UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

💜 አስር ብስራቶች ፈጅር ሶላትን በጀማዓ ለሰገደ ሰው ።

እነዚህ ብስራቶችን አንብቦ የፈጅር ሶላት የሚያመልጠው ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም❗

▪ ብስራት ①

👉🏼 ለቂያም ለት ሙሉ ብርሃን

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ በጨለማ ወደ መስጂዶች የሚሄዱትን ለቂያም ለት ሙሉ ብርሃን እንደሚኖራቸው አበስራቸው። }

▪ብስራት ②

👉🏼 የፈጅር ሁለት ሱና ሶላቶች ከአዱንያና በውስጧ ካለው ነገር ይበልጣሉ።

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ የፈጅር ሁለት ሱና ሶላቶች ከአዱንያና በውስጧ ካለው ነገር ይበልጣሉ። }

▪ብስራት ③

👉🏼 ወደ መስጊድ በሚራመደው ልክ ምንዳ ይፃፍለታል።

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ ከቤቱ ወደ መስጂድ የወጣ ሰው… በሚራመደው እያንዳንዷ እርምጃ አስራ አጅር ይፃፍለታል… }

▪ብስራት ④

👉🏼 የመላኢኮች ምስክርነት

አሏህ እንዲህ ብለሏል:

{ ሶላትን ከፀሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፡፡ የጎህንም ሶላት ስገድ፡፡ የጎህ ሶላት (መላእክት) የሚጣዱት ነውና፡፡ }

▪ብስራት ⑤

👉🏼 ከእሳት መዳን

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ ከፀሐይ መውጣትና መግባት በፊት– ማለትም ፈጅርና አሱር – የሰገደ ሰው ጀሀነም አይገባም። }

▪ብስራት ⑥

👉🏼 አሏህን ማየት

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ ጨረቃዋ ሙሉ በነበረችበር አንድ ለሊት ነቢዩ (ሰ ዐ ወ) ዘንድ ነበርን። ነቢዩ (ሰ ዐ ወ) ጨረቃዋን ተመለከቱና እንዲህ አሉ: "እናንተ ይህን ጨረቃ ሳትጨናነቁ እንደምታዩት አሏህንም ታዩታላችሁ… ከቻላችሁ ከፀሐይ መውጣትና መግባት በፊት ባለው ሶላት አትሸነፉ። ማለትም ፈጅርና አሱር። }

▪ብስራት ⑦

👉🏼 የለሊት ሶላት ምንዳ

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ ኢሻ ሶላትን በጀመዓ የሰገደ የለሊቱን ግማሽ እንደቆመ ይቆጠራል። ፈጅርን በጀማዓ የሰገደ ሰው ደግሞ ለሊቱን ሙሉ በጀመዓ እንደሰገደ ይቆጠራል። }

▪ብስራት ⑧ 

👉🏼 የመላኢካዎች ዱዓ

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ ፈጅር ሶላት ሰግዶ በመስገጃው ላይ ቁጭ ያለ መላኢካዎች በርሱ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ። የነርሱ ሰለዋት: አሏህ ሆይ ማረው አሏህ ሆይ እዘንለት ነው። }

▪ብስራት ⑨

👉🏼 የሐጅና የዑምራ ምንዳ

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ የፈጅር ሶላትን በጀማዓ የሰገደና ፀሐይ እስትወጣ ቁጭ ብሎ ዚክር ያደረገ ከዚያ ሁለት ረከዓ የሰገደ ልክ እንደ ሙሉ ሙሉ ሙሉ የሐጅና ዑምራ ምንዳ ይሆንለታል።}

▪ብስራት ⑩

👉🏼 በአሏህ ከለላና ጥበቃ ስር

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

{ ፈጅር ሶላት የሰገደ ሰው በአሏህ ከለላ ስር ነው። በአሏህ ከለላ ስር ያለን ሰው ነክታችሁ አሏህ እንዳያሳድዳችሁ። አሏህ ያሳደደው ሰው ይደርስበትና ጀሀነም ውስጥ ይደፋዋል። }

አሏህ ሆይ የፈጅር ሶላትን አግራልን ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
abu niema nursefa Mohammed Сhanged his profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group