ሚዛን!
~
የትኛውንም ብሄር በሆኑ አባላቱ ጥፋት በጅምላ አትወርፍ። እራስህ ላይ ቢሆን የማትፈልገውን ነገር ሌሎች ላይ አትለጥፍ። በራስህ ሞኞች ሰበብ ዘርህ እንዲሰደብ እንደማትፈልገው ድፍን ብሄርን ባልዋለበት አትፈርጅ፤ በሌለበት አትክሰስ። በወቅታዊ የፖለቲካ ግለት ተነሳስተህ በጅምላ ሰዎችን አታጥቃ። መጠቃታቸውንም አትደግፍ። ባንተ ብሄር ላይ ቢቀለድ የምትከፋ ሆነህ ሳለ በሌሎች ላይ አትቀልድ፣ አታሰራጭ።
የሆኑ ነውረኞች ዘርህን ስለ ሰደቡ የነሱን ዘር አትሳደብ። ከረከሱ ጋር ከምትረክስ በማስተዋልህ ከፍ በልና ከነሱ ተሽለህ ተገኝ። ስትወድም፣ ስትጠላም፣ ሲከፋህም፣ ሲደላህም፣ በራስህም ይሁን በሌሎች ብሄር ጉዳይ ላይ ሚዛን አትሳት፣ ፍትህ አትልቀቅ። والانصاف خير الأوصاف
በየትኛውም ጉዳይ ላይ በማንኛውም ሁኔታ ሃይማኖትህን አስቀድም። ኢስላም የማይቀበለውን ነገር ለመጋፈጥ የብሄርና የፖለቲካ አሰላለፍ አትመልከት። ሌሎች ሲፈፅሙት ጥፋት የሆነ ተግባር ያንተ ብሄር ሰዎች ሲፈፅሙት ፅድቅ አይሆንም። ሌላ ብሄር ውስጥ ያሉ ሰዎች የፈፀሙትን ጥፋት እያብጠለጠልክ ያንተ ብሄር ሰዎች ሲፈፅሙት ለመከላከል አትነሳ። እፍረት ይኑርህ እንጂ። ህሊናህን አክብር እንጂ። ደግሞም እወቅ! ሌሎች ላይ የምታየውን ጥፋት ለመኮነን ዘራቸውን አትነካካ።
ደግሞም ንቃ! ለየትኛውም የፖለቲካ ኃይል ደጋፊ ብትሆን የእምነትህን እሴቶች እስከ መዋጋት፣ ወይም እምነትህን ለሚያራክሱ አካላት እስከመወገን ድረስ አትውረድ። "ሞኝ አህያ ጅብ ይሸኛል" ይላል ብሂሉ። ለሞኝነትህ ለከት አብጅለት።
የፖለቲካ ጥላቻና ውግንና አቅልህን አያስትህ። የ'ውር ድንብር ጥላቻና ውዴታ ውስጥ አይክተትህ። ኋላ ትጎዳለህ። ድንገት ያስተዋልክ እለት ታፍራለህ። ምናልባት ካስተዋልክ!
Ibnu Munewor
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
* ኡማ ላይፍ፦ https://ummalife.com/IbnuMunewor
ሚዛን!
~
የትኛውንም ብሄር በሆኑ አባላቱ ጥፋት በጅምላ አትወርፍ። እራስህ ላይ ቢሆን የማትፈልገውን ነገር ሌሎች ላይ አትለጥፍ። በራስህ ሞኞች ሰበብ ዘርህ እንዲሰደብ እንደማትፈልገው ድፍን ብሄርን ባልዋለበት አትፈርጅ፤ በሌለበት አትክሰስ። በወቅታዊ የፖለቲካ ግለት ተነሳስተህ በጅምላ ሰዎችን አታጥቃ። መጠቃታቸውንም አትደግፍ። ባንተ ብሄር ላይ ቢቀለድ የምትከፋ ሆነህ ሳለ በሌሎች ላይ አትቀልድ፣ አታሰራጭ።
የሆኑ ነውረኞች ዘርህን ስለ ሰደቡ የነሱን ዘር አትሳደብ። ከረከሱ ጋር ከምትረክስ በማስተዋልህ ከፍ በልና ከነሱ ተሽለህ ተገኝ። ስትወድም፣ ስትጠላም፣ ሲከፋህም፣ ሲደላህም፣ በራስህም ይሁን በሌሎች ብሄር ጉዳይ ላይ ሚዛን አትሳት፣ ፍትህ አትልቀቅ። والانصاف خير الأوصاف
በየትኛውም ጉዳይ ላይ በማንኛውም ሁኔታ ሃይማኖትህን አስቀድም። ኢስላም የማይቀበለውን ነገር ለመጋፈጥ የብሄርና የፖለቲካ አሰላለፍ አትመልከት። ሌሎች ሲፈፅሙት ጥፋት የሆነ ተግባር ያንተ ብሄር ሰዎች ሲፈፅሙት ፅድቅ አይሆንም። ሌላ ብሄር ውስጥ ያሉ ሰዎች የፈፀሙትን ጥፋት እያብጠለጠልክ ያንተ ብሄር ሰዎች ሲፈፅሙት ለመከላከል አትነሳ። እፍረት ይኑርህ እንጂ። ህሊናህን አክብር እንጂ። ደግሞም እወቅ! ሌሎች ላይ የምታየውን ጥፋት ለመኮነን ዘራቸውን አትነካካ።
ደግሞም ንቃ! ለየትኛውም የፖለቲካ ኃይል ደጋፊ ብትሆን የእምነትህን እሴቶች እስከ መዋጋት፣ ወይም እምነትህን ለሚያራክሱ አካላት እስከመወገን ድረስ አትውረድ። "ሞኝ አህያ ጅብ ይሸኛል" ይላል ብሂሉ። ለሞኝነትህ ለከት አብጅለት።
የፖለቲካ ጥላቻና ውግንና አቅልህን አያስትህ። የ'ውር ድንብር ጥላቻና ውዴታ ውስጥ አይክተትህ። ኋላ ትጎዳለህ። ድንገት ያስተዋልክ እለት ታፍራለህ። ምናልባት ካስተዋልክ!
Ibnu Munewor
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.....Munewor?mibextid=ZbW
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0....029VaA3X1e5kg7BlsJbo