UMMA TOKEN INVESTOR

የትዕግስት ጥልቀት

-----------------

لو كانت الدُنيا سهلة مُيسره لما كان الصبر أحد أبواب الجنة !

ይህች አለም «ዱንያ» ቀላል ብትሆን ኖሮ «ሶብር» የጀነት አንዱ በር አይሆንም ነበር።

‏قيل لأحد الصالحين :

‏ ما هو الصّبر الجميل ؟

‏قال : أن تُبتلى وقلبك يقول الحمد لله ...

አንድ መልካም ተጠየቀ፦

አስደናቂ የሆነው ትዕግስ ምንድን ነው አሉት!?

በመከራ እየታሸህ ልብህ ግን «አልሀምዱ ሊላህ»ማለቱ ነው አለ ይባላል።

«እናማ ታገስ ነው የምልህ»

Send as a message
Share on my page
Share in the group

⭕️👉 በረመዷን ዉስጥ የጅሀድ(የጥረት) አይነቶች፦

〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

ኢብኑ ረጀብ አላህ ይዘንላቸዉና እንዲህ አሉ፦

ረመዷን ዉስጥ ሙእሚን ለሆነ አካል ሁለት  የጅሀድ አይነቶች ለሱ ይሠባሠብለታል ።

⓵ኛ)) በቀን ላይ የሚገኝ የፆም ጅሀድ

⓶ኛ))በለሊቱን በመቆም(ተራዊ በመቆም) የሚገኝ የጅሀድ አይነት

በሁለቱ ጅሀዶች መካካል ሀቃቸዉን በትክክል ያስገኘ(የሠበሠበ ) የሆነ አካል እንዲሁም ሳይመረር ሳይሰላች የታገሰ የሆነ አካል  ያለምንም ገደብ ምንዳዉ ይሠጠዋል።

👉ስለዚህ ምን ያክል እረመዷንንተዘጋጅተን በጉጉት  እየጠበቅነዉ ነዉ ??

Send as a message
Share on my page
Share in the group

✍️ቁርጠኛ  ሰው ጋ ስኬት ደስታ፣ተድላና ሳቅ ሁሌም አይጠፋም። ቆራጥ የሆነ ሰው ለዱንያ እጅ አይሰጥም ይልቁንስ በአሏህ ታግዞ ሚፈልገውን ነገር ሚያገኝበትን መንገድ ሰለቸኝ  ደከመኝ ሳይል ይጓዛል........መቸም ተስፋ አይቆርጥም ህልሙ እውን ሆኖ እስካላየው ድረስ።

~

Send as a message
Share on my page
Share in the group

ጥቂት እውነታዎች ስለ ረመዷን

~

1- የረመዷን ወር ፆም ከኢስላም አምስቱ ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ምሰሶ ነው።

2- ረመዷን በኢስላማዊው አቆጣጠር 9ኛው ወር ነው።

3- የረመዷን ወር ፆም የተደነገገው በ2ኛው አመተ ሂጅራ ነው። ነብያችን ﷺ ባጠቃላይ የፆሙት 9 ረመዷን ነው።

4- ረመዷን ቁርኣን የወረደበት ወር ነው።

5- ልዩ የሆነችዋ ለይለተል ቀድር የምትገኘው በረመዷን ወር ውስጥ ነው።

6- በረመዷን የተፈፀመ ዑምራ የሐጅ ደረጃ ወይም ከነብያችን ﷺ ጋር የተፈፀመ ሐጅ ደረጃ አለው።

7- ረመዷን የጀነት በሮች የሚከፋፈቱበት፣ የጀሃነም በሮች የሚዘጋጉበት፣ ሸይጧኖች የሚጠፈሩበት ወር ነው።

8- የረመዷን ወር ከኢዕቲካፍ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው።

9- ረመዷን እንደ የበድር ድል፣ የመካ መከፈት፣ የቃዲሲያ ድል፣ የዑዛ ጣኦት መወገድ፣ ሞንጎሎች የተሸነፉበት የዐይን ጃሉት ድል፣ ወዘተ ትልልቅ ክስተቶች የተከሰቱበት ወር ነው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group

ድሀ ማለት ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን?

ከእኔ ኡመቶች ድሀ ማለት አሉ ረሱል

(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ብዙ ሰላቶችን ፣ብዙ ዘካዎችን፣ብዙ መልካም ስራዎችን ሰብስቦ የቂያም ቀን አላህ ዘንድ ይቀርባል።

ነገር ግን በሰውዬው ላይ  አንዱ ሰድቦኛል አንዱ ክብሬን አጉድፏል አንዱ ደሜን አፍስሶታል።አንዱ ደግሞ ገንዘቤን በልቶብኛል የሚል ክስ ይቀርብበታል።

ለእነዚያ ሰዎች የሰበሰበውን ሰላት፣ዘካ ባጠቃላይ በምድር የሰራቸውን መልካም ስራዎች አከፋፍሎ ይጨርሳል።

እዳውን ጨርሶ ሳይከፍል መልካም ስራው ካለቀበት ከእነሱ ወንጀል ላይ ተቀንሶ ወደ እርሱ ይጨመር እና ጀሀነም እንድገባ ይደረጋል።

ድሀ ማለት ይሄ ነው።የሚሰራው መልካም ስራ ሁሉ ለሰው

Send as a message
Share on my page
Share in the group