UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

አህባሾች ከተሳሳቱባቸው ነጥቦች መካከል ሌላኛው በአሏህ ስምና ባህሪያት በተመለከተ በግልፅ የመጡ የቁራዓንና የሀዲስ ማስረጃዎች በማዞር መተርጎሙና አዞሮ መረዳቱ ግዴታና አስፈላጊ ነው ብለው ማመናቸው ሲሆን ይህ ከቁርዓን ከሱና የወጣና ከሰሀቦችና ከታቢዕዮች እንደዚሁም ከእነርሱ በዃላ የመጡና እነርሱን የተከተሉ ሙስሊሞች መንገዳቸውን መቃወምና መንገዳቸውን ስምምነታቸው ሲሆን ሙስሊሞች ደግሞ የአሏህ ስምና ባህሪያት በቁራዓንና በሀዲስ በመጣው መልኩ ያለማንሻፈፍ፣ ያለማራቆት፣ ያለማመሳሰልና ትርጉም አልባ ሳያደርጉ ይቀበላሉ ማመኑን ግዴታ ነው ብለው ያምናሉ።

አሏህ ከማንም ይበልጥ ስለራሱ አዋቂ በመሆኑና ከፍጡራኖቹ ውስጥ ኑብዩ ከሁሉም በላይ አዋቂ በመሆናቸው ሙዕሚኖች ነብዩ ስለአሏህ የገለፁበትና ያፀደቁትለት እንደዚሁም አሏህ ስለራሱ የገለፀበትና ያፀደቀውን ነገር አያጣጥሉም ውድቅ አያደርጉም አያርቁም፣ ሌላ ትርጉም አይሰጡም፣ ትርጉም አልባ አያደርጉም፣ አይክዱም ለአሏህ ብጤን አያደርጉም።

በሁሉም ሙስሊም ላይ ማመኑ ግድ ሆኖ በቁራዓንና በሀዲስ ከመጡ ለጌታችን አሏህ ፊት እንዳለው ማመን ነው።

(በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡(26)

የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡(27)አረረህማን)

(ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገሩ ሁሉ ከእርሱ ፊቱ በቀር ጠፊ ነው፡፡ ፍርዱ የርሱ፤ ብቻ ነው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡አልቀሰስ 88)

በሶሂህ ሙስሊም እንደመጣው ነብዩ ( "የአሏህ ሂጃቡ ኑር ነው ቢገልጠው የፊቱ ጨረር ከፍጥረቶቹ አይኑ የደረሰበት ቦታ ደረስ ያቃጥላቸው ነበር።") ።

ነቢዩ በሌላ ሀዲሳቸው (ጀነቶች አሉ ከብር የተሰሩ መጠቃቀሚያቸውም ከብር የሆኑ፤ ከወርቅም የተሰሩ መጠቃቀሚያቸው ከወርቅ የሆነ በሰዎችና በጌታቸው ፊት መካከል መመልከታቸው የክብር ጋቢ ቢጨምርላቸው እንጂ።)

አህባሾች ስህተት ውስጥ እንዲወድቁ ከአደረጋቸው አንዱና ዋነኛው ነገር ለአሏህ ፊት እንዳለው ካረጋገጥን ለፍጡራኖችም ፊት ስላላቸው አሏህ ደግሞ ከማንም ጋር ስለማይመሳሰል ከፍጡራኖቹ ጋር ይመሳሰልብናል ብለው ማሰባቸው ሲሆን በስም መመሳሰል ብቻ አንድ ነው ማለት የማያስችል ጉዳይ ሲሆን ለምሳሌ ያክል ለሰው ልጅ ፊት እንደለው ሁሉ ለበሬም ፊት አለውና ለሰው ፊት አለው ካልን የሰው ልጅ ከበሬ ጋር ማመሳሰል ስለሆነ ለሰው ልጅ ፊት የለውም ብለን እንደማይባል ሁሉ ይህን እዚህ ግባ የማይባል ምክንያት ምክንያት ተደርጎ አሏህ ለራሱ አለኝ ያለውና ነብዩ ለአሏህ ያረጋገጡለትን ነገር ማስተባበል ትልቅ ስህተት ሲሆን ሙስሊም ነኝ ከሚል አካል የማይጠበቅም ተግባር ነው።

ሙስሊሞች በቁራዓንና በሀዲስ እንደመጣው ለአሏህ ከማንም ጋር የማይመሳሰል እራሱ ብቻ የሚያውቀው ፊት እንዳለው ያምናሉ ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አሏህ የሙሽሪኮች ተግባር አንድ በአንድ ከንቱና ውድቅ መሆኑን አብራርቶ ሲያበቃ ሽርክ ለባለቤቱም የሚያስከትለው አደጋም እንደዚሁ አብራርቷል፦

(አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ፡፡) አኒሳዕ ፡48

(ይህ የአላህ መምሪያ ነው፡፡ በእርሱ ከባሮቹ የሚሻውን ሰው ይመራል፡፡ ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር፡፡)አልአናም፡88

ነብዩ በሀዲሳቸውም" ከአሏህ ውጭ ሌላን ሲጣራ የሞተሰው እሱ የእሳት ነው" እንዳሉት በአሏህ ማጋራትን በተመለከተ የመጡ የቁራዓንና የሀዲስ መረጃዎች በጣም በርካታ ከመሆናቸው የተነሳ በዚህ ፅሁፍ ማካተት ከባድ ቢሆንም በጥቅሉ ሽርክ በሰው ልጅ ላይ ከሚያስከትለው ጉዳት መካካል ከአሏህ ውጭ ጉዳትም ይሁን ምንም አይነት ጥቅም የማያመጡለትን ለራሳቸው የአሏህ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው አካላትን ወይም የመያውቁትንና የማይሰሙትን አካላት በመተናነሱ ምክንያት የሰውን ልጅ ክብር ያሳጣል፣ ሰዎች ከመልካም ስራ ያዘናጋል፣ ሰዎች በመጥፎ ስራ እንዲዘወትሩ ያደርጋል፣ለሰው ልጅ የስጋትና የፍርዓት ምንጭ ይሆናል፣

የህዝቦች መለያየት ሰበብ ይሆናል፣ሰዎች በጀኸነም ውስጥ ዘውታሪ እንዲሆኑ ምክንያት ይሆናል።

አህባሾች ቁራዓንና ሀዲስ በቅጡ ባለመረዳት የሽርክ ምንነትና አደገኝነት ባለማወቅ የዲነል ኢስላም መሰረታዊ የሆነውን ተውሂድ ወደዃላ በማድረግ ተራውን አላዋቂ ማህበረሰብ ቀድሞ ባለማወቅ የሚፈፅማቸው መሰረተ ቢስ ነገሮች በአዲስ እምነት አድርገው በመያዝና እንዲመለሱበት በማድረግ የተለያዩ ከአሏህ ውጭ የሚመለክባቸው ቦታዎች አመታዊ መሰብሰቢያዎች፣ወለይዎች ብለው በሚሞግቷቸው ግለሰቦች መቃብር በመገኘት እንደዚሁም ማህበረሰቡን በመቀስቀስና ዳዕዋ በማድረግ ገንዘብ በመሰብስና በማስተባበር በነብዩ መውሊድና በወልዩቻቸው መውሊድ የተለያዩ ከእስልምና የሚስወጡ ተግባራትና ሁራፋቶች ከአሏህ ውጭ ባሉአካላት በሞተም ይሁን እሩቅ በሆነ አካል እርዳታን ይጠይቃሉ ድረስልኝ፣ ጠብቀኝ፣ነብዩን እጄን ያዙኝ፣ወንጀሌን ማረኝ ሲሉና ሲለምኑእና ሌሎች የሽርክ ተግባራትን ሲፈቅዱና እነርሱም ሲሰሩና ይስተዋላል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የአህባሾች እምነትና ስህተቶቻ

ክፍል ሁለት

ሽርክ

አህባሾች በመግቢያችን ላይ እንዳየነው እስልምና ውስጥ ከተፈጠሩ ቡድኖች ሲሆኑ ራሳቸውን አንዳንዴ ኧኽለሱና በማለት የሚሰይሙ አንዳንዴ አሻዕሪያና ማቱሪዲያ መንገድ ነው የምንከተለው የሚሉ አንዳንዴ የጥንት የመሰረቱ እስልምና የኛ ነው የሚሉ ንግግር ከንግግራቸው፣ ተግባር ከተግባራቸው እንዲሁም ንግግርና ተግባራቸው እርስ በእራሱ የሚጋጭ ቁራዓን በማንበብና በመሀፈዝ፣ የአረብኛ ቋንቋን፣ ሰዋሰውንና የተወሰኑ አመክንዮችን በመማር ሰዎች የሚያታልሉ ነገር ግን በሀቂቃ ስለቁራዓንና ሀዲስ በጥቅሉ ደግሞ የዲን ግንዛቤ የሌላቸው ቡዱኖች ሲሆን ከስህተቶቻቸው መካከል ደግሞ ሽርክ በዋነኝነት ይጠቀሳል ።

አህባሾች በኪታቦቻቸው፣ በአስተምህሮታቸውና ብዙ ጊዜ እንደሚሰማው ከአላህ ውጭ በሞተም ይሁን እሩቅ በሆነ አካል እርዳታን መጠየቅ ድረስልኝ ማለት ጠብቀኝ ማለት ነብዩን እጄን ያዙኝ ማለት ወንጀልን ይምራሉ ብሎ ማመንና እሳቸውን መለመን እና ሌሎች የሽርክ ተግባራትን ሲፈቅዱና እነርሱም ሲሰሩት ይስተዋላል።

ሽርክ ማለት አሏህ ብቻ የተነጠለበትና ለአሏህ ብቻ የሚገቡ ነገሮችን ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት ሲሆን ከተግባር ከንግግር እንደዚሁ በልብ በሚቋጥረር ነገር ይገኛል የፈፀመው ግለሰብ አሏህ የሰማይና የምድር ፈጣሪ መሆኑ፣የሚፈጥርና የሚገድል፣ የሚያበላና የሚያጠጣና ምድር የሚቆጣጣረ መሆኑን ቢያውቅም-(ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ ታድያ እንዴት ይመለሳሉ፡፡ ) አንከቡት፡61 አሏህ የሰማይና የምድር ፈጣሪ እኔ መሆኔን ካውቁ የማይጎዳቸውና የማይጠቅማቸውን መጠየቅና መለመን ተትተው የምጠቅማቸውና የምጎዳቸውን በሁሉም ነገር ቻይ ወደሆንኩት ወደ እኔ ለምን አይመለሱም? ይጠይቃልደ

የመካ ሙሽሪኮች የአለማቱ ጌታ አሏህ ብቻ መሆኑን እያወቁ በመካ ዙሪያ በቀደምት ደጋግ ናቸው ብለው በሚያስቧቸው ሰዎች ስም 360 ጣዎታትን ሰይመው ቀን ከፋፍለው ከአሏህ ጋር ያቃርቡናል ብለው ለአሏህ ብቻ የሚገባውን የአምልኮ ዘርፍ አንስተው በመስጠታቸው አልጠቀማቸውም አሏህ ተግባራቸው ሽርክ ብሎ ነው ብሎ መልሶባቸዋል፦(ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ «እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን» በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡)ዩኑስ፡18

ከአሏህ ውጭ ይጠቅመኛል ይጎዳኛል ብሎ መጥራትም ሆነ ወደ እነርሱ በተለያዩ ተግባራት መቃርብ መገዛት ወይም ማምለክ ነው።

ይህን አስመልክቶ ደግሞ አሏህ እንደዚህ ይላል፦

(ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ «እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን» በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡) ዩኑስ፡ 18

እዚህ ቦታ ላይ ይገዛሉ ነው ያለው።ሰዎች የአሏህ ሀቅ ብቻ በሆነው ነገር ከእሱ ውጭ ያሉ አካለትን ይጠራሉ ወደ እርሱም እንዲያቃርቡን በሚል ምክንያት ድረስልን፣ ጠብቀን፣ እርዳን ጉዳያችንፈፅምልን፣ ሀጃችን ሙላልን በማለት ይለምነታል፣ይዋደቃሉለታል፣ ስለት ይሳሉለታል ስለታቸው ያቀርቡለታል፣ በስሙም ሶደቃን ይሰጡለታል፣ ይወዱታል፣ ስለሚወዱትም በስሙ እንጂ አይምሉም፣ ከተማለላቸው አምነምነው ይቀበላሉ የእርሱን ቀን ብለው ቆርጠው ያከብራሉ።

የተሰጠው አካል መላይካም ቢሆን ነብይም፣ ወልይም ቢሆን ተራ ግለሰብም፣ ጠንቋይም ቢሆን ጅን፣ እንጨትም ቢሆን ድንጋይ፣ ጀበናም ቢሆን ሲኒ፣ቄጤማም ቢሆን ጉዝጋዝ ሌላም ሌላም ቢሆን ከ ቀልቡ ካንጠለጠሉበት ተግባራቸው ውድቅ እንደሆነና ይህን ተግባራቸውን አሏህ አምልኮ ብሎ ጠርቶታል ።አምልኮ ወይም ኢባዳዕ ደግሞ ከአሏህ ውጭ አሳልፎ መስጠት ሽርክ እንደሆነ ጥርጥር የለውም ይህን የፈፀመ ሰው ደግሞ ጠማማ ነው ይላል፦(እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን (ጣዖት) ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡)አህቃፍ፡5

ይህ ደግሞ በድሮ ህዝቦችና በነብዩ ዘመን የነበሩ ሙሽሪኮች እምነት ሲሆን ነብዩምና ቀደምት ነቢያቶች የተላኩበት አላማ ነው።፦( በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡.......) አነህል፡36 አሏህን በብቸኝነት ለማምለክ ነው የሰውልጅና ጅን የተፈጠረው የጂሀድ ሜዳ የተቋቋመው ልዩነቶች የተስፋፉት ደሞች የፈሰሱት ስደት የተከሰተው ይህን ከአሏህ ውጪ የሚደረጉ ተግባራትን ለማስቀረት ነው።

በዚህ ርዕስ ይቀጥላል.......

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የአህባሽ እምነትና ስህተቶቹ

መግቢያ

ምስጋና ሁሉ ለአለማቱ ጌታ ለአሏህ ይገባው የአሏህ ሰላምና ውዳሴ በነብያችን ላይ ይሁን፦

ከእስላምና ውጭ አሏህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሀይማኖት የለም።

አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው። አል ኢምራን፡19

እስልምና ማለት በየትኛውም ዘመን ለየትኛው የሰው ዘር ምንም አይነት እንከን የሌለበት ለፍጥረታት ፍትህና ለምድር የሚበጅ ለተከተለውና አጥብቆ ለያዘ ክብርና አሸናፊነትና ለሁለቱም ሀገር ስኬትና መዳን ያረጋገጠ ሀይማኖት ነው።

(አላህ እነዚያን ከእናንተ ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን እነዚያን ከእነሱ በፊት የነበሩትን እንደተካ በምድር ለይ በእርግጥ ሊተካቸው፣ ለእነሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፣ ከፍርሃታቸውም በኋላ ጸጥታን ሊለውጥላቸው ተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል፡፡ .......) አን-ኑር ፡55

(ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖራቸዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን)።

አነህል፡97

እንደዚሁም ደግሞ እሱን ከመቀበልና ከመተግበር አሏህ ትዛዝ በመራቅ ውድቅና አፀያፊ ተግባራት የፈጣሪና የፍጡር መብቶች በመዳፈር ምድርን በተለያዩ አምባገነንነት ክፋት እና ሌሎች ሰይጣናዊ አመለካከቶች በመንሰራፋታቸዉ ምክንያት የማህበረሰብ ውርደት ሽንፈትና የበታችነት የኑሮ ውድነት የበረካ ማጣት የእርስ በእርስ ጦርነት ክፍፍል ዘረኝነት አደጋዎች መብዛትና ድንገተኛ መሆን ወረርሽኝ ድርቅ የጎርፍ አደጋ የመሬት መንቀጥቀጥ የመሳሰሉ ቀውሶች እንጀሚያስከትል አሏህም በማያሻማ ቃሉ የተናገረ ነብዩም በበርካታ ሀዲሳቸው አብራርተዋል።

ለዚህም ማረጋገጫ መለኮታዊ መልዕክት በሚመጣበት ዘመን የነበሩ ማህበረሰቦች ነብዩና የእርሳቸው ባልደረቦች በአሏህ በማመናቸው መልዕክተኛውና ይዞት የመጣው መልዕክት በመቀበላቸው የታዘዙት በመታዘዝ ራቁ የተባሉትን በመራቃቸው ምክንያት የክፍለ ዘመኖች ሁሉ ምርጥ የተባለለትን የማህበረሰብ ስኬትና ስዕብና ማሳለፉ ኢብኑ መስዑድ በአስተላለፉት ዘገባ በሁለቱ ሶሂሆች እንደመጣው ነብዩ "የሰዎች ምርጥ እኔ ያለውበት ክፍለ ዘመን ነው ከዚያም ቀጥሎ ከዚያም ቀጥሎ" እንደተናገሩት እና አሏህም በቃሉ

(ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡) አተውባ፡ 100 በማለት አረጋግጦላቸዋል።

በመቀጠልም ከእዚህ ከብቻኛው እስልምና አሏህ ከሰማይ ከወረደው ህግጋት የክፈለ ዘመኖች ሁሉ ምርጥ የተባለትን ክፍለ ዘመን አልፎ ሌላ ሲመጣ የሰዎች አስተሳሳብ እና ዝንባሌ በተንስራፋ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በራሱ ከትክክለኛ እምነትና አስተምሮ እንደሚርቅ ነብያችን በንግግራቸው " ከእናንተ እድሜው የቆየ ሰው ብዙ ልዩነቶችን ያያል፤ የእኔን ሱና አጥብቃቹ በመያዝ አደራቹ" እንዳሉትም በእርካታ ልዩነቶችና አለመግባባቶች እንደዚሁም መናጋቶች በርካታ አንጃዎች በቡድንም ይሁን በግለሰቦች ደረጃ ከእዚህ ትክክለኛው አስተምሮ የወጡ ሆነው ይስተዋላሉ።

ከእነዚህ ከጥመት ቡድኖች መካካል በቅርቡ 2004 ከሊባኖስ የመጣው አገራችን በከፍተኛ ሁኔታ ከገጠር እስከ ከተማ ከተራው ማህበረሰብ እስከ ትልልቅ መሻይሆች ያተራመሰው በወቅቱ ተቃውሞ የገጠመው ከመሰረቱ ጀምሮ ከፍተኛ የሆኖ በጥመቶች በስህተቶችና በሽርክያት የተጨማለቀ ለውይይትና ለመማር በሩ ዝግ ያደረገና አሁን ላይ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች መርከዝና መስጅዶች እንደዚሁ ትልልቅ ባለሀብቶችና በተለያዩ መስሪያ ቤትች በሀላፊትና የሚሰሩ ግለሰቦችና ባለስልጣናት እንደዚሁም ደግሞ ምንም የማያውቀው ማህበረሰብ ከጎኑ በማድረግ ቁራዓንና ሀዲስ እናስተምራለን በሚል ሙስሊሙን ማህበረሰብ ሊያስቀረው እየሞከረ የነበረው በዓድ አምልኮ በአዲስ መልክ እንዲሰራፋና ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመጤ እና መሰረተ ቢስ ድርጊቶች የተሞላና ከነብዩ አስተምሮ ውጪ የሆነው የአህባሽ ቡዱን አንዱ ነው። እንደ አካባቢያችን ደግሞ በተለይ በስልጤ አብዛኛ አካባቢ እንደ ጉራጌ እነደዚሁ በስፋት ጉብሬ ጌቶ እነምር እንደ ጉመር ቦሌ ቀቡል ባድ አበኬና የተለያዩ ቦተዎች መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። አሏህ ካለ ለወደፊት የዚህን እምኑቱ የተበላሸ ቡዱን ስህተቶች በተከታታይነት የምናቀርብ ሲሆን ለትችት ለፉከራ እኔ ብቻ ልክ እንደዚሁም ለእልክ ሳይሆን በመጀመሪያ ካለብን የዲን ሀላፊነት ሌላው እነሱን ከስህተታቸው አውቀው ወደ ቁራዓንና ሱና እንዲመለሱ በመቀጠል ባለማውቅ በስህተታቸው የተሸወደው ሙስሊሙ ማህበረሰብ አውቆ አንዲጠነቀቃቸው ብቻ ነው።

በአሏህ ፈቃድ ለሚቀርቡ ለማንኛውም አስተያየት ሀሳብና ማስተካከያዎች በመማማር መልኩ፦

📞0943113278

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
mohammed neda Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group