UMMA TOKEN INVESTOR

umma1698146359 Сhanged his profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

✍️ #ኢስቲግፋር ማድረግ

ጭንቀትን እና ሀዘን #ማስወገድ ሲሆን

✍️አላህ #ኢስቲግፋር አድራጊዎችን በእውነት #ክንፍ_ስር ያቅፋቸዋል «❥︎»#አላህ ከሚወዳቸው #ባሪያዎቹ ያድርገን🤲

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የቀድሞ የ አሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እስራኤል በጋዛ በንጹሃን ላይ የምትወስደውን እርምጃ ተቃወሙ።

እስራኤል ከሃማስ ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት በፍልስጤማውያን ንጹሃን ላይ የወሰደችው እርምጃ ዋጋ እንደሚያስከፍላት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ተናገሩ።

ቴል አቪቭ በጋዛ ምግብ፣ ውሃ እና ኤሌክትሪክ ማቋረጥ የፍልስጤማውያንን የትግል አመለካከት ይበልጥ እያጠነከረው እንደሚሄድም ገልጸዋል።

የሰብአዊ ኪሳራን ታሳቢ ያላደረገ የእስራኤል ወታደራዊ ስትራቴጂም በመጨረሻ ውጤቱ በተቃራኒው መሆኑ አይቀርም ብለዋል።

የጋዛ ነዋሪዎችን መሰረታዊ አገልግሎቶች ማቋረጥ የሰብአዊ ቀውሱን ከማባባሱ ባሻገር “እስራኤል በአለማቀፍ ደረጃ ድጋፍ እንድታጣ እና ጠላቶቿ እንዲበዙ ያደርጋል” ሲሉም ተደምጠዋል።

ይህም በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ለአመታት ሲደረጉ የቆዩ ጥረቶችን ወደኋላ ይመልሳል ነው ያሉት።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሃማስን ጥቃት ባወገዙበት ንግግራቸው እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት ቢገልጹም ጦርነቱ በንጹሃን ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ሊታሰብበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኦባማ በዋይትሃውስ የስምንት አመት ቆይታቸው እስራኤል ከሃማስ ለሚሰነዘርባት ጥቃት ምላሽ እንድትሰጥ ድጋፍ ማድረጋቸውን ሬውተርስ በዘገባው አስታውሷል።

አሜሪካ ከኢራን ጋር በ2015 ያደረገችው የኒዩክሌር ስምምነት ግን የኦባማ እና ኔታንያሁ ግንኙነትን ማሻከሩ አይዘነጋም።

የኦባማ ምክትል የነበሩት የአሁኑ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም ሁለቱን መሪዎች ለማቀራረብ ሲሞክሩ የቆዩ ሲሆን፥ አሁን ላይ ዋነኛ የኔታንያሁ አጋር ሆነዋል።

ባይደን በኦባማ የስልጣን ዘመን ተጀምሮ የነበረውን የእስራኤል እና ፍልስጤም መሪዎች ድርድር ጫፍ ከማድረስ ይልቅ የጦር መሳሪያዎች እና ወታደሮችን በመላክ ውጥረቱን እያባባሱት ነው።

18ኛ ቀኑን በያዘው የእስራኤልና ሃማስ ጦርነት ህይወታቸው ያለፈ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ5 ሺህ በላይ ሆኗል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

"ኡማ ላይፍ"ን እንቀላቀል!

•••••••••••••••••••••••••

ፌስቡክ ወራሪዋ እስራኤልን የሚያወግዝና ፈለስጢንን የሚደግፉ ልጥፎችን በማስወገድ ለእስልምና እና ሙስሊም ያለውን ጥላቻ በግልፅ እያሳየን ባለበት በዚህ ወቅት በነፃነት ስለ ሙስሊሙ አለም የሚወራበትና ሐራም ነገሮች ክልክል የተደረጉበት ኡማ ላይፍ የተሰኘ የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ይፋ ተደርጓል።

ይህን የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ሁላችንም አካውንት በመክፈት ልንቀላቀል እና ለሌሎች ልናስተዋውቅ ይገባል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ለሸሀዳ የተቀሰረች ጣት!

ከፍርስራሽ መሐል ቦግ ብላ የምታበራ!

የእሳት አሩር ያላጠፋት የድሮን ቦንብ ያላደበዘዛት አመልካች ጣት!

Send as a message
Share on my page
Share in the group