Translation is not possible.
ነገ ሐሙስ
✨ዙልሒጃ 9ኛው ቀን (ዐረፋ )
✨የዓረፋን_ቀን_መፆም
የዐረፋ ቀን | ዱዓእ ተቀባይነት ሊያገኝበት ከሚችልባቸው ቀናት መካከል አንዱ እና ልዩ ቀን ነው:: መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ በማለት የዓረፋ ቀን ዱዓእ ገልፀዋል:-
“ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓእ ነው::”
ስለሆነም በዚህ ቀን ለራሳችን ፣ ለወላጆቻችን ፣ ለልጆቻችን ፣ ለባለቤቶቻችን ፣ ለቅርብ ዘመዶቻችን ፣ በኛ ላይ ሀቅ ላላቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ሁሉ በርትተን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።
አቡ–ቀታዳ (ረዲየላሁ ዓንሁ) እንዳስተላለፉት:‐
«የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ እለተ #ዓረፋ_ጾም ተጠየቁ ፤ እሳቸውም "ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ" አሉ።»
Send as a message
Share on my page
Share in the group