📜 አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱ ላሂ ወበረካትሁ
📌 ነብዩላህ ኑህ ዐለይሂ ሰላም
📍 አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ከነዚያ ህዝቦች ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራቸው ዘንድ ኑህ የተባሉ መልዕክተኛን አስነሳ።
👉 ኑህም ህዝባቸውን ሰበሰቡና፦
"እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ። አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም። በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ (ክፍያ) አልጠይቃችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም" ብለው ህዝባቸውን ተጣሩ።
👉 ይህን ሲሰሙ አስተባበሉት። ምንም ሊያምኑለት አልቻሉም። እንዲያውም
ያፌዙበት ጀመር።
👉 ኑህ ዐለይሂ ሰላም ያለመሰላቸት ዘወትር ጥሪም ያደርግላቸውም ነበር።
👉 የህዝቦቹ ማፊዝ እና ማላገጥ በበዛበትም ግዜ፦ "ወገኖቼ ሆይ‼ ምንም መሳሳት የለብኝም፡፡ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልእክተኛ ነኝ፡፡ የጌታዬን መልዕክቶች አደርስላችኋለሁ፡፡ ለእናንተም እመክራችኋለሁ፡፡ ከአላህም
በኩል የማታውቁትን አውቃለሁ።" አላቸው።
👉 የኑህን ዐለይሂ ሰላም ንግግር በሰሙ ጊዜ በጣም በመገረም፦ "አንተ ኑህ‼ አንተ እኮ እንደኛው ሰው ነህ እንዴት ነው መልዕክተኛ ነኝ ምትለው?
በዛ ላይ ጥቂት ተከታዮች አሉህ። ሁሉም ግን ድሀ እና ኮሳሳ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ናቸው።
ደግሞም በሀብትም ሆነ በክብር ከኛ ጋር አትመጣጠኑም" ብለውም አስተባበሉ።
👉 ያም አላንስ ብሏቸው እርስ በርስ በሚፈፅሙት የሀውልት አምልኮ እንዲፀኑ ይመካከሩም ጀመር።
👉 ኑህም የህዝቡ ሁኔታ ተስፋ ሲያስቆርጠው በመለማመጥ መልኩ፦ አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከእናንተው (ጎሳ) በኾነ ሰው ላይ
እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ቢመጣላችሁ ትደነቃላችሁን" እያለ
ቢያግባባቸውም ክህደታቸው ይበልጥ እየጨመረ እንጂ ምንም አይቀንስም
ነበር።
👉 ምንም እንኳን ኑህ ዐለይሂ ሰላም የህዝቡ ነገር ተስፋ ቢያስቆርጣቸውም ተልዕኮዋቸውን በሚገባ በማድረስ ላይ ቀጥለዋል።
👉 እናም ሁሌ ቀን እና ማታ ህዝባቸውን ስለ አላህ ሲያስታውሷቸው ህዝባቸው
የነቢያቸውን ዳዕዋ ከመስማት ጆሮዋቸውን መያዝ ጀመሩ።
👉 ጆሮዋቸውን ይዘው መስማት እንቢ ሲሉ ኑህ ዐለይሂ ሰላም በምልክት ይነግሯቸው ነበር።
👉 ኑህም በምልክት ሲነግሯቸው ህዝቡ ግን አይኖቻቸውን በልብሶቻቸው ይሸፍኑ ነበር።
👉 ምንም ተስፋ አልቆርጥ ብሎ መቆም መቀመጥ ሲከለክላቸው፦ "ድሆች እና
ዝቅተኛ ሰዎች ያንተ ተከታይ ሆነው ሳለ እኛም ከነሱ ጋር እንድንከተልህ ትሻለህን‼
👉 ይልቁንስ እኛ እንድንከተልህ ከፈለግክ እነዚህን ተራ ሰዎች ከጎንህ አርቃቸው።" አሉት።
👉 ኑህ'ም ዐለይሂ ሰላም፦ "እነሱ የሚሰሩትን አላህ ነው ሚያውቀው። እኔ ላባርራቸው አልችልም። እንዴትስ ረዳቶቼን፣ አክባሪዎቼን አባርር ትሉኛላችሁ??? ቆይ ባባርራቸውስ እኔን
ከአላህ ማን ያተርፈኛል??? አታስተውሉምን???" ብሎ ጠንከር አለባቸው።
👉 ኑህ ዐለይሂ ሰላም መልካም ነብይ ነበሩ። ሀብታም፣ ድሀ ደከማ፣ ጠንካራ፣ ትልቅ፣ ትንሽ ስይሉ ለሁሉም በክብር የተላኩትን ዳዕዋ አደረሱ።
👉 ምንም እንኳም ለ950 አመታት ዳዕዋ ቢያደርጉም ዳዕዋቸውን ከ80 በላይ ሰው ሊቀበላቸው ባለመቻሉ ሁኔታው ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ለጌታቸው ስሞታ ለማቅረብ ተገደዱ።
👉 እንዲህም ሲሉ ለአላህ ነገሩት፦ "ጌታዬ‼ ህዝቦቼ እኮ አስተባበሉኝ። በእኔና በእነርሱም መካከል (ተገቢ) ፍርድን ፍረድ፡፡ አድነኝም፡፡ ከእኔ ጋር ያሉትንም ምእምናን(አድን)፡፡"
👉 ከዚህ በኋላ የኑህ ዐለይሂ ሰላም የዳዕዋ ጥሪ ዛቻ አዘል መሆን ጀመረ።
👉 እነሱም ለኑህ ዐለይሂ ሰላም ዛቻ ግድ አልነበራቸውም ይልቁኑ፦ "የምትዝትብንን አምጣ እውነተኛ ከሆንክ" እያሉ ሲሳለቁበትም ጀመር።
👉 ኑህም፦ "ይህ እኮ በኔ ቁጥጥር ውስጥ አይደለም። ያ የአላህ ስልጣን ነው" ይላቸዋል።
👉 አሁን ነገሩ መቋጫው ተቃርቧል።
👉 አላህም አስፈሪ ወህይ እንዲህ ሲል ወደ ኑህ አወረደ፦" ከሕዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር (ወደፊት ከአሁን በኋላ) አያምኑም፡፡ ይሠሩትም በነበሩት (ክህደት) አትዘን"
👉 በመቀጠልም አላህ ኑህን ዐለይሂ ሰላም የዘንባባ ችግኝ እንዲተክል አዘዘው።
👉 ያች ዛፍ ለማፍራት ስትበቃ የአላህ ቅጣትም በነዚያ ህዝቦች ላይ እንደሚፈፀም ቃል ገባለት።
👉 የአላህ የተለምዶ እዝነቱ የታወቀ ነው።
👉 ትልልቅ ሰዎች ባጠፉት ህፃናትን
አይቀጣም'ና ህፃናት የቅጣቱ ሰለባ እንዳይሆኑ ቅጣቱ ከመፈፀሙ ከ40
አመታት በፊት የሴቶቹ ማህፀን ፅንስ መሸከም እንዳይችል አደረገው።
👉 ለ40 አመት ያህል ምንም አይነት ህፃን ሳይወለድ ቀረ።
👉 በዚያ ዘመም ኑህ ዐለይሂ ሰላም የታዘዘውን ዛፍ እንክብካቤ ሲያደርግ
👉 እነዚህ አመፀኛ ህዝቦች እንዲህ በማለት ይሳለቁበት ነበር፦ "አንተ ኑህ ነቢይ ነኝ እያልክ ዘራፍ ብለህ አላዋጣ ሲልህ ወደ ግብርና ገባህ እንዴ‼"
👉 ድንጋይም ይወረውሩባቸው ነበር።
👉 የተተከለው ዛፍ 50 አመት ሲሞላው አላህም ለኑህ ዐለይሂ ሰላም ወህይ በማውረድ ዛፎችን እንዲቆጣቸው አዘዛቸው።
👉 ኑህም ዐለይሂ ሰላም ዛፎቹን ከቆረጠ በኋላ አላህም ትልቅ መርከብ እንዲሰራ
አዘዘው።
👉 ጂብሪልም መርከብ እንዴት እንደሚሰራ ሊያሳየው ከሰባት ሰማያት
ወረደ።
👉 አላህም እንዲህ ሲል ወህይ አወረደ፦
"የመርከቧ ርዝመት 1200 ክንድ
የጎን ስፋት 800 ክንድ
ከፍታው ደግሞ 80 ክንድ የሆነችን መርከብ ስራ"
👉 በተንጣለለ አሸዋማ እና በረሀማ ቦታ ላይ ኑህ መርከቧን መስራት ጀመሩ።
👉 ህዝቦቹም ከአጠገቡ ሲያልፉ፦
"አንተ ኑህ ከነብይነት አናፂነት ይሻላል
ብለህ ነው?" እያሉ ያፌዙበታል።
👉 ከፊሎቹ ደግሞ፦ "አንተ ኑህ መርከብ እኮ ለባህር ነው የሚሰራው አንተ እልም
ያለ በረሀ ላይ ትሰራለህ እንዴ‼" ይሏቸዋል።
👉 ኑህም ለስለስ ባለ አንደበት፦ ኢንሻ አላህ #የነብዩሏህ_ኑህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ
...ይ
.......ቀ
...........ጥ
...............ላ
....................ል