Translation is not possible.

السلام  عليكم  ورحمة  الله وبركاته

#የነብዩሏህ_ኢሳ_የመርየመ_ልጅ  #ዓለይሂ_ሰላም_ታሪክ  

#ክፍል_ሁለት

መርየምም፦"መልካምን ንግግር ተናገር(ጠይቅ)" አለችው።

ዩሱፍም፦"ቡቃያ ያለ ዘር ይበቅላልን?" አላት።

መርየምም፦"አዎን ይበቅላል" አለችው።

ዩሱፍም፦"አረንጓዴ ቅጠልስ ዝናብ ሳያገኝ መብቀል ይችላልን?" አላት።

መርየምም፦"አዎን መብቀል ይችላል" አለችው።

ዩሱፍም፦"ያለ ወንድ ሴት ልጅ ብቻ መውለድ ትችላለችን?" አላት።

መርየምም፦"አዎን ትችላለች" አለችው።

መርየምም ቀጠል አድርጋ፦" ዩሱፍ ሆይ! አላህ ቡቃየን የፈጠረ ቀን ያለ ዘር እንደፈጠረው አታውቅምን?!!

አላህ አረንጓዴ ቅጠልንስ ለመጀመሪያ ግዜ ሲፈጥረው ያለ ዝናብ እንደፈጠረው አታውቅምን?!!

ታዲያ መጀመሪያ ቅጠልን እና ቡቃያን ዘርም ሆነ ዝናብ ሳይኖር የፈጠረው ጌታ አሁን ያለ ዝናብ እና ያለ ዘር መፍጠር ይከብደዋል ትላለህን!!!?" አለችው።

ዩሱፍም፦"አይ እኔ እንደዛ ልል ፈልጌ አይደለም አላህ በፈለገው ነገር ላይ ሁሉ ቻይ ነው።አንድን ነገር ማድረግ በፈለገ ግዜም ሁን ይለዋል ይሆናልም" አላት።

መርየምም፦"አላህ ያለ ወንድም ሆነ ያለ ሴት አደምን አልፈጠረምን!!!? ያለ ሴትስ ሀዋን አልፈጠረምን!!!?" አለችው።

ዩሱፍም፦"አዎን ፈጥሯል" አላት። ከዚያም በልቡ ግን መናገር ያልፈለገችው ያአላህ ተአምር በሆዷ እንዳለ አወቀ።

መርየምም የመውለጃ ሰዐቷ በተቃረበ ግዜ የቤተ አምልኮውን ግቢ ለቃ ወጣች።ብቻወን በረሀ ላይ ሳለች ምጡ ጀመራት በጣምም አመማት አሁን ያለችበትን እንግልት እና ከመውለዷ በኋላ የሚከተላትን እንግልት ስታስብ፦"ዋ! ምኞቴ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ፡፡ ተረስቼም የቀረሁ በሆንኩ" ብላ ተመኘች።

በመጨረሻም ወደ አንድ የደረቀ የተምር ዛፍ ዘንድ በመጠጋት ልጇን ዒሳን ተገላገለች።ልክ ልጁን እንደተገላገለች ጂብሪል መጣ'ና፦" አትዘኝ፡፡ ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል፡፡

የዘምባባይቱንም ግንድ ወዳንቺ ወዝውዣት ባንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና፡፡ብይም፣ ጠጭም፣ ተደሰችም" አላት።

በልታ ስታበቃም ጂብሪል፦"ማንም ሰው ሊያናግርሽ ቢፈልግ እኔ ለአር ረህማን(ለአላህ) ማንንም ሰው ላላናግር ፆሚያለሁ በይ" አላት።

ኢብሊስም መርየም ልጇን ከተገላገለች በኋላ ወደ ኢስራኢላውያኑ ካህናት በመሄድ የመርየምን መውለድ ነገራቸው።ካህናቱም በጣም በመቆጣት ይዝቱባትም ጀመሩ።

ከዚያም መርየም ልጇን ተሸክማ ወደ ቤተ አምልኮው መጣች። ሁሉም ተሰብስቧል....ገና ፊትለፊታቸው ብቅ ስትል፦"የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም" አሏት።(የሀሩን እህት ያሏት ሳሊህ ሰዎችን በሀሩን ስለሚመስሉ ነው።)

እሷም ምንም መልስ ሳትሰጥ ህፃኑን እንዲያናግሩ ወደ ልጇ አመላከተቻቸው።ሁሉም በሁኔታዋ በመገረም ዚና ያደረገችው እንሷት እኛ ላይ ታሾፋለች እንዴ እያሉ ከተነጋገሩ በኋላ፦"በአንቀልባ ያለን ሕጻን እንዴት እናናግራለን" አሏት።

ያን ግዜ ህፃኑ ዒሳ  ቀና

ይቀጥላል............🖊️

Send as a message
Share on my page
Share in the group