Translation is not possible.

የነቢዩሏህ_ዒሳ_የመርየም_ልጅ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ

                     ክፍል1

     የዛሬው እንግዳችን የአላህ ባሪያ እና ነቢይ የሆነው ዒሳ ኢብን መርየም ቢንት ዒምራን ኢብን ማሳን ኢብን ጋዚር ኢብን አልዩድ ኢብን ኢክተር ኢብን ሳዱቅ ኢብን ኢያዙዝ ኢብን አልያቂም

ኢብን አይቡድ ኢብን ዙርያቢል ኢብን ሻልታል ኢብን ዩሀይና ኢብን በርሻ ኢብን አሙን ኢብን

ሚሻ ኢብን ሂዝቃ ኢብን አሀዝ ኢብን መውሳም ኢብን አዝሪያ ኢብን ዩዋርም ኢብን ዩሻፊጥ ኢብን ኢሻ ኢብም አይባ ኢብን ረህባዓም ኢብን ሱለይማን ኢብን ዳዉድ......በመባል የዘር ሀረጉ ከዳዉድ ይመዘዛል።

ትናንት እና ከትናንት በስቲያው እንደዳሰስነው መርየም በህፃንነቷ ለቤተ አምልኮ የተሰጠች ልጅ ስትሆን ዉሎ አዳሯ እዚያው ቤተ አምልኮ ውስጥ ነው።ለወሳኝ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ከዚያ ግቢ አትወጣም ነበር።

ኢዚያ ቤተ አምልኮ ውስጥም ዩሱፍ የተባለ የአጎቷ ልጅ አለ።እሱም ውሎ አዳሩ እዚያው ስለሆነ ዝምድናቸውን ይበልጥ አጠናክሮታል።

ዘወትር ውሀ ለመቅዳትም ከቤተ አምልኮው አቅራቢያ ወዳለው ምንጭም አብረው ነበር የሚሄዱት።

ከእለታት አንድ ቀን መርየም እንስራዋን ይዛ ዩሱፍ ዘንድ በመሄድ፦"ምንጩ ጋ ሄደን ውሀ እንቅዳ" አለችው።

ዩሱፍም፦"እኔ እስከ ነገ የሚበቃኝ ውሀ አለኝ" አላት።

እሷም ትታው ብቻዋን ሄዳ ምንጩ ቦታ በመቅዳት ላይ ሳለች ጂብሪል በሰው ተመስሎ አጠገቧ ቆመ።

እሷም በጣም ደንግጣ፦"አላህን የምትፈራ እንደሆን ካንተ በአላህ እጠበቃለሁ።" አለችው።

እሱም፦"እኔ ንፁሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ የጌታሽ መልክተኛ ነኝ" አላት።

መርየምም፦"(በጋብቻ) ሰው ያልነካኝ ሆኜ አመንዝራም ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል!?" በማለት ጠየቀች።

ጂብሪልም፦"(ነገሩ) እንደዚህሽ ነው፡፡ ጌታሽ *እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው፡፡ ለሰዎችም ታምር ከእኛም ችሮታ ልናደርገው (ይህንን ሠራን) የተፈረደም ነገር ነው* ብሏል አላት።

ያን ግዜ እሷም ለጌታዋ ትእዛዝ እጅ ሰጠች።ጂብሪልም ጠጋ አለ'ና ደረቷ ላይ ልብሷን ከፈት አድርጎ ሩህ ነፋባት።መርየምም በእንስራዋ ውሀዋን ሞልታ ወደ ቤተ አምልኮው ተመልሳ ሄደች።

ግዜ ግዜን እየተካ የመርየም ፅንስ ሆዷን እየገፋ መጣ።ይሄን የተመለከተውም የአጎቷ ልጅ ዩሱፍ ሁኔታው በጣም ግራ አጋባው።

አርግዛ ነው እንዳይል ከቤተ አምልኮ ከሱ ውጭ ከማንም ወጥታም ታይታም አጣውቅም።ምንም አልተፈጠረም እንዳይል የእርግዝና ምልክቶች እንዳለ ይታዩባታል።

በመጨረሻም ይሄን የሚያጣራበት አንድ መፍትሄ አገኘ'ና ሊያናግራት ወስኖ እርሷ ዘንድ በመሄድ፦"መርየም የሆነ ነገር በውስጤ ይመላለሳል።እደብቅሻለሁ እያልኩ ግን አልቻልኩም በቃ ልጠይቅሽ" አላት።

               #ይቀጥላል.............

Send as a message
Share on my page
Share in the group