UMMA TOKEN INVESTOR

Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

አንድ ስመ-ጥር ባለ ስልጣንና ባለሀብት ያለህበትን ጭንቅና መከራ ተመልክቶ #አብሽር እኔ አለሁልህ ቢልህ ምን ይሰማሃል ? ደስታ አይደል ?!

እንግዲያውስ የመስጠትም የመንሳትም ስልጣን ፣ የመፍጠርም የማጥፋትም ኃይል  ፣ የመሸለምም የመቅጣትም መብት ..... ያለው አሏህ ችግርህን በሚገባ ያውቃል , ብሶትህንም በሚገባ ይረዳል እናም  እንዲህ ይልሃል

وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ ۝

" ታጋሾችንም አብስር "

አሏህ ታገስ ሲልህ ባልጠበቅከው መልኩና እጅግ በትልቁ ሊያስደስትህ ነውና ታገስ!!!

نقل

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

‎يا واقف عند قبري

‎لا تتعجب من امري

‎بالأمس كنت مثلك

‎وغدا تكون مثلي

እቀብሬ የቆምከው ሰው ሆይ

በነገሬ መገረምህ ምነው?

ትናንት እንዳንተው ነበርኩ

ነገ እኔን መሆንህ እርግጥ ነው "

የተራ ጉዳይ እንጂ ከዛ የሚቀር የለም..

እናም..

መሞታችን ሳይሆን አሟሟታችን ነው አሳሳቢው!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

የሃይስኩል ተማሪ እያለች ነበር ኒቃብ የለበሠችው፡፡ ያውም በአንድ ቀን ደዕዋ፡፡ ቀኑና ጊዜውን ለማስታወስ በትዝታ ወደኋላ ርቃ ሄደች፡፡ ዕለቱ ጁሙዓ ነበር፡፡ ከሶላት በኋላ ስለ ሒጃብ ደዕዋ ያደረገው ኡስታዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፤ በተለይ ሴቶች ጆሮ እንዲሠጡት ይወተውታል ‹ሴት ልጅ ዐውራ ናት፣ ፈፅሞ ፎቷ መታየት የለባትም፣ ፊት ያልተሸፈነ ምን ሊሸፈን!፣ ኒቃብ ግዴታ ነው፤ ሴቶቻችን አላህን ፍሩ፣ ኒቃብ ልበሱ፤ ወላጆችም እንድታለብሱ …› እያለ ይመክራል፡፡

እዚያው እያለች ወሠነች፡፡ ወደ ቤቷ ገባች፡፡ ለወላጆቿ ነገረች፡፡ ኒቃብ መልበስ አለብኝ አለች፡፡ ከብዙ ክርክር በኋላ አሳመነቻቸው፡፡ ትምህርት ብትጨርስም ዉጤት አልመጣላትም፡፡ በግል ኮሌጅ አካውንቲንግ ተማረች፡፡ ዉጤቷ ጥሩ ነበር፡፡ ሥራ ፈለገች፡፡ ግና በኒቃቧ ምክንያት ተገፋች፡፡ ተቆጨች፣ ተናደደች ….

ዕድሜዋ ሲገፋ ይታወቃታል፡፡ ከአሥራ ቤት ወጥቶ ሀያ ገብቶ ወደ ሰላሳም ተጠግቷል፡፡ በዚህ በኩል የሥራ ማጣት፣ በወዲያ ከትዳር መዘግየት አስጨነቃት፡፡ ወንድ አትቀርብም፤ ወንዶችም ሊቀርቧት ይፈራሉ፡፡ የለበሠችው በልጅነት በመሆኑ ቀይ ትሁን ጥቁር፤ ቆንጆ ትሁን መልከ ጥፉ በአካል አያውቋትም፡፡ ብቻ በሩቅ ይሸሷታል፡፡ አንድም ኢማናቸውን ንቀው አሊያም ታጠብቃለች፣ አክራሪ ናት ብለው በመፍራት፡፡ ሁለት ፈተና በአንድ ጊዜ ወጥሮ ያዛት፡፡ የለፋችበት ትምህርት ቆጫት፤ የምትመኘው ትዳር ራቃት፡፡ ብዙ ጓደኞቿ ሥራ አገኙ፡፡ በዕድሜ ታናሾቿ ተራ በተራ አገቡ፡፡ ሒጃብን ለሥሙ ብቻ ጣል የሚያደርጉት ጥሩ ትዳር ያዙ፡፡

አላህ እሱን ለማይፈሩት ነው እንዴ የሚያደላው! አለች፡፡ ጥሩዎች ሲጎዱ መጥፎዎች ሲጠቀሙ አየች፡፡ ታዘበች፣ አሰበች፡፡ ኢማኗ እየደከመ መጣ፣ በራስ መተማመኗ ቀነሰ፣ ሌሎች የሚያወሩላት ወሬ ሸረሸራት፡፡ ከራሷ ጋር ታገለች፡፡ ኡስታዞችንና ዓሊሞችን ጠየቀች፡፡ ‹ልጅ ሆኜ ስለ ዲን ብዙም ሳላውቅ ነበር በችኮላ የለበስኩት፤ አሁን ማውለቅ እችላለሁ ?› አለች፡፡ አውልቂ የሚላት ጠፋ፡፡ ወደ ራሷ ተመለሰች፡፡ ከሁለት ያጣች እንደሆነች ታወቃት፡፡ ኒቃብ ከሥራም ከትዳርም እየከለከላት እንደሆነ ሸይጧን ሹክ አላት፡፡ ደስ እያላት ባለመልበሷ ምክንያት ምንም አጅር እንደማታገኝም ነገራት፡፡

ወረደች፣ ተጠራጠረች፣ ግራ ታጋባች …. በጥርጣሬ ዉስጥ ከምዋልል ለምን አላወልቀውም አለች፡፡ ከብዙ ትግል በኋላ አወለቀች፡፡ የመጀመሪያ ሰሞን እርቃኗን የሆነች ያህል ተሰማት፡፡ ግና አንድ አድርጌዋለሁ ብላ ራሷን አበረታታች፡፡ ያዩዋትና የሚያውቋት ደነገጡ፡፡ እሷ ናት ወይስ ሌላ? አሉ፡፡ እሷነቷን ሲያረጋግጡ ብዙ አወሩ፣ ተሳለቁ በወሬያቸው ይበልጥ ባሰባት፣ እልህ ተጋባች፡፡ በዚያው ሄደች፡፡ ወደ ቀደመ ቦታዋ አልተመለሠችም፡፡ እሷ የድሮ ኒቃቧን ረሣች፡፡ እነርሱም አውርተው ሲደክሙ ዘነጓት፡፡

ኒቃብ የለበስሽ እህቴ ሆይ!

1- ኒቃብ ስትለብሺ ዒባዳ መሆኑን አስቢ፤ ኒያሽ ቀጥ ያለና የተስተካከለ ይሁን፣

2- ጊዜው ቢረዝምም፣ ቀኑ ቢቆይም አላህ መልካም ባሮቹን ጥሎ አይጥልም፡፡

3- ኒቃብ በማውለቅና ፎቶ በመለጠፍ የሚገኝ ትዳር የለም፤

4- በአላህ መመካትሽ እንደ ወፍ ይሁን፣ ባዶ ሆዷን ወጥታ ሆዷን ሞልታ ትገባለች፣

5- በአላህ አምኛለሁ በይና ቀጥ በይ፣

6- ጥሩ መጨረሻ አላህን ለሚፈሩና ለጥንቁቆች ነው፡፡

7- አላህ በመልካም ነገር ላይ ፅናት ይስጠን፡፡

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

Ameen

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

ከቆሻሻ ቦታ ላይ ምግብ አንስተው መብላት የሚያቆሙት ቆሻሾች የድሆችን ሃቅ መብላት ሲያቆሙ ነው **.. !

pray for palestine 💜

Send as a message
Share on my page
Share in the group