UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

የዑለማኦቹ መልስ

አንድ ሰው ኢብኑ አልጀውዚ ረሒመሁሏህ ዘንድ መጣና ‹ተስቢሕ ላድርግ /አላህን ላወድስ/ ፤ ወይንስ ኢስቲግፋር /ምህረት/ ልጠይቅ የቱ ይሻለኛል?› አላቸው፡፡ እርሣቸውም ‹አንድ ሰው ልብሱ የቆሸሸ እንደሆነ ሽቶ ከመቀባት ይልቅ ማጠቡ ይሻለዋል፡፡› አሉት፡፡ (ከአላህ ምህረት መጠየቅን አስቀድም፡፡) ማለታቸው ነው፡፡

ኢማሙ አሽሻፊዒይ ‹ዓሊም የማያውቀውን ጥያቄ ይጠየቃል ወይ?› ተብለው ተጠየቁ፡፡ እርሣቸውም ‹ዓሊም የሚያውቀውንም የማያውቀውንም ሊጠየቅ ይችላል፡፡ የሚያውቀውን ይመልሣል፤ የማያውቀውን ይማራል፤ ጃሂል ግን ሲጠየቅ ይቆጣል፤ ለመማርም ዝግጁ አይደለም፡፡› አሉ፡፡

ኢማም አሽሻፊዕይ ‹ በእድሜ ወጣት ሆነው ሣለ ለምን ምርኩዝ ይይዛሉ?› ተብለው ተጠየቁ፡፡ እርሣቸውም ‹ መንገደኛ መሆኔን መርሣት እንደሌለብኝ እራሴን ለማስታወስ፡፡› ብለው መለሱ፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ለዒልም ተማሪዎች ጉርሻ

~

ኪታብ ከሚቀሩ ተማሪዎች ውስጥ ብዙዎቹ ለልፋታቸው የሚመጥን በቂ ግንዛቤ አይጨብጡም። ከነዚህ በተቃራኒ ደግሞ በቂራአት ማእድ ላይ ያላቸው ቆይታ አነስተኛ ሆኖ የተሻለ የሚጠቀሙ አሉ። ልዩነቱ ከምን የመነጨ ነው? ለዚህ ልዩነት ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ አድምቶ አለመቅራት የሚያመጣው ክፍተት ነው። የብዙ ተማሪዎች አያያዝ የለብ ለብ ነው። አንዱን ኪታብ ጥንቅቅ አድርገን ሳንይዝ ከፍ ወዳለው ለመግባት ያለን ጉጉት ብዙ ቀርተናል የሚል ጉጉታችንን ከማርካት ባለፈ ብስለት እንዳይኖረን ሊያደርገን ይችላል።

ይህንን ክፍተታችንን ለመድፈን ከሚያግዙ መንገዶች ውስጥ ሶስቱን ላንሳ፦

1- ቃላት ለቀማ

2- መልእክቱን መጨበጥ

3- ነጠብጣቦችን ማገናኘት

ላብራራቸው።

1- ቃላት ለቀማ፦

ከምንቀራው ኪታብ ውስጥ አንድ የማናውቀው ቃል መኖር የለበትም። በተቻለ መጠን ሁሉንም ልቅም አድርገን ልንይዝ ይገባል። በዚህ መልኩ ስንሄድ ደርስ በጣም እየቀለለን ነው የሚሄደው። ቃላት በቅጡ ሳንይዝ የምንጓዝ ከሆነ ግን ወደላይ በገፋን ቁጥር ይበልጥ እየከበደን ይሄዳል። በዚያ ላይ ቃላት የማንይዝ ከሆነ አጠቃላይ የደርሱን ጭብጥ የመያዝ እድላችን እያነሰ ነው የሚሄደው።

2- መልእክቱን መጨበጥ:-

ከኪታብ ትምህርት ዋናው የሚፈለገው አላማ መልእክቱን መጨበጥ ነው። ቁርኣን የወረደው፣ ሐዲሥ የተላለፈው የቃላት ትርጉም ለማስተማር ሳይሆን ለሰዎች የሚበጃቸውን መልእክት ለማስተላለፍ ነው። በብዛት በሃገራችን የተለመደው የቃል በቃል ትርጉም የማስተማር ዘዴ በዚህ በኩል ጉልህ ክፍተት አለበት። ስለዚህ ለመልእክት በቂ ትኩረት መስጠት ይገባል።

እዚህ ላይ አንድ ወሳኝ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። "የተማርነውን ኪታብ በበቂ ሁኔታ እንደተገነዘብነው መለኪያው ምንድነው?" የሚል። መለኪያው የተማርነውን ኪታብ ለሌላ ማስተማር በሚያስችል መጠን ይዘነዋል ወይ?" ብለን ራሳችንን መጠየቅ ነው። ለራሳችን እውነተኛ ሆነን እንመልስ። አንዳንዴ አስተማሪዎች ሲሳሳቱ "ማግኘታችን" የራስ ሽንገላ ውስጥ እንዳይከተን ልንጠነቀቅ ይገባል። የእውነት ኪታቡን በስርአት ቁጭ ብለን ማስተማር እንችላለን? ካልሆነ ወደሌላ ኪታብ ለመቀጠል ከመጓጓታችን በፊት አጥርተን እንማር። "ይህንን ኪታብ ቀርተነዋል፤ ሌላ ይሁንልን" ከማለታችን በፊት ራሳችንን እንገምግም።

3- ነጠብጣቦችን ማገናኘት:-

በዚህ ክፍል ሁለት ነጥቦችን ነው መጠቆም የፈለግኩት።

1ኛ፦ ማስረጃን ከነጥቡ ጋር፣ በአንድ ባብ (ርእስ) ስር የተደረደሩ የቁርኣን አንቀፆችንና ሐዲሦችን ከርእሱ ጋር ማገናዘብ። እየነጠሉ መረዳት በቂ አይደለም። ይሄ ሐዲሥ እንዴት ነው ማስረጃ የሚሆነው? ይሄ መልእክት ከርእሱ ጋር እንዴት ነው የሚናኘው? እያልን ማስተዋል ይኖርብናል።

2ኛ፦ ከራሳችንና ከህዝባችን ተጨባጭ ጋር ማገናኘት። ይህም የምንማረው ትምህርት ራስንም ወገንንም ለመለወጥ እንዲያግዘን ይረዳናል።

ወላሁ አዕለም

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ገደልነው ሲሉ ህያው ሞተ ሲሉም እየዳነ ዛሬም ድረስ በህይወት ያለ ተንቀሳቃሹ ሰማዕት። ተራማጁ ሸሂድ። የማይነጥፍ የወንድነት ባህር! የፍልስጤማዊያን ኩራት! የዘመኑ አብሪ ኮከብ! የጦር ሊቅ! የኬምስትሪ ደቂቅ። ፍፁም ትሁት አስተዋይና ለስላሳ ቁጥብነትን የተላበሰ ጀግና። መልካም ልብ፣ ደግ ማንነትን የታደለ ወንድ።

ጌታዬ ሆይ!

ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑልወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ

Mahi Mahisho

አሰልጥኖ የሚያሰማራቸው ወታደሮች፣ አብላልቶ የሚተኩሳቸው ሮኬቶች የወራሪዋን ራዳር ጥሰው ሰማዩን እየሰነጣጠቁ ጠላትን ማሸበር ከጀመሩ እነሆ 23 አመታት ተቆጠሩ። የእስራኤል የስለላ ተቋም ሮኬቶቹ ሲሰሩ እንኳ አያቅም። ተምዘግዛጊ ሮኬቶችን እንደታጠቁ ያወቁት በ2001 አየሩን ሰንጥቀው ከተማቸው ውስጥ ሲያርፉ ነው።

ከእነዚህ ሮኬቶች ጀርባ አንድ የኬምስትሪ ምሩቅ አለ። ለዚህ ብሎ የተማረ። ብረትን ከፖታሺየም ናይትሬትና የወዳደቁ እቃዎችን ከማዳበሪያ ጋር ቀምሞ በቆርቆሮ ሲሊንደር አብላልቶ ሮኬቶቹን የሚያዘጋጅ ታንክን በዲንጋይ የገጠመ ፍፁም ለአላህ ያደረ ዓቢድ። ባመሸበት ቦታ የማያድር ባረፈደበት መንደር የማይውል። በእናቱ ቀብር ላይ እንኳ ያልተገኘ ፍፁም ጥንቁቅ።

ሞሳዶች አስማተኛው ሰይጣን ይሉታል። ከጠቅላይ ሚኒስቴር ሽሞን ፔሬዝ እስከ ቢኒያሚን ኔታንያሆ በሰማይ በምድር የሚፈለግ ረብጣ ዶላር መድበው ደህንነቶቻቸውን አሰማርተው የዛሬሀያ ስምንት ዓመት እንዲገደል ትዕዛዝ ያስተላለፉበት የጋዛው ኮማንደር።

በማለዳ ተነስተው ከስክስ ጫማቸውን አጥልቀው ተራራውን ሮጠው ያላገኙት፣ የጥይት አሩር እየተኮሱ ቦንብ ከአውሮፕላን ቢያዘንቡ ፍፁም ሊገሉት ያልቻሉት የፍልስጤማዊያን ቁልፍ ሰው።

በእግሮቹ የሚራመድ ሸሂድ ቢሉት አትገረሙ። በእርግጥም ልክ ናቸው። ብዙ ጊዜ ከሞት ድኗል። የሞሳድ ደህንነቶች ከጓደኞቹ በአንዱ የእጅ ስልክ ላይ የተጠመደውን ፈንጂ ተኩሰው ሲገድሏቸው፣ መኪናው በድሮን ተደብድባ ሁለት ጠባቂዎቹና አንድ ረዳቱ ሲገደሉ እርሱ ተርፏል። የተማረበትን ዩንቨርስቲ ሊጎበኝ በሄደበት F1 የጦር ጀቶች ዩንቨርስቲውን ዶግ አመድ ሲያደርጉት በህይወት ድኗል። የእስራኤል አየር ኃይል ጋዛ በሚገኘው መኖርያ ቤቱ ላይ ድብደባ ፈፅሞ ሚስቱና ሁለት እንቦቃቅላ ልጆቹን ገድሎ የሙጃሂዶቹን አከርካሪ አጥንት ሰበርነው አዎ አስወገድነው ገደልነው ብለው በደስታ ውስኪ ሲራጩ ነፍሱ አዛኙንና ኃያሉን አላህ ለመገናኘት አልተፈቀደላትም ነበርና አለሁ ብሎ ብቅ ብሏል።

ሙሐመድ ዲያብ ኢብራሒም ይሰኛል። ፍልስጤማዊያን ደይፍ ይሉታል እንግዳ እንደማለት ነው። በእርግጥም እርሱ በወራሪዋ ደህንነቶች ታድኖ ሊገደል፣ ተጠፍሮም ሊያዝ ያልቻለ አሳዳጆቹ እጅ ሳይገባ ሀያ ስምንት አመታቶችን ያስቆጠረ ሁሌም እንግዳ ሰው ነው።

የሙስሊሞች ለቅሶ የእናቶች እሪታ፣ የልጆች ስቅስቅታ በጆሮው ሲንቆረቆር ለበይክ ብሎ በለጋ ዕድሜው የተነሳ ወጣትነቱን በትግል ያሳለፈ ትንታግ ነው። ወንድሞቹ ሲሞሻለቁ፣ እህቶቹ በድምፅ አልባ መሳሪያ ሲወቁ ትከሻም ልቡም ለመሸከም አልፈቀዱለትም፡፡ ድንቡሽቡሽ ፊት ያላቸው እንቦቃቅላ ልጆቹን ትቶ፣ የእናቱን የእጅ ደበሳ ርቆ በጂሃድ ሜዳ ላይ ተሰየመ፡፡

የብሩህ አዕምሮ ባለቤት የመሐፈዝ አቅሙ ከፍተኛ የሰማውን ቀብ፣ ያየውን ልቅም አድርጎ የሚይዝ ፈጣን ነው። በየትኛውም ቴሌቪዥን ታይቶ አይታወቅም። ምንም አይነት ቴክኖሎጂ የማይጠቀም ባለ ዊልቸሩ የጦር መሪ።

አባቱ ልብስ እየሰፉ በአነስተኛ የዶሮ እርባታ እንቁላል እየሸጡ ያሳደጉት ልጅ ዛሬ ስሙን እንጂ ማንነቱን ለማወቅ ከብዷል። አላህ ረጅም ሐያት ከሙሉ አፊያ ጋር!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

https://ummalife.com/post/158300

Umma Life ምንድነው? ማነው የሰራው? ዓላማውስ ምንድነው?

ይህ Umma Life(ኡማ ላይፍ) የተሰኘው አፕልኬሽን ልክ እንደ ፌስቡክ አካውንት ከፍተን የራሳችንን ፅሁፎች፣ ምስሎች እና ቪድዮዎች ጭምር ማጋራት የምንችልበት ፕላትፎርም ሲሆን ከፌስቡክ የሚለየው እያንዳንዱ የምንለቃቸው ነገሮች ከሸሪዐ አስተምህሮ ጋር የሚጋጭ መሆን የለበትም።

የዚህ ፕላትፎርም መስራችና ስራ አስኪያጅ "ዒሳ ዳገስታኒ(Isa Dagestani) ሲባል በዜግነት ቱርካዊ ነው።

ይህን ፕላትፎርም ለማዘጋጀት እንደምክንያት ሆኖ ያነሳሳቸው በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሀሳቡን ሲያንፀባርቅ ሀሳቡን/ፅሁፉን ከማገድ አልፈው አካውንቱን እስከመዝጋት በመድረሳቸው ነው።

Non-ሙስሊም የሆኑ ሰዎች የፕላትፎርሙን ህገ_ደንብ ካከበሩ መቀላቀል እንደሚችሉ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።

እኔ ያየሁዋቸው መስተካከል ያለባቸው የተወሰኑ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ የኮሜንት ሴክሽኑ ክፍት ቢሆንም ሀሳብ ማስፈር አንችልም። በተጨማሪ አንድ ጊዜ ፖስት ካደረግን በኋላ Edit ማድረግ አንችልም።

አሁን ቨርዥን 2.4.15 ላይ ደርሷል።

አፕልኬሽኑን ለማግኘት ተቸግረናል ላላችሁኝ በሚከተለው የቴሌግራም ሊንክ ገብታችሁ በቀላሉ ማውረድ ትችላላችሁ።

👇👇👇👇👇

https://t.me/AmmarAli75/623

ተጠቀሙበት! ለሌሎችም አድርሱት!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group