Gender: | Male |
Date of birth: | 24-10-98 |
Сountry of residence: | Ethiopia |
University: | Education HARAMAYA |
Gender: | Male |
Date of birth: | 24-10-98 |
Сountry of residence: | Ethiopia |
University: | Education HARAMAYA |
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
#የነብዩሏህ_ኢሳ_የመርየመ_ልጅ #ዓለይሂ_ሰላም_ታሪክ
መርየምም፦"መልካምን ንግግር ተናገር(ጠይቅ)" አለችው።
ዩሱፍም፦"ቡቃያ ያለ ዘር ይበቅላልን?" አላት።
መርየምም፦"አዎን ይበቅላል" አለችው።
ዩሱፍም፦"አረንጓዴ ቅጠልስ ዝናብ ሳያገኝ መብቀል ይችላልን?" አላት።
መርየምም፦"አዎን መብቀል ይችላል" አለችው።
ዩሱፍም፦"ያለ ወንድ ሴት ልጅ ብቻ መውለድ ትችላለችን?" አላት።
መርየምም፦"አዎን ትችላለች" አለችው።
መርየምም ቀጠል አድርጋ፦" ዩሱፍ ሆይ! አላህ ቡቃየን የፈጠረ ቀን ያለ ዘር እንደፈጠረው አታውቅምን?!!
አላህ አረንጓዴ ቅጠልንስ ለመጀመሪያ ግዜ ሲፈጥረው ያለ ዝናብ እንደፈጠረው አታውቅምን?!!
ታዲያ መጀመሪያ ቅጠልን እና ቡቃያን ዘርም ሆነ ዝናብ ሳይኖር የፈጠረው ጌታ አሁን ያለ ዝናብ እና ያለ ዘር መፍጠር ይከብደዋል ትላለህን!!!?" አለችው።
ዩሱፍም፦"አይ እኔ እንደዛ ልል ፈልጌ አይደለም አላህ በፈለገው ነገር ላይ ሁሉ ቻይ ነው።አንድን ነገር ማድረግ በፈለገ ግዜም ሁን ይለዋል ይሆናልም" አላት።
መርየምም፦"አላህ ያለ ወንድም ሆነ ያለ ሴት አደምን አልፈጠረምን!!!? ያለ ሴትስ ሀዋን አልፈጠረምን!!!?" አለችው።
ዩሱፍም፦"አዎን ፈጥሯል" አላት። ከዚያም በልቡ ግን መናገር ያልፈለገችው ያአላህ ተአምር በሆዷ እንዳለ አወቀ።
መርየምም የመውለጃ ሰዐቷ በተቃረበ ግዜ የቤተ አምልኮውን ግቢ ለቃ ወጣች።ብቻወን በረሀ ላይ ሳለች ምጡ ጀመራት በጣምም አመማት አሁን ያለችበትን እንግልት እና ከመውለዷ በኋላ የሚከተላትን እንግልት ስታስብ፦"ዋ! ምኞቴ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ፡፡ ተረስቼም የቀረሁ በሆንኩ" ብላ ተመኘች።
በመጨረሻም ወደ አንድ የደረቀ የተምር ዛፍ ዘንድ በመጠጋት ልጇን ዒሳን ተገላገለች።ልክ ልጁን እንደተገላገለች ጂብሪል መጣ'ና፦" አትዘኝ፡፡ ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል፡፡
የዘምባባይቱንም ግንድ ወዳንቺ ወዝውዣት ባንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና፡፡ብይም፣ ጠጭም፣ ተደሰችም" አላት።
በልታ ስታበቃም ጂብሪል፦"ማንም ሰው ሊያናግርሽ ቢፈልግ እኔ ለአር ረህማን(ለአላህ) ማንንም ሰው ላላናግር ፆሚያለሁ በይ" አላት።
ኢብሊስም መርየም ልጇን ከተገላገለች በኋላ ወደ ኢስራኢላውያኑ ካህናት በመሄድ የመርየምን መውለድ ነገራቸው።ካህናቱም በጣም በመቆጣት ይዝቱባትም ጀመሩ።
ከዚያም መርየም ልጇን ተሸክማ ወደ ቤተ አምልኮው መጣች። ሁሉም ተሰብስቧል....ገና ፊትለፊታቸው ብቅ ስትል፦"የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም" አሏት።(የሀሩን እህት ያሏት ሳሊህ ሰዎችን በሀሩን ስለሚመስሉ ነው።)
እሷም ምንም መልስ ሳትሰጥ ህፃኑን እንዲያናግሩ ወደ ልጇ አመላከተቻቸው።ሁሉም በሁኔታዋ በመገረም ዚና ያደረገችው እንሷት እኛ ላይ ታሾፋለች እንዴ እያሉ ከተነጋገሩ በኋላ፦"በአንቀልባ ያለን ሕጻን እንዴት እናናግራለን" አሏት።
ያን ግዜ ህፃኑ ዒሳ ቀና
ይቀጥላል............🖊️
የነቢዩሏህ_ዒሳ_የመርየም_ልጅ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ
ክፍል1
የዛሬው እንግዳችን የአላህ ባሪያ እና ነቢይ የሆነው ዒሳ ኢብን መርየም ቢንት ዒምራን ኢብን ማሳን ኢብን ጋዚር ኢብን አልዩድ ኢብን ኢክተር ኢብን ሳዱቅ ኢብን ኢያዙዝ ኢብን አልያቂም
ኢብን አይቡድ ኢብን ዙርያቢል ኢብን ሻልታል ኢብን ዩሀይና ኢብን በርሻ ኢብን አሙን ኢብን
ሚሻ ኢብን ሂዝቃ ኢብን አሀዝ ኢብን መውሳም ኢብን አዝሪያ ኢብን ዩዋርም ኢብን ዩሻፊጥ ኢብን ኢሻ ኢብም አይባ ኢብን ረህባዓም ኢብን ሱለይማን ኢብን ዳዉድ......በመባል የዘር ሀረጉ ከዳዉድ ይመዘዛል።
ትናንት እና ከትናንት በስቲያው እንደዳሰስነው መርየም በህፃንነቷ ለቤተ አምልኮ የተሰጠች ልጅ ስትሆን ዉሎ አዳሯ እዚያው ቤተ አምልኮ ውስጥ ነው።ለወሳኝ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ከዚያ ግቢ አትወጣም ነበር።
ኢዚያ ቤተ አምልኮ ውስጥም ዩሱፍ የተባለ የአጎቷ ልጅ አለ።እሱም ውሎ አዳሩ እዚያው ስለሆነ ዝምድናቸውን ይበልጥ አጠናክሮታል።
ዘወትር ውሀ ለመቅዳትም ከቤተ አምልኮው አቅራቢያ ወዳለው ምንጭም አብረው ነበር የሚሄዱት።
ከእለታት አንድ ቀን መርየም እንስራዋን ይዛ ዩሱፍ ዘንድ በመሄድ፦"ምንጩ ጋ ሄደን ውሀ እንቅዳ" አለችው።
ዩሱፍም፦"እኔ እስከ ነገ የሚበቃኝ ውሀ አለኝ" አላት።
እሷም ትታው ብቻዋን ሄዳ ምንጩ ቦታ በመቅዳት ላይ ሳለች ጂብሪል በሰው ተመስሎ አጠገቧ ቆመ።
እሷም በጣም ደንግጣ፦"አላህን የምትፈራ እንደሆን ካንተ በአላህ እጠበቃለሁ።" አለችው።
እሱም፦"እኔ ንፁሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ የጌታሽ መልክተኛ ነኝ" አላት።
መርየምም፦"(በጋብቻ) ሰው ያልነካኝ ሆኜ አመንዝራም ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል!?" በማለት ጠየቀች።
ጂብሪልም፦"(ነገሩ) እንደዚህሽ ነው፡፡ ጌታሽ *እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው፡፡ ለሰዎችም ታምር ከእኛም ችሮታ ልናደርገው (ይህንን ሠራን) የተፈረደም ነገር ነው* ብሏል አላት።
ያን ግዜ እሷም ለጌታዋ ትእዛዝ እጅ ሰጠች።ጂብሪልም ጠጋ አለ'ና ደረቷ ላይ ልብሷን ከፈት አድርጎ ሩህ ነፋባት።መርየምም በእንስራዋ ውሀዋን ሞልታ ወደ ቤተ አምልኮው ተመልሳ ሄደች።
ግዜ ግዜን እየተካ የመርየም ፅንስ ሆዷን እየገፋ መጣ።ይሄን የተመለከተውም የአጎቷ ልጅ ዩሱፍ ሁኔታው በጣም ግራ አጋባው።
አርግዛ ነው እንዳይል ከቤተ አምልኮ ከሱ ውጭ ከማንም ወጥታም ታይታም አጣውቅም።ምንም አልተፈጠረም እንዳይል የእርግዝና ምልክቶች እንዳለ ይታዩባታል።
በመጨረሻም ይሄን የሚያጣራበት አንድ መፍትሄ አገኘ'ና ሊያናግራት ወስኖ እርሷ ዘንድ በመሄድ፦"መርየም የሆነ ነገር በውስጤ ይመላለሳል።እደብቅሻለሁ እያልኩ ግን አልቻልኩም በቃ ልጠይቅሽ" አላት።
#ይቀጥላል.............
📜 አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱ ላሂ ወበረካትሁ
📌 ነብዩላህ ኑህ ዐለይሂ ሰላም
🔮 ክፍል 2
📍 ኑህም ለስለስ ባለ አንደበት፦
"ዛሬ በኛ ላይ ብትሳለቁብን ነገ እኛም በእናንተ ላይ እንሳለቅባችኋለን" ይላቸው ነበር።
👉 የመርከቧ ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ አላህ ኑህን ያመኑበትን ሁሉ መርከቧ ላይ
እንዲጭን እና ከእያንዳንዱ እንስሳት እና የዱር አራዊት አንድ ወንድ አንድ ሴት
በመርከቧ እንዲጭን አዘዘ።
👉 የምዕመናኑ ቁጥር 80 ብቻ ነበር። ለኑህም ዐለይሂ ሰላም ሁለት ሚስቶች ነበሩት።
አንደኛዋ ሙስሊም ስትሆን
ሁለተኛዋ አመፀኛ ካፊር ናት።
👉 እሱም ሙስሊሟን መርከብ ላይ ጫናት።
👉 መርከቧ ውስጥ ሁሉም ቦታውን ከያዘ በኋላ ፀሀይ ብርሀኗን ተነጠቀች ምድር በአስፈሪ ፅልመት ተዋጠች።
👉 ሰማይም ዶፍ ዝናብን ማንቧቧት ጀመረ...
👉 በከርሰ ምድርም ታምቆ የነበረው ውሀ ምድሪቱን እየሰነጠቀ ለጉድ መፍለቅ ጀመረ።
👉 ከሰማይ የወረደው ውሀ እና ከምድር የወጣው ውሀ ሲገናኝ ምድር ከአቅሟ
በላይ መጥለቅለቅ ጀመረች።
👉 ያን ግዜ መርከቧ ቀስ እያለች መንሳፈፍ ጀመረች።
👉 ውሀው በየሰዐቱ እየጨመረ ነው አጋጣሚ ኑህ ዐለይሂ ሰላም ሁኔታውን ለማጣራት ወደ ምድር ሲመለከቱ
የአብራካቸው ክፋይ የሆነው ልጃቸው አንዴ ሲወድቅ አንዴ ሲነሳ ውሀው ሲያንከራትተው ተመለከቱት።
👉 እንዲህም ሲሉ ተጣሩ፦ "ልጄ ና ከኛ ጋር ተሳፈር ከካሀዲያን ህዝብም አትሁን"
👉 ልጁ ግን በትዕቢት የተሞላ ነው'ና፦
"ከውሀው ይጠብቀኝ ዘንድ ወደ ተራራ
እወጣለሁ" ብሎ መለሰላቸው።
👉 እሳቸውም፦ "ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም። (እርሱ) ያዘነለት
ካልሆነ በቀር" ብለው ንግግራቸውን ሳይጨርሱ እንደ ትልቅ ተራራ ያለ ማዕበል መጣና ልጁን ጠራርጎ ወሰደው።
👉 ኑህም ልጄ እያሉ ወደ አላህ ሲጮሁ
አላህም፦" ኑሕ ሆይ‼ እርሱ ከቤተሰብህ
አይደለም፤ እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር
አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ" አለው።
👉ውሀውም ምድርን ለ40 ቀናት ያህል ካጥለቀለቀ በኋላ ምንም አይነት ነፍስ
ያለው ነገር ከምድረ ገፅ ጠፋ።
👉 ያን ግዜ አላህም ምድርን፦ "ምድር ሆይ‼ ውሃሽን ዋጪ፡፡ ሰማይም ሆይ
(ዝናብሽን) ያዢ፡፡" ብሎ ምድርን ከመጥለቅለቅ አስቆመ።
👉 ምድር ትንሽ ጠፈፍ ማለት ስትጀመር ኑህን እና ተከታዮቹን የተሸከመችው
መርከብ በሰላም ጁዲይ በተባለ ተራራ ላይ አረፈች።
👉 አላህም የተቀረውን ውሀ ወደ ውቅያኖስ እንዲፈስ አደረገው።
👉 ያን ግዜ ኑህ እና ተከታዮቹ ከመርከቢቷ ወርደው የያዟቸውንም እንስሳት አውርደው ለቀቋቸው።
👉 በምድርም እንደ አዲስ ግንባታ ጀመሩ። የተለያዩ ዛፎችንና አዝርዕትን መትከልም ጀመሩ።
👉 ምእመናኑ'ም ምድር ላይም በመበታተን የተለያዩ ከተማዎችን በመመስረት ብዙ ልጆችን ወልደው ምድርን እንደ አዲስ መሙላት ጀመሩ።
በመጨረሻም አላህ ኑህን ዐ ሰ፦
"ኑህ ሆይ‼ እኔ ፍጥረታትን የፈጠርኩት
እንዲገዙኝ ነው። እኔ ያዘዝኳቸውንም እንዲታዘዙኝ ነው።
ነገር ግን አመፁኝ፤ ከኔ ሌላ የሆነንም አካል ጌታ አድርገው ያዙ።
ያን ግዜ ቁጣዬም እነሱ ላይ ተፈፃሚ
ሆነ። በውሀም አጥለቀለቅኳቸው" ብሎ ወህይ አወረደለት።
👉 አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ የኑህን ዐለይሂ ሰላም ህዝብ በውሀ ካጥለቀለቀ በኋላ
በምድር ላይ ከ ኑህ ዐለይሂ ሰላም ጋር አብረው ከዳኑት ምዕመናን ውጭ ምንም
አይነት የሰው ልጅ አልቀረም ነበር።
👉 ይህ በእንዲህ እንዳለ ኑህ ዐለይሂ ሰላም እና በዘመኑ የነበሩት ሰዎች ከሞቱ በኋላ አንዱ
አንዱን ሲተካ ምድር ዳግም በሰዎች ትሞላ ጀመር።
👉 ያ ዘመን ካለፈ በኋላ የነበሩ ህዝቦችም ማንም አምልኮ ከሚያውቀው በላይ ጣኦትን ማምለክ ተያያዙት።
👉 የህዝቡ መለያ ስማቸውም (ዓድ) ይባላል።
👉 በመጀመርያ የዓድን ህዝቦች ላስተዋውቃችሁ...
👉 የዓድ ህዝቦች በዐረቢያ ምድር በየመን ግዛት "አህቃፍ" በሚባል አካባቢ
"ኢረም" በተባለች ከተማ የሚኖሩ በጣም ትላልቅ ቁመና ያላቸው ህዝቦች ሲሆኑ፤
👉 አላህ ስፍር ቁጥር የሌለውን የፀጋ አይነት ያትረፈረፈባቸው ህዝቦች ናቸው።
👉 ከፀጋዎቻቸውም የሚኖሩበት ምድር በጣም ለቡቃያ አመቺ እና ለም አፈር ያለበት አካባቢ ነው።
👉 ሰውነታቸውም በጣም ግዙፎች እና ረጃጅሞችም ነበሩ።
👉 ከሰውነታቸው መግዘፍ የተነሳ አንድን የቴምር ዘንባባ በሁለት ጣታቸው ይነቅሉ
ነበር።
(የተምር ዛፎች ምን ያህል ግዙፍ እንደሆኑ ዐረብ ሀገር ያላችሁ ውዶች
ታውቁታላችሁ)
👉 ነገር ግን አላህ ለዋለላቸው እንዲህ አይነት ኒዕማ ምላሻቸው ምስጋና ሳይሆን
ድንበር ያለፈ አመፅ እና መኩራራት ነበር።
👉 የኑህ ህዝቦች ያደርጉት የነበረውን የጣኦት አምልኮ አሟሙቀው ጀመሩት።
👉 ያም አላንስ ብሏቸው ምድርን በተለያዩ የወንጀል አይነቶች ይሞሏትም ጀመር።
👉 ነገር ግን ለቅጣት የማይቸኩለው አላህ በእዝነት አዘል ጥበቡ ከመጥፎ
ከልክሎ ወደ መልካም የሚመራቸውን (ሁድ) የተባለውን መልዕክተኛ
ከመሀከላቸው ላከላቸው።
📜 አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱ ላሂ ወበረካትሁ
📌 ነብዩላህ ኑህ ዐለይሂ ሰላም
📍 አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ከነዚያ ህዝቦች ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራቸው ዘንድ ኑህ የተባሉ መልዕክተኛን አስነሳ።
👉 ኑህም ህዝባቸውን ሰበሰቡና፦
"እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ። አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም። በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ (ክፍያ) አልጠይቃችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም" ብለው ህዝባቸውን ተጣሩ።
👉 ይህን ሲሰሙ አስተባበሉት። ምንም ሊያምኑለት አልቻሉም። እንዲያውም
ያፌዙበት ጀመር።
👉 ኑህ ዐለይሂ ሰላም ያለመሰላቸት ዘወትር ጥሪም ያደርግላቸውም ነበር።
👉 የህዝቦቹ ማፊዝ እና ማላገጥ በበዛበትም ግዜ፦ "ወገኖቼ ሆይ‼ ምንም መሳሳት የለብኝም፡፡ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልእክተኛ ነኝ፡፡ የጌታዬን መልዕክቶች አደርስላችኋለሁ፡፡ ለእናንተም እመክራችኋለሁ፡፡ ከአላህም
በኩል የማታውቁትን አውቃለሁ።" አላቸው።
👉 የኑህን ዐለይሂ ሰላም ንግግር በሰሙ ጊዜ በጣም በመገረም፦ "አንተ ኑህ‼ አንተ እኮ እንደኛው ሰው ነህ እንዴት ነው መልዕክተኛ ነኝ ምትለው?
በዛ ላይ ጥቂት ተከታዮች አሉህ። ሁሉም ግን ድሀ እና ኮሳሳ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ናቸው።
ደግሞም በሀብትም ሆነ በክብር ከኛ ጋር አትመጣጠኑም" ብለውም አስተባበሉ።
👉 ያም አላንስ ብሏቸው እርስ በርስ በሚፈፅሙት የሀውልት አምልኮ እንዲፀኑ ይመካከሩም ጀመር።
👉 ኑህም የህዝቡ ሁኔታ ተስፋ ሲያስቆርጠው በመለማመጥ መልኩ፦ አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከእናንተው (ጎሳ) በኾነ ሰው ላይ
እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ቢመጣላችሁ ትደነቃላችሁን" እያለ
ቢያግባባቸውም ክህደታቸው ይበልጥ እየጨመረ እንጂ ምንም አይቀንስም
ነበር።
👉 ምንም እንኳን ኑህ ዐለይሂ ሰላም የህዝቡ ነገር ተስፋ ቢያስቆርጣቸውም ተልዕኮዋቸውን በሚገባ በማድረስ ላይ ቀጥለዋል።
👉 እናም ሁሌ ቀን እና ማታ ህዝባቸውን ስለ አላህ ሲያስታውሷቸው ህዝባቸው
የነቢያቸውን ዳዕዋ ከመስማት ጆሮዋቸውን መያዝ ጀመሩ።
👉 ጆሮዋቸውን ይዘው መስማት እንቢ ሲሉ ኑህ ዐለይሂ ሰላም በምልክት ይነግሯቸው ነበር።
👉 ኑህም በምልክት ሲነግሯቸው ህዝቡ ግን አይኖቻቸውን በልብሶቻቸው ይሸፍኑ ነበር።
👉 ምንም ተስፋ አልቆርጥ ብሎ መቆም መቀመጥ ሲከለክላቸው፦ "ድሆች እና
ዝቅተኛ ሰዎች ያንተ ተከታይ ሆነው ሳለ እኛም ከነሱ ጋር እንድንከተልህ ትሻለህን‼
👉 ይልቁንስ እኛ እንድንከተልህ ከፈለግክ እነዚህን ተራ ሰዎች ከጎንህ አርቃቸው።" አሉት።
👉 ኑህ'ም ዐለይሂ ሰላም፦ "እነሱ የሚሰሩትን አላህ ነው ሚያውቀው። እኔ ላባርራቸው አልችልም። እንዴትስ ረዳቶቼን፣ አክባሪዎቼን አባርር ትሉኛላችሁ??? ቆይ ባባርራቸውስ እኔን
ከአላህ ማን ያተርፈኛል??? አታስተውሉምን???" ብሎ ጠንከር አለባቸው።
👉 ኑህ ዐለይሂ ሰላም መልካም ነብይ ነበሩ። ሀብታም፣ ድሀ ደከማ፣ ጠንካራ፣ ትልቅ፣ ትንሽ ስይሉ ለሁሉም በክብር የተላኩትን ዳዕዋ አደረሱ።
👉 ምንም እንኳም ለ950 አመታት ዳዕዋ ቢያደርጉም ዳዕዋቸውን ከ80 በላይ ሰው ሊቀበላቸው ባለመቻሉ ሁኔታው ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ለጌታቸው ስሞታ ለማቅረብ ተገደዱ።
👉 እንዲህም ሲሉ ለአላህ ነገሩት፦ "ጌታዬ‼ ህዝቦቼ እኮ አስተባበሉኝ። በእኔና በእነርሱም መካከል (ተገቢ) ፍርድን ፍረድ፡፡ አድነኝም፡፡ ከእኔ ጋር ያሉትንም ምእምናን(አድን)፡፡"
👉 ከዚህ በኋላ የኑህ ዐለይሂ ሰላም የዳዕዋ ጥሪ ዛቻ አዘል መሆን ጀመረ።
👉 እነሱም ለኑህ ዐለይሂ ሰላም ዛቻ ግድ አልነበራቸውም ይልቁኑ፦ "የምትዝትብንን አምጣ እውነተኛ ከሆንክ" እያሉ ሲሳለቁበትም ጀመር።
👉 ኑህም፦ "ይህ እኮ በኔ ቁጥጥር ውስጥ አይደለም። ያ የአላህ ስልጣን ነው" ይላቸዋል።
👉 አሁን ነገሩ መቋጫው ተቃርቧል።
👉 አላህም አስፈሪ ወህይ እንዲህ ሲል ወደ ኑህ አወረደ፦" ከሕዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር (ወደፊት ከአሁን በኋላ) አያምኑም፡፡ ይሠሩትም በነበሩት (ክህደት) አትዘን"
👉 በመቀጠልም አላህ ኑህን ዐለይሂ ሰላም የዘንባባ ችግኝ እንዲተክል አዘዘው።
👉 ያች ዛፍ ለማፍራት ስትበቃ የአላህ ቅጣትም በነዚያ ህዝቦች ላይ እንደሚፈፀም ቃል ገባለት።
👉 የአላህ የተለምዶ እዝነቱ የታወቀ ነው።
👉 ትልልቅ ሰዎች ባጠፉት ህፃናትን
አይቀጣም'ና ህፃናት የቅጣቱ ሰለባ እንዳይሆኑ ቅጣቱ ከመፈፀሙ ከ40
አመታት በፊት የሴቶቹ ማህፀን ፅንስ መሸከም እንዳይችል አደረገው።
👉 ለ40 አመት ያህል ምንም አይነት ህፃን ሳይወለድ ቀረ።
👉 በዚያ ዘመም ኑህ ዐለይሂ ሰላም የታዘዘውን ዛፍ እንክብካቤ ሲያደርግ
👉 እነዚህ አመፀኛ ህዝቦች እንዲህ በማለት ይሳለቁበት ነበር፦ "አንተ ኑህ ነቢይ ነኝ እያልክ ዘራፍ ብለህ አላዋጣ ሲልህ ወደ ግብርና ገባህ እንዴ‼"
👉 ድንጋይም ይወረውሩባቸው ነበር።
👉 የተተከለው ዛፍ 50 አመት ሲሞላው አላህም ለኑህ ዐለይሂ ሰላም ወህይ በማውረድ ዛፎችን እንዲቆጣቸው አዘዛቸው።
👉 ኑህም ዐለይሂ ሰላም ዛፎቹን ከቆረጠ በኋላ አላህም ትልቅ መርከብ እንዲሰራ
አዘዘው።
👉 ጂብሪልም መርከብ እንዴት እንደሚሰራ ሊያሳየው ከሰባት ሰማያት
ወረደ።
👉 አላህም እንዲህ ሲል ወህይ አወረደ፦
"የመርከቧ ርዝመት 1200 ክንድ
የጎን ስፋት 800 ክንድ
ከፍታው ደግሞ 80 ክንድ የሆነችን መርከብ ስራ"
👉 በተንጣለለ አሸዋማ እና በረሀማ ቦታ ላይ ኑህ መርከቧን መስራት ጀመሩ።
👉 ህዝቦቹም ከአጠገቡ ሲያልፉ፦
"አንተ ኑህ ከነብይነት አናፂነት ይሻላል
ብለህ ነው?" እያሉ ያፌዙበታል።
👉 ከፊሎቹ ደግሞ፦ "አንተ ኑህ መርከብ እኮ ለባህር ነው የሚሰራው አንተ እልም
ያለ በረሀ ላይ ትሰራለህ እንዴ‼" ይሏቸዋል።
👉 ኑህም ለስለስ ባለ አንደበት፦ ኢንሻ አላህ #የነብዩሏህ_ኑህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ
...ይ
.......ቀ
...........ጥ
...............ላ
....................ል
Are you sure you want to leave the group with your friends?
Are you sure, you want to remove this member from your family?
You have poked Umma1698156820
New member has been successfully added to your family list!
Are you sure, you want to delete this photo?
Are you sure you want to delete the user and their posts, photos, videos, etc.?
Выберите тип блокировки:
Выберите параметры блокировки:
Comment has been successfully reported
The post has been successfully added to your timeline!
You have reached your limit of 100000 friends!
File size error: The file exceeds the allowed limit (9 GB) and can not be uploaded.
Your video is being processed,
We’ll let you know when it's ready to view.
It's impossible to upload the file: This file type is not supported.
We have detected adult content on the uploaded image,
therefore we have declined the uploading process.
To get a verification (tick) on the Islamic social network Umma Life, you must meet at least one of the following criteria: 1. Social network activity: Participants seeking verification must be active users of the social network. At least one useful message must be posted per day, and the message topics can be non-religious. 2. A well-known Islamic blogger or Muslim: If you are a well-known Islamic blogger or Muslim, even if your activities are not related to religious topics on the Internet, you can also apply for verification. 3. A large number of subscribers or active religious pages: If you have a lot of subscribers on social networks or you actively manage useful religious pages, this can also be a basis for getting verified. If you meet at least one of these criteria, submit an application for verification on the Islamic social network Umma Life via private message https://ummalife.com/ummalife and your account will be reviewed by the social network administration.