UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

✍️أركان الإيمان !!

⏠⏠⏠⏠⏠

የእምነት መሠረቶች!!

⏡⏡⏡⏡⏡

↳ክፍል  ⓸↲

⏟⏟⏟

    «እምነት ማለት ምን ማለት ነዉ??»

☞በአላህማመን፣በመላክቶቹ፣በመፀሐፎቹ፣በመልክተኞቹ፣በመጨረሻዉ ቀን እና ጥሩም ይሁን መጥፎ  በአላህ ዉሳኔና ፍርድ ማመን ነዉ።

☞ይህ እምነት የመልክተኞች ሁሉ መሪ የሆኑት የመደምደሚያ ነብይﷺ ያመኑበት እምነት ፣ያስተማሩት ትምህርት ነዉ። ባልደረቦቻቸዉም ንግግራቸዉ የተስማማበት፣ቃላቸዉ አንድ የሆነበት፣ መሪዎቻቸዉ የተሰበሰቡበት፣ተከታዮቹ ከቀዳሚዎቹ የወረሱት እምነትና እዉቀት ነዉ

۞በአላህ አንድነት፣በነብያችንﷺ መልክተኝነት ማመንና መመስከር በሰዎች ላይ ያለባቸዉ የመጀመሪያ ግደታ ነዉ።

«ኢማንንና አፍራሹን ለማወቅ ማስረጃዉ የአላህ ቁርአንና የመልክተኛዉﷺ ሐዲስ መሠረት ነዉ።»

⇘ኢማን፦ ክፍሎቹ(ቅርንጫፍ) ላሉት መጠሪያ ስም ሲሆን ፣ትልቅና ትንሽ አለዉ። ትልቁ ላኢላሃ ኢለሏህ ማለት ሲሆን ትንሹ ከመንገድ ላይ ሰዎችን የሚያስቸግር ነገር ማንሳት ነዉ።

⇘ኢማን፦በልብ የሚቋጠር፣በምላስ የሚነገር፣በሰዉነት አካል የሚተገበር፣አላህን በመታዘዝ የሚጨምር፣ አላህን በማመፅ የሚቀንስ፣ ድብቅም ግልጽም ሊሆን የሚችል ነዉ።

⇛ድብቅ(ስዉር)፦ ልብ ዉስጥ የተረጋጋ እምነት መሰረት ነዉ።

⇛ግልፁ(ገሀዱ)፦በምላስ ሲነገር የሚሰማ ንግግር፣በሰዉነት አካላት ሲፈፀም የሚታይ ተግባር ነዉ።

⊰የልብ ስራዎች፦ አላህን መገዛት፣ ስራን ለአላህ ብሎ ማጥራት፣ አላህን መፍራት፣ በአላህ ላይ መመካት፣አላህን ማላቅ፣ወደ አላህ መዋደቅ፣ አላህን እርዳታ መጠየቅ፣  አላህን ማክበር፣ እሱን ማፈር እና የመሳሰሉት ናቸዉ።

⭞የቀልብ  ስራ የመልካም ነገሮች ሁሉ መሰረት ነዉ።

⭞መልካም ሁሉ የሚመነጨዉ ከልብ ነዉ።

⭞የልብ ስራ በአላህ ባሪያ ላይ ሁሉ ግደታ ነዉ።

⭞ለመጨረሻ ቀን በጣም ጠቃሚ ነዉ።

⭞የልብ ስራ ለሰዉ ልጅ ለአካል ስራዉ መሰረት ነዉ።

↬በምላስ መናገር በሰዉነት አካል መተግበር ከግልጽ ኢማን ነዉ። አላህን ማስታወስ ቁርአን መቅራት ይመስል።

↬በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል

የሸሪዓ መመሪያ መከተል።

↳በምላሱ አምኖ በልቡ የከዳ ከሙናፊቆች ነዉ ምንኛ ተጎዳ።

✍️ኢንሻ አላህ ይቀጥላል......

↳↴↷↴↷↴↷↴↷↴↷↴↷↴↷↲

t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed

t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አልሃምዱሊላህ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
مدينه الح Changed her profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group