን ጋር ቃላቶቹ ጋር እኩል ናቸው።

ሌላም ልቀጥል የአረበኛ ፊደላት ብዛታቸው 28 ናቸው ።

ከነዚህ ውስጥ አስገራሚው ነገር አዛን የሚባልባቸው ፊደላት ብዛት 17 ናቸው ።

ከታች ፊደላትን ቁጠሩ እስኪ

ا ل ه ك ب ر ش د ن م ح س و ي ع ص ف

እነዚህ 17 ፊደላት በቀን ውስጥ ከምንፈፅመው ረከአ ጋር እኩል ናቸው።

ሱብሀነላህ ጥራት ይገባህ ጌታየ!

ይቀጥላል ፣

አንድ አመት አስራ ሁለት ወር ነው ቁርአንን ይህን ያረጋግጥልናል አል_ተውባህ 36 ኛው አንቀፅ ላይ ይናገራል።

እዚህ ላይ ምን ያስገርማል ካላችሁ የአዛን ንግግሮች 12 አረፍተ ነገር ናቸው ።

الله اكبر الله اكبر1

الله اكبر الله اكبر2

اشهد ان لا اله الا الله3

اشهد ان لا اله الا الله 4

اشهد ان محمد رسول الله 5

اشهد ان محمد رسول الله 6

حى على الصلاة7

حى على الصلاة8

حى على الفلاح9

حى على الفلاح10

الله اكبرالله اكبر11

لا اله الا الله12

12 አረፈተ ነገር ብቻ መሆናቸው ሳይሆን የአዛን ድምፅ በነዚህ ወሮች ለደቂቃዎች ለሰከንድ ጥሪው በአለም አይቁያረጥም።

በቅርቡ ሳይንስ ይህን አረጋግጡዋል ።

በመሆኑም ምድራችን ዙሪያዋ 360° ሲሆን እያንዳንዱ ዲግሪ ማሐል የ4 ደቂቃ ልዩነት ቢኖርም አዛን ለአንድ ደቂቃ እንኳን ሳይቋረጥ መሰማቱ እጅግ አስገራሚ ነው።

የአንድ እለት 24 ሰዓት ማለት ምድር በምድር ወገብ 360 ድግሪ አንዴ የምትዞረበት ጊዜ ማለት ነዉ፡፡

በቅድሚያ ድግሪ ማለት የምድር ወራጅ መስመር እና ገዳሚ መስመር የሚገናኙበት ነጥብ ማለት ነዉ፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ የምድር ወራጅ መስመር እና ገዳሚ መስመር የሚገናኙበት 4 የተለዩ ነጥቦች አላቸዉ፡

በያአንዳንድ ዲግሪ ርቀት መካከል የ4 ደቂቃ ልዩነት አዛን ይደረጋል ይህም 360° × 4 ደቂቃ= 1440 ደቂቃ = 24 ሳአት ይሆናል ። ሱብሃነላህ

የመጨረሻው የአዛን ቃላት ላኢላሀ ኢለላህ የሚለው አረፍተ ነገርም የፊደሎቹ ብዛት 12 ነው።

ሙሐመድ ረሱሉላለህ የሚለውም የፊደል ብዛት እንዲሁ 12 ነው።

ሱብሀአነላህ

ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ" لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ "ከአሏህ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ማለት ነው፣

እነዚህ ቃላቶች الله ከሚለው ሶስት ፊደሎች ብቻ የተዋቀሩ ናቸው ።

لا إله إلا الله

«ማንኛውም እዚህ ዩንቨርስ ያለ አካል የራሱን ስም የተፃፈበትን ፊደላት በመጠቀም ስለማንነቱ መልሶ በነዚያው ፊደላት ለሌላው መግለፅ የሚችል ከአላህ በቀር ወይም ከዚህ ከላኢላኢለላህ ከሚለው ቃላት በቀር ሌላ ቃላት የለም ወደፊትም መፍጠር አይቻልም ።

እንቀጥል ሌላ ተአምር

አዛን አላህ አክበር ብሎ «አላህ»ብሎ በአላህ ስም ይጀምራል ላኢላሀኢለላህ ብሎ በ «አላህ» ስም አዛኑ ያልቃል ። አዛን ላይ የሚደጋገመሙ ብዙ ቃላቶች አላህ የሚለው ነው።

በብዛት የተደጋገሙ ቃላቶችችም እነዚህ የአላህ ስም የተገለፀባቸው ቃላቶች ናቸው ።

አዛን ውስጥ ብዛት ያለው ቃል አላህ የሚለው አስር አንድ ግዜ ተጠቅሱዋል።

11 ቁጥር በባህሪው እኩል መካፈል የሚችለው ለአንድ ብቻ እና ብቻ ነው ።

ሱብሀነላህ

በአዛን ውስጥ አሊፍ የሚለው ፊደል 47 ጊዜ ተጠቅሱዋል ።

ላም የሚለው ፊደል 45 ግዜ ይነሳል ።

ሀ የሚለው ፊደል 20 ግዜ ተጠቅሱዋል የነዚህ ፊደላት ድምር = 112 ፊደላት ናቸው።

አስገራሚው ነገር ይህ ቁጥር የአላህ ስም ከሱረቱል ፋቲሀ እስከ ሱረቱል ኢኽላስ ባለው ምዕራፍ መካከል ተገልፁዋል ግን በመጨረሻዎቹ ፈለቅ እና ናስ በሚባሉ ሁሉት ሱራዎች ላይ የአላህ ስም የለም ።

ሱብሀነ አላህ

አዛን በአመት ከ1800 ግዜ በላይ እንሰማለን ይህ ሁሉ ተአምር እንደያዘ አስተውለን ይሆን?

ምንም አማራጭ የለንም አልሀምዱሊላህ አላ ኒእመተል አዛን አልሀምዱሊላህ አላኒዕመተል ኢስላም ከማለት ውጭ አላህ ታላቅ ነው።

ኢስላምን ተረድተው ከሚያስረዱት አድርገን ያረብ ልቤን አታድረቅብኝ ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group