Translation is not possible.

✍ጦርነቱ አለቀ እንዴ?

ፍልስጤማዊያን ለሶስት ወራት ረሃብን ጥማትን መፈናቀልን ስደትን ህመምን የሚወዱትን ማጣትን ብሎም ሞትን በየቀኑ እየኖሩት ነው እኛ ግን ለቅሷችን ከአንድ ሳምንት አላለፈም ምክንያቱም የወንድም ህመምን መታመም የወንድም ችግርን መቸገር የሚለው ምርጡ እስልምናችን መርህ ከእኛ ርቆ ሄዷል፡፡

ግልፅ ነው እና በጉልበት የምናደርግላቸው ነገር የለም ነገር ግን በየቀኑ እነሱን አስታውሶ ዱጫ እንዲደረግላቸው ሰበብ መሆን ትልቅ ነገር ሆኖ ሳለ በሀገራቸው የሚገኙ የሁሉንም የዲን አስተማሪዎች ማህበራዊ ገፆችን ተመለከትኩ ግን ሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ ስልነዚያ ምርጦች የፃፉት ጦርነቱ በተጀመረ ሳምንት ነበር፡፡ ምነው አሁን ጦርነቱ አለቀ እንዴ? ፍልስጤም ድንበሯ የተከበረ ዜጎቿም በነፃነት የሚኖሩ ሆኑ እንዴ?

ሁኔታችንን ዞር ብለን ብናየው ለፍልስጤማዊያን ሳይሆን ለራሳችን ማልቀስ ያለብን ደረጃ ላይ ደርሰናል እነሱማ የቀን ጉዳይ እንጂ ቃል ተገብቶላቸዋል እንዲህ ያሰቃዩዋቸውን የሁዲዎች የበላይ ሆነው መልስ ይሰጧቸዋል እኛ ግን ለነዚያ ሙስሊም ወንድሞቻችን ምን ድርሻ እንደተወጣን ስንተየቅ በአቅማችን ምንችለውን ዱዓ እንኳን አድርገን ሌሎች እንዲያደርጉላቸው ሰበብ መሆን አለመቻል ውርደት ነው፡፡

ባለፉት ሶስት ወራት ወራራዋ ጽዮናዊት ሀገር በዚያች ጠባብ ምድር ላይ 65000 ቶን ቦምብ ዘንቦባታል 22,637 በላይ ላኢላሃ-ኢለላህ ብለው ያመኑ ሙስሊም ወንድሞቻችን ያውም ሴት እና ህፃናት ሞተውባታል 57,296 በላይ የሚሆኑ ጉዳት ደርሶባቸዋል 7,000 በላይ ሰዎች የገቡበት አልታወቀም፡፡ ታዲያ ጦርነቱ አለቀ እንዴ? ፍልስጤምስ ሰላም ሆናለች እንዴ?

በጋዛ እና በሁሉም የፍልስጤም ምድር የሚገኙ ሙጃሂዶች ይህን መሪር ትግላቸውን አሁንም ቀጥለዋል በእያንዳንዱ ደቂቃ የወራሪውን ጦር እያደኑ እያጠቁ ነው እስራኤልም ይፋ ባታደርገውም እጂግ ከባድ የሆነ ፈተና ውስጥ ገብታ መውጫው ጠፍቶባታል፡፡ ጦርነቱ አላለቀም ፍልስጤምም ገና ትግል ላይ ነች፡፡

እስኪ ሼር አድርጉት ሁሉም ቢነቃ

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group