በቁርኣን አንዱ በሌላው ድምፅን ከፍ ማድረግ
~
ሶላት ስንሰግድ አጠገባችን ሌላ ሰጋጅ ካለ እንዳንወሰውስ ድምፃችንን ዝቅ ልናደርግ ይገባል። ልክ እንዲሁ መስጂድ ውስጥ - ለምሳሌ ጁሙዐ ቀን ሊሆን ይችላል - ቁርኣን ስንቀራ ሌሎችን በሚረብሽ መጠን ድምፃችንከፍ ያለ መሆን የለበትም። ነብያችን ﷺ በአንድ ወቅት ኢዕቲካፍ ላይ ነበሩ። ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየቀሩ ሰሟቸው። መጋረጃቸውን ገለጥ አድርገው እንዲህ አሉ፦
أَلَا إِنَّ كُلَّكُمْ مُنَاجٍ رَبَّهُ، فَلَا يُؤْذِيَنَّ بَعْضُكُمْ بَعْضًا، وَلَا يَرْفَعْ بَعْضُكُمْ عَلَى بَعْضٍ فِي الْقِرَاءَةِ ، أَوْ قَالَ: فِي الصَّلَاةِ
"ንቁ! እያንዳንዳችሁ ከጌታው ጋር ነው እየተንሾካሾከ ያለው። ስለዚህ አንዳችሁ ሌላውን አያስቸግር። ከፊላችሁ በከፊሉ ላይ በቂራኣ - ወይም በሶላት - አይጩህ። [አቡ ዳውድ፡ 1332]
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፦
أما إن أحدكم إذا قام في الصلاة، فإنه يناجي ربه، فليعلم أحدكم ما يناجي ربه، ولا يجهر بعضكم على بعض بالقراءة في الصلاة
"አንዳችሁ ለሶላት ሲቆም ከጌታው ጋር ነው የሚንሾካሾከው። ስለሆነም ከጌታው ጋር የሚንሾካሾክበትን ይወቅ። ከፊላችሁ በከፊሉ ላይ በሶላት ውስጥ በቁርኣን አይጩህ።" [ሙስነድ አሕመድ፡ 11896]
ስለዚህ ሌሎች ሰጋጆች ባሉበት ጀማዐ ሶላት ላይ ያለፈንን ስንመልስ፣ ወይም ካጠገባችን ሌሎች ቁርኣን የሚቀሩ ሲኖሩ ድምፃችንን ዝቅ በማድረግ ልንቀራ ይገባል። ጁሙዐን እየጠበቁ በድምፅ ማጉያ ቁርኣንን ከመስጂድ መክፈትም እንዲሁ ተገቢ አይደለም።
ልክ እንዲሁ በየቤታችን ሆነን ሶላት የሚሰግድ ባለበት እየተንጫጩ ማውራትም የተለመደ ነው። ይህም መታረም ያለበት ነው። በቁርኣን አንዱ በሌላው ላይ እንዲጮህ ካልተፈቀደ በሌላ ወሬ፣ ያውም ሶላት ላይ ያለን አካል መወስወስ ግልፅ የሆነ ጥፋት ነው። ለሶላት ክብር ሊኖረን ይገባል። ልጆቻችንንም እንዲሁ አደብ ማስተማር አለብን።
Ibnu Munewor
=
* የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
* የዋትሳፕ ቻናል፦
https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
* ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL

https://whatsapp.com/channel/0....029VaA3X1e5kg7BlsJbo
* ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Ibnu.....Munewor?mibextid=ZbW