UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Nejat Jemal 1 shared a
Translation is not possible.

ኢብን አልቀይም ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላል

"እውቀትን እና የዕውቀት ባለቤቶችን የወደደ በእርግጥመመ አላህ የወደደውን ወዷል።"

#ምንጭ [መፋቲሁ ዳሩ ሰአዳህ 1/ 435]

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Nejat Jemal 1 shared a
Translation is not possible.

ጌታህን ጠቃሚ እውቀት ጠይቅ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿سَلوا اللهَ عِلمًا نافعًا وتعَوَّذوا باللهِ مِن علمٍ لا ينفعُ﴾

“አላህን ጠቃሚ እውቀት እንዲሰጣችሁ ጠይቁት። ከማይጠቅማችሁ እውቀትም በአላህ ተጠበቁ።”

📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 1511

Join my page 👉 Abdulmenan Amin

✌️✌️🇵🇸🇵🇸

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Nejat Jemal 1 shared a
Translation is not possible.

ሙዓዊያ እና ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁማ በተጋጩ ጊዜ ሁለት ኢስላማዊ ስረወ መንግስት ተመሰረተ የሮሙ ንጉስ ይህን ሰምቶ እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈ ፦

" ከሮም ንጉሰ ነገስት ለሙስሊሞች መሪ ሙዐዊያ አቡ ሱፍያን!! 

ባንተ እና በዐሊይ መካከል የተከሰተውን ግጭትሰምተናል ስለዚህም ለሙስሊሞች መሪ አንተ መሆን እንዳለብህም ስለምናምን አንተ ፍቃድህ ከሆነ የዐሊይን ጭንቅላት 

ቀንጥሶ የሚያመጣልህን ወታደር ልላክልህ "

ይህ ደብዳቤ ሙዐዊያ ጋር እንደደረሰም ሙዓዊያም :-

" ከሙዓዊያ ለሮም መሪ!!! ሁለት ወንድማማቾች ስለተጣሉ አንተ ምን አገባህ? አፍህን የማትዘጋ ከሆነ ጅማሬው እኔ ጋ የሆነ 

እና ፍፃሜው አንተ ጋ የሆነ ሰራዊት ልኬ አንገትህን በማስቀንጠስ ለዐሊይ በስጦታ መልኩ አበረክትለታለሁ "

#ይህ_ትክክለኛ_ሙስሊሞች_ሳለን_ነው‼️

============================

ኻሊድ ኢብን ወሊድ ለፐርሺያው ንጉሰ ነገስት እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈለት፦

"ስለም ትድናለህ። እንቢ ያልክ እንደሆን ግን፤ እናንተ ህይወትን የምትወዱትን ያህል ሞትን የሚወዱ ሰራዊቶችን ይዤልህ 

እመጣለሁ።" 

ንጉሱ ይህን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ የቻይናውን ንጉስ የጦር እርዳታ ሊለምነው ደብዳቤ ፃፈለት። የቻይናውም ንጉስ እንዲህ ሲል ደብዳቤ መልሶ ላከለት። 

"ንጉስ ሆይ! ተራራን እንኳን ለመናድ ካሰቡ ምንም ከማያግዳቸው ወታደሮች ጋር ለመጋፈጥ አቅሙ ስለሌለኝ 

ጥያቄህን መፈፀም አልችልም።"

# ምን_ያህል_ሀያላን_እንደነበርን_ተመልከቱ ‼️

============================

በደውለቱል ዑስማኒያ የአገዛዝ ዘመን የሙስሊም ወታደሮች የጦር መርከቦቻቸውን ይዘው በአውሮፓ ደሴቶች ሲያልፉ በአከባቢው ያሉ አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ሙስሊሞች መጥተው ፈትህ እንዳያደርጉ በመፍራት ከበሮ ከመምታት እና ምንም አይነት ድምፅ ከማሰማት ይቆጠቡ ነበር። 

#ያኔ_ጀግና_ሳለን‼️

============================

በደውለቱል ኡስማኒያ የአገዛዝ ዘመን በያንዳንዱ ቤት ደጅ ላይ ሁለት የበር ማንኳኩያዎች ይኖራሉ። አንዱ ትልቅ ሲሆን አንዱ ትንሽ ነው። በትልቀኛው ከተንኳኳ አንኳኪው ወንድ ነውና በሩን ሊከፍት 

የሚመጣው ወንድ ይሆናል። ነገር ግን በትንሸኛዋ ከተንኳኳ አንኳኪዋ ሴት መሆኗ ስለሚታወቅ ሴት ትከፍትላታለች። 

በዚያ ምርጥ ዘመን አንድ ቤት ውስጥ ሰው ከታመመ ደጅ ላይ ቀይ አበባ ይንጠለጠል ነበር። ያን አበባ የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ 

እዚያ ቤት በሽተኛ መኖሩን ስለሚያውቁ በበሩ ሲያልፉ ድምፃቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር። 

#ሹፍ_ምን_እንመስል_እንደነበር ‼️

============================

ጊዜው ሰላሀዱን አል አዩቢ በይተል መቅዲስን ባስመለሰበት ግዜ ነበር። እና ጦርነቱ ነገውን ሊጀመር ማታ ላይ የጦር መሪው ሰላሀዲን የወታደሮቹን ድንኳን እየዞረ ሲያዳምጥ፤ ግማሹ ለይል ይሰግዳል፣ ሌላው ቁርአን ይቀራል፣ የተቀሩት ደግሞ ይዘክራሉ። 

ግን ድንገት በሆነ ድንኳን አጠገብ ሲያልፍ በድንኳኑ ውስጥ ያሉት ሁሉም ተኝተው ነበር። ይህን ጊዜ ፦"በዚህች ድንኳን አዳሪዎች 

ምክንያት ልንሸነፍ እንችላለን" ብሎ አለፈ። 

#ማንተኛበት_ዘመን‼️ 

___ 

ቀደምት ዑለማዎች በሶስት ነገራት አደራ ይባባሉ ነበር። 

1.ሰውዬው በሱ እና በአሏህ መካከል ያለውን ግንኙነት ካሳመረ፤በሱ እና በሌሎች መካከል ያለው ግንኙነት ያምርለታል። 

2.ሰውዬው ሚስጥራዊ ተግባሩን ካሳመረ አሏህ ይፋዊ ተግባሩን ያሳምርለታል። 

3፦ሰውዬው የአኺራው ጉዳይ ካስጨነቀው አሏህ የዱንያውንም የአኺራውንም ጉዳይ ያግራራለታል። 

============================

#ትልቁ_ኪሳራ_ማለት_ይህ_ነው‼️ 

ጀነት ስፋቷ የምድርን እና የሰማያትን ያህል ሁና ላንተ በሷ ቦታ ሳይኖርህ ሲቀር...ትልቅ ኪሳራ ነው።  አዎ ትልቁ ኪሳራ ይህ ነው!!

በእለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ ቁርአንን መቅራት ካልተካተተ ይህም ትልቅ ኪሳራ ነው። 

ይህን ፅሁፍ በማሰራጨት ጓደኛህን/ሽን እንድታነቃው ይከጀላል!

Luli wedding Poems

Luli wedding Poems

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Nejat Jemal 1 shared a
Translation is not possible.

እኔ ፍልስጤማዊያን እጆግ የሚደንቀኝ ጀግንነታቸው አይደለም ! ማንም ጀግና ሊሆን ይችላልጰ!

እኔ ከነርሱ እጅግ ድንቅ የሚለኝ ሶብራቸው ነው ፅናታቸው ! የእነርሱን ፅናት ማንም ህዝብ ላይ አንብቤውም አይቼውም ሰምቼውም አላውቅም !

ቤተሰባቸው አልቀው ፅኑ ናቸው ሶብረኛ ! አካላቸው ጎድሎ እግራቸው እጃቸው ተቆርጦ አይናቸው ጠፍቶ ተስፋ ቆርጠው አይቀመጡም ! ይወጣሉ ይፋለማሉ ይታገላሉ ! ተስፋ አይቆርጡም አይደክሙም አይዝሉም ልባቸው ተሰብሮ አይልፈሰፈሱም ! መላው ምእራባዊ ሀገር ጠላታቸው ሆኖ አያለቃቅሱም ! ታግለው ቢችሉ ጥለው ይወድቃሉ እንጅ ተነፋርቀው ጠላቶቻቼውን አያስደስቱም !

ይሄ ጀግና የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ዋኢል አልደህዱህ የፍልስጤማውያን ፅናትና ሶብር አንዱ ማሳያ ነው ።

ትላንት መላ ቤተሰቡን አጣ ልጆቹን የልጅ ልጆቹን ባለቤቱን ተነጠቀ ። ቤተሰቦቹን ራሱ ሶላተል ጀናዛ አሰግዶ ኢማም ሆኖ ቀበረ ። ከዚያስ ከዚያማ ህዝቡ ትግል ላይ ነውና የቤተሰቦቹን ሀዘን ተቀምጦ ከማዘን ይልቅ ወደ ስራ ገበታው ተመለሰ ።

ታድያ ፍልስጤማዊያን የእርሱን ድምፅ በሚፈልጉበት ሰአት እንደት ለሀዘን ይቀመጥ !

ወላሂ ይሄንን ከፍልስጥኤማውያን ውጭ ማንም ያደርገው አይመስለኝም !

ምን አይነት ኢማን የው ? ምን አይነት ሶብር ነው ? ምን አይነት ኢስቲቃማ ነው ? ምን አይነት ጀሀድ ነው ? ምን አይነት ጀግንነት ነው ? ለነርሱ ብቻ ተነጥሎ የተሰጣቸው ?!!!

በመጨረሻም ተንታኞች ጋዜጠኛውን ካዩ በሗላ ያሉትን ልንገራችሁ " እነዚህን ህዝቦች ማሸነፍ አይቻልም !!!!"

#seid_mohammed_alhabeshiy

ቴሌግራም

👉 t.me/Seidsocial

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group