Translation is not possible.

🚫 የፍልስጢን ጤና ሚኒስቴር

" ፍልስጢን ውስጥ በወራሪው ኢስራኢል የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 6546 መድረሱና ከእነዚህ ውስጥ 2704ቱ ህፃናት መሆናቸውን ገለፀ ።"

የሐማስ ወታደሮች ቤተሰቦቻቸውን አሽሽተው ራሳቸው ጉድጓድ ውስጥ ሆነው የፍልስጢን ህፃናትና አዛውንት ያስጨርሳሉ ። የዚህ ድራማ ሚስጢር አላህ ሳያወጣው አይቀርም ። ኢራን በምትመራው ሐማስ የተወሰደው የመጀመሪያው እርምጃ እውን ኢስራኢል ሳታውቀው ቀርታ ነው ? ወይስ ኢስራኢል 1400 ሰው አጥታ የፍልስጢን ተተኪ ትውልድ ማጥፋት መርጣ ይሁን ?

በኢራን አይዞህ ባይነት ሐማስ በወሰደው እርምጃ 1400 ኢስራኢላዊያን መጀመሪያ ላይ ሞቱ ከዛ በኋላ የፍልስጢን ህፃናትና አዛውንቶች ይረሸናሉ ። ምእራባዊያን ኢስራኢል ራስዋን የመከላከል መብት አላት ብለው ሽፋን በመስጠት በመሳሪያና በገንዘብ ይረዳሉ ።

ይህ እንደሚሆን አውቀን ነው የሚሉት የሐማስ ወታደሮች የዐረብ ሀገሮችን አማክረው የገቡበት ይመስል ትተውናል ብለው እሪ ይላሉ ። የኢራንና የኢኽዋን የገደል ማሚቶ የሆኑ ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች ዐረብ ሀገራት ለምን ገብተው ህዝቦቻቸውን አላስጨረሱም ብለው ያላዝናሉ ።

ቅስም የሚሰብረውና የሰራካላት የሚያሳምመው ንፁሇን ህፃናትና አዛውንቶች ኢኽዋንና ራፊዳ ላቀጣጠሉት እሳት ማገዶ መሆናቸው ነው ።

ሁሉን አዋቂና ተመልካች የሆነው አላህ ደካማ ፍልስጢናዊያንን ከዚህ በላእ ያውጣልን ። ለሁሉም የሚገባውን ይስጥልን ። ሁሉን ቻይና የሀይል ባልተቤት እሱ ብቻ ነውና ።

https://t.me/bahruteka

Telegram: Contact @bahruteka

Telegram: Contact @bahruteka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahr
Send as a message
Share on my page
Share in the group