UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ፈጅርን አለመስገድ ያለው አደጋ! እና ከዚህ አደጋ ለመዳን መጠቀም ያለባቹ መፍትሄዎች!!!

❶📌 የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ከፈጅር ሶላት

መሳነፍ አደገኛ የሆነ የሙናፊቆች ምልክት ነውና!!

[ቡኻሪና ሙስሊም]

❷♦️ የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ የሸይጣን መፀዳጃ አትሁን፡፡ በአንድ ወቅት ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ እስከሚነጋ ድረስ ሌሊቱን ስለሚተኛ ሰው ተወራ፡፡ ይህኔ እሳቸው እንዲህ አሉ፡- “ያ በጆሮዎቹ ውስጥ ሸይጣን ሽንቱን የሸናበት ሰው ነው!” አሉ፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 644]

❸📌 የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ያለበለዚያ የሸይጣን ወጥመድ ሲሳይ ትሆናለህ፡፡ ቀንህን ሙሉ ድብርት ይጫጫንሃል፣ ንቃት ይቀልሃል፡፡ ፈጅር ላይ ተነስቶ ውዱእ አድርጎ ያልሰገደ ሰው ቆሻሻ ነፍስ ይዞ እንደሚያነጋና ስንፍና እንደሚጫጫነው ተናግረዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]

❹♦️ ፈጅርን ስገድ ያለበለዚያ በቀብርህ ውስጥ እስከ

እለተ ቂያማ የሚዘልቅ ዘግናኝ ስቃይ ትሰቃያላህ፡፡ ከነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተላለፈው አንድ ሰው

ተንጋሎ ሌላው ካጠገቡ ቋጥኝ ይዞ በመቆም እራሱን

ይደቁሰዋል፡፡ ድንጋዩ ተንከባሎ ሲሄድም እሱን አምጥቶ

እስከሚመለስ ድረስ እራሱ እንደነበር ይመለሳል፡፡ ከዚያም እንደ መጀመሪያው ይሰራበታል፡፡ ቂያማ እስከሚቆም ድረስም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል፡፡ ይህን በዚህ መልኩ የሚሰቃየውን ሰውየ ምንነት ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጂብሪል ሲጠይቁት “ይሄ ቁርኣንን ይዞ ፊት የሚነሳው ከግዴታ ሶላትም የሚተኛ ነው” አላቸው፡፡

ወንድም እህቶች ሆይ! ከፈጅር ሶላት አትዘናጉ፡፡ ወቅቱን ጠብቃቹ እንድትሰግድ የሚያግዛቹሁን ብልሃትም ተጠቀሙ!

❶♦️በጊዜ ተኛ! የምሽት ወሬ ይቅር፡፡ ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከዒሻ በፊት እንቅልፍ፣ (ከዒሻ) ቡኋላ ደግሞ ወሬ ይጠሉ ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]

❷📌ቀኑን በወንጀል ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ወንጀል ከኸይር

ስራ ያቅባል፡፡ በሌላ በኩል ለኸይር ስራ ትጋ፡፡ ኢስላማዊ

የመኝታ ስርኣቱን ጠብቅ፡፡ የኸይር ስራ አንድ ሽልማቱ

ለሌላ ኸይር ስራ መታደል ነውና፡፡

❸♦️ማታ ከመተኛትህ በፊት ለፈጅር ለመነሳት ቁርጠኛ

ውሳኔ አድርግ፡፡ ረጅም ጉዞ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ

ቢኖርብህ ያለ ማንም አጋዥ ምናልባትም ያለአላርም

እየነቃህ ለሶላት ሲሆን መዘናጋትህ ስለእውነት ከባድ

የሞራል ልሽቀት ነው፡ችዋ

❹📌 ማንቂያ ደወል (አላርም) ተጠቀም፡፡ ምናልባት

ሳይታወቅህ አጥፍቶ የመተኛት አጉል ባህሪ ካለብህ ትንሽ

ራቅ አድርገህ አስቀምጠው፡፡

❺♦️በሰአቱ ነቅተህ ከተጫጫነህ “ትንሽ ተኛ” ለሚሉ ሸይጣን እና ነፍስያ ሸንጋይ ጉትጎታ እድል አትስጥ፡፡ መነሳትህ ያለውን ዋጋ፣ መተኛትህ ያለውን አደጋ ላፍታ አስብ፡፡ ብትነሳ 50 ዶላር ይሰጣል ቢባል የሚኖርህን ንቃት ቃኝና እራስህን ታዘብ፡፡ ፈርዱ ቀርቶ ትርፍ የሆነችዋ የፈጅር 2 ረከዐ እንኳን ከዱንያ ፀጋ ሁሉ በላጭ እንደሆነች እራስህን አስታውስ!

❻📌በመልካም የሚያግዝ ጓደኛ ወይም የህይወት አጋር

ካለህም እሰየው! አልሀምዱሊላ ነው

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

👉 ምን ማድረግ እንችላለን ?

ውድ በየሀገሩ ሆናችሁ ለፍልጢን ህፃናትና አዛውንቶች ደም እንባ ለምታነቡ ። የሚጠባ ህፃን የእናቱን ጡት እንደጎረሰ በአይሁድ ጅቦች ሲበላ ለምታዩ አማኞች ። እርዳታ የሚፈልጉ አቅመ ደካሞችና አዛውንቶች ከላይ በጦር አውሮፕላን በሚዘንበው የእሳት ቦንብ እየጋዩ ከስር በታንክ ሲጨፈለቁ ለምታዩ የአላህ ባሮች ምን ማድረግ እንደምንችል ልንገራችሁ ወላሂ ይህን በሰው አካል የተፈጠረ ሰው በላ አውሬ የምናጠፋበት መሳሪያ በእጃችን አለ ። አው ጠላት ሊጠቀምበት የማይችል መሳሪያ በእጃችን አለ ። እውን የፍልስጢን ህፃናትና አዛውንት ስቃይ እንዲያበቃ የነብያት መሰደጃ የሆነው ታሪካዊ የተቀደሰ የአላህ ቤት መስጂደል አቅሳ ከዚህ አውሬ መረገጥ እንዲጠበቅ የምንፈልግ ከሆነ ይህን መሳሪያ እንጠቀመው ።

ይህ መሳሪያ በየአንዳንዱ ሙእሚን እጅ ላይ ነው ያለው ። እሱም የዱዓእ መሳሪያ ነው ።

መሳሪያ ኢላማውን እንዲመታ አጠቃቀሙን ማውቅ ያስፈልጋል ። እንዳገኙት ቢተኩሱት ኢላማውን አይመታም ። በመሆኑም የዚህ የዱዓእ መሳሪያ ኢላማው እንዲመታ ከቻልን ውዱእ አድርገን ሁለት ረካዓ ሰግደን ስጁዱን አርዝመን ተደፍተን የዚህ አውሬ ማንነትና በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለውን መከራና ስቃይ ከፊትለፊታችን አድርገን የአላህን ሀያልነትና ሁሉን ቻይነት በማሰብ በኛና ፍልስጢን ላይ ባሉ ወነጀለኛ በሆኑ ባሮቹ ምክንያት እርዳታውን እንዳይነፍጋቸው እንባችንን በማርገፍ እንለምነው ። አይታወቅም ከኛ ውስጥ አላህ የሚሰማው ይኖራል እኔ አላህ አይሰማኝም አንበል ።

አላህ ባሮቹ የፈለገ ወንጀል ቢኖርባቸው ከሱ በስተቀር የሚረዳና ከመከራ የሚያወጣ እንደሌለ አውቀው ወደርሱ እጃቸውን ሲዘረጉ ይሰማል ። ፈረጀት ያመጣል ።

በዚህ መልኩ ማድረግ ባንችል ለፍልስጢን ህፃናትና አዛውንት አላህ ፈረጀት ሊያመጣ ለሰው ዘር ባጠቃላይና ለአላህና ለመልእክተኛው እንዲሁም ለሙስሊሞች በተለይ ጠላት የሆነውን ሰው በላው የአይሁድ አውሬ አላህ እንዲያጠፋው ነይተን ፀደቃ ሰጥተን ዱዓእ እናድርግ ።

ይህን ማድረግ ካልቻልን ሶላታችን በሰገድንበት አጋጣሚ ያ አላህ እንበል ። እርግጠኛ እንሁን አላህ ይሰማናል ። ጊዜና ቦታ መምረጥ መስፈርት አይደለም ሁላችንም ፊታችንን ወደ አላህ አዙረን ያ አላህ እንበል የአላህ እርዳታ መጥቶ ፍልስጢን ከዚህ አውሬ ነፃ እስክትሆንና ህፃናትና አዛውንቶች ከመበላት እስኪድኑ መስጂደል አቅሳ ዳግም የእነዚህ አውሬዎች መረጋገጫ ከመሆን ስጋት እስኪወጣ አላህን እንለምን ።

አላህ ሙስሊሞችን ወደ ትክክለኛ ዲናቸው መልሶ በተውሒድና ሱና ላይ ፀንተው ጠላት ሲያስባቸው የሚፈራቸው ያድርግልን ።

እርግጠኛ እንሁን ሙስሊሞች አሁን ላሉበት ውድቀት መንስኤው ከዲናቸው መራቃቸውና የነብዩን ሱና መተዋቸው ነው ። ሙስሊሞች አላህን ፈርተው የሱን ትእዛዝ ፈፅመው ወደ መልእክተኛው መከተል ቢመለሱ እነዚያ የመጀመሪያዎቹ ትውልዶች አላህ የበላይ እንዳደረገው የበላይ ያደርጋቸዋል ። አላህ በተውሒድና በሱና የበላይ የምንሆን ህዝቦች ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka

Telegram: Contact @bahruteka

Telegram: Contact @bahruteka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahr
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🚫 የፍልስጢን ጤና ሚኒስቴር

" ፍልስጢን ውስጥ በወራሪው ኢስራኢል የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 6546 መድረሱና ከእነዚህ ውስጥ 2704ቱ ህፃናት መሆናቸውን ገለፀ ።"

የሐማስ ወታደሮች ቤተሰቦቻቸውን አሽሽተው ራሳቸው ጉድጓድ ውስጥ ሆነው የፍልስጢን ህፃናትና አዛውንት ያስጨርሳሉ ። የዚህ ድራማ ሚስጢር አላህ ሳያወጣው አይቀርም ። ኢራን በምትመራው ሐማስ የተወሰደው የመጀመሪያው እርምጃ እውን ኢስራኢል ሳታውቀው ቀርታ ነው ? ወይስ ኢስራኢል 1400 ሰው አጥታ የፍልስጢን ተተኪ ትውልድ ማጥፋት መርጣ ይሁን ?

በኢራን አይዞህ ባይነት ሐማስ በወሰደው እርምጃ 1400 ኢስራኢላዊያን መጀመሪያ ላይ ሞቱ ከዛ በኋላ የፍልስጢን ህፃናትና አዛውንቶች ይረሸናሉ ። ምእራባዊያን ኢስራኢል ራስዋን የመከላከል መብት አላት ብለው ሽፋን በመስጠት በመሳሪያና በገንዘብ ይረዳሉ ።

ይህ እንደሚሆን አውቀን ነው የሚሉት የሐማስ ወታደሮች የዐረብ ሀገሮችን አማክረው የገቡበት ይመስል ትተውናል ብለው እሪ ይላሉ ። የኢራንና የኢኽዋን የገደል ማሚቶ የሆኑ ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች ዐረብ ሀገራት ለምን ገብተው ህዝቦቻቸውን አላስጨረሱም ብለው ያላዝናሉ ።

ቅስም የሚሰብረውና የሰራካላት የሚያሳምመው ንፁሇን ህፃናትና አዛውንቶች ኢኽዋንና ራፊዳ ላቀጣጠሉት እሳት ማገዶ መሆናቸው ነው ።

ሁሉን አዋቂና ተመልካች የሆነው አላህ ደካማ ፍልስጢናዊያንን ከዚህ በላእ ያውጣልን ። ለሁሉም የሚገባውን ይስጥልን ። ሁሉን ቻይና የሀይል ባልተቤት እሱ ብቻ ነውና ።

https://t.me/bahruteka

Telegram: Contact @bahruteka

Telegram: Contact @bahruteka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahr
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አሚን ያረብ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group