abubeker worku Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

✍ጦርነቱ አለቀ እንዴ?

ፍልስጤማዊያን ለሶስት ወራት ረሃብን ጥማትን መፈናቀልን ስደትን ህመምን የሚወዱትን ማጣትን ብሎም ሞትን በየቀኑ እየኖሩት ነው እኛ ግን ለቅሷችን ከአንድ ሳምንት አላለፈም ምክንያቱም የወንድም ህመምን መታመም የወንድም ችግርን መቸገር የሚለው ምርጡ እስልምናችን መርህ ከእኛ ርቆ ሄዷል፡፡

ግልፅ ነው እና በጉልበት የምናደርግላቸው ነገር የለም ነገር ግን በየቀኑ እነሱን አስታውሶ ዱጫ እንዲደረግላቸው ሰበብ መሆን ትልቅ ነገር ሆኖ ሳለ በሀገራቸው የሚገኙ የሁሉንም የዲን አስተማሪዎች ማህበራዊ ገፆችን ተመለከትኩ ግን ሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ ስልነዚያ ምርጦች የፃፉት ጦርነቱ በተጀመረ ሳምንት ነበር፡፡ ምነው አሁን ጦርነቱ አለቀ እንዴ? ፍልስጤም ድንበሯ የተከበረ ዜጎቿም በነፃነት የሚኖሩ ሆኑ እንዴ?

ሁኔታችንን ዞር ብለን ብናየው ለፍልስጤማዊያን ሳይሆን ለራሳችን ማልቀስ ያለብን ደረጃ ላይ ደርሰናል እነሱማ የቀን ጉዳይ እንጂ ቃል ተገብቶላቸዋል እንዲህ ያሰቃዩዋቸውን የሁዲዎች የበላይ ሆነው መልስ ይሰጧቸዋል እኛ ግን ለነዚያ ሙስሊም ወንድሞቻችን ምን ድርሻ እንደተወጣን ስንተየቅ በአቅማችን ምንችለውን ዱዓ እንኳን አድርገን ሌሎች እንዲያደርጉላቸው ሰበብ መሆን አለመቻል ውርደት ነው፡፡

ባለፉት ሶስት ወራት ወራራዋ ጽዮናዊት ሀገር በዚያች ጠባብ ምድር ላይ 65000 ቶን ቦምብ ዘንቦባታል 22,637 በላይ ላኢላሃ-ኢለላህ ብለው ያመኑ ሙስሊም ወንድሞቻችን ያውም ሴት እና ህፃናት ሞተውባታል 57,296 በላይ የሚሆኑ ጉዳት ደርሶባቸዋል 7,000 በላይ ሰዎች የገቡበት አልታወቀም፡፡ ታዲያ ጦርነቱ አለቀ እንዴ? ፍልስጤምስ ሰላም ሆናለች እንዴ?

በጋዛ እና በሁሉም የፍልስጤም ምድር የሚገኙ ሙጃሂዶች ይህን መሪር ትግላቸውን አሁንም ቀጥለዋል በእያንዳንዱ ደቂቃ የወራሪውን ጦር እያደኑ እያጠቁ ነው እስራኤልም ይፋ ባታደርገውም እጂግ ከባድ የሆነ ፈተና ውስጥ ገብታ መውጫው ጠፍቶባታል፡፡ ጦርነቱ አላለቀም ፍልስጤምም ገና ትግል ላይ ነች፡፡

እስኪ ሼር አድርጉት ሁሉም ቢነቃ

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እንግሊዝ በተቃውሞ እየተናጠች ነው !

የእንግሊዝ ፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ ስብሰባ ጠርቷል !

በእንግሊዝ የሚደረገው የፍልስጤማውያን የድጋፍ ሰልፍ የእንግሊዝ መንግስትን ወንበር እየነቀነቀ ነው። ትውልደ ህንዳዊው ሪሺ ሱናክ የሚመራው የእንግሊዝ መንግስት ለእስራኤል የማያወላውል ድጋፍ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክም እስራኤል ድረስ በመሄድ "ብቻሽን አይደለሽም እንግሊዝ ከጎንሽ አለች" ብሎ የመሰረተቻት ሀገር አሁንም እንደማትተዋት ገልፆ ወደ እንግሊዝ ሲመለስ ግን የገጠመው የእንግሊዝ ህዝብ ቁጣን ነው።

ለንደን የፍልስጤም ከተማ እየመሰለች ነው። እናም ነገ እጅግ ከባድ የሆነ የፍልስጤማውያን የድጋፍ ስልፍ በመጠራቱ መንግስት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወድቋል።

በመሆኑም የእንግሊዝ መንግስት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስቸኳይ የፓርላማ ስብሰባ የጠራ ሲሆን በፍልስጤም እና በእስራኤል ላይ ያለውን አቋም እንደሚያሳውቅም ገልጿል። እናም መንግስት ለእንግሊዝ ህዝብ ባስተላለፈው ጥሪ የነገን ብቻ እንዲጠብቁ እስከ ውሳኔው ድረስ በትእግስት እንዲጠብቁ ተማፅኗል።

እንግሊዝ እየተነሳባት ባለው የህዝብ ቁጣ ከአቋማ እየተንሸራተተች ሲሆን የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ድምፀ ተአቅቦ ማድረጓ ይታወቃል።

ፍልስጤሞች የምእራቡን አለም ህዝብ እያሸነፉ ሙምጣታቸውና ምእራባውያን ህዝቦች ለእስራኤሎች ያላቸው ጥላቻ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ እስራኤልን እና አሜሪካን በከፍተኛ ሁኔታ ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል።

መረጃው ሌሎች ጋር እንድደርስ ሸር ማድረጋችሁን አትርሱ።

💯ተጨማሪ መረጃ እንድደርስዎ ቻናላችንን Join በማድረግ ይቀላቀሉ

👇👇👇

ቴሌግራም:–

https://t.me/Brathersmedia

👇👇👇

ኡማ ላይፍ:–

https://ummalife.com/Brathersmedia

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ምዕራቡ አለም በብሪቴይን እርግዝና በፈረንሳይ አዋላጅነት በጥቅመኛ አረቦች አጨብጫቢነት የወለዷትን የግፍና የበደል ልጅ መጠበቅ ላይ መተባበር መያዛቸው ብዙ አያስገርምም። ታማኝነት አልባ፣ የሁለት ሚዛን ባለቤት ከሆኑት የግፍ መሪዎችና ልሂቃን ስብስብ ከዚህ የተለየ መጠበቅም የዋህነት ነው። ቅሉ ሁሉም ነገር ማብቂያ አለው፤ ሁሉም ነገር መጠናቀቂያ አለው።

★ ማብቂያውም ፍትህን ለተነፈጉት ሁሉ ብርሃን መሆኑ ነው። ወላዱም፣ ያዋለደውም፣ ያጨበጨበውም፣ የተወለደውም የበደልና የግፍ ልጅም መዋረዳቸው አይቀርም። በነፍሶቻቸው ውስጥ የነገቡት የበላይነትና ሁሉን አድራጊነት መንፈስ ቅዠት መሆኑ አይቀርም። የአላህ ቃል እንዲህ ይላል።

« إن الذين كفروا ينفقون أموالهم ليصدوا عن سبيل الله فسينفقونها ثم تكون عليهم حسرة ثم يغلبون… »

« እነዚያ የካዱት ሰዎች ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘባቸውን ያወጣሉ። በእርግጥም ያወጣሉ። (ካወጡም በኃላ) ፀፀት ትሆንባቸዋለች። ከዚያም ይሸነፋሉ። የካዱት ሰዎች ወደ ገሀነምም ይሰበሰባሉ።»

እንዲህም ይላል።

« …عسى الله أن يكف بأس الذين كفروا والله أشد بأسا وأشد تنكيلا »

« … አላህ የካዱትን ሰዎች ኃይል ሊከለክልልህ ይከጀላል (ይከለክልልሃል)። አላህም በኃይል ሲይዝ የበረታ፤ ቅጣቱም እጅግ ጠንካራ ነው። »

★ በተቃራኒው በበደል ውስጥ በትግልና በትእግስት፣ በትእግስትና በትግል ያለፉት ሁሉ የአላህ እርዳታ እየጨመረላቸው፤ እዝነቱንና እገዛውን እያሰፋላቸው፤ የድልን ካባ እንደሚያጎናፅፋቸው እርግጥ ነው።

ለተወዳጁ መልእክተኛው (ሰዐወ) አላህ እንዲህ ይላቸዋል።

« …فسيكفيكهم الله وهو السميع العليم »

« … ከእነርሱም (ከከሃዲያኑ) አላህ ይበቃሃል። እርሱ ሰሚና ዐዋቂው ነው። »

እንዲህም ይላል።

« أليس الله بكاف عبده ويخوفونك بالذين من دونه… »

« አላህ ለባሪያው በቂ አይደለምን? ከእርሱ ውጪ (በታች በሆኑት ጣኦቶቻቸው) በሆኑት ነገሮች ያስፈራሩሃል። … »

اللهم افرغ على المجاهدين الصابرين الصبر وانصرهم على الظالمين الغاصبين

#الأقصى حياتنا

والموت في سبيلها اسمى امانينا

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Alhamdulilah for every thing

Send as a message
Share on my page
Share in the group