የዑለማኦቹ መልስ
አንድ ሰው ኢብኑ አልጀውዚ ረሒመሁሏህ ዘንድ መጣና ‹ተስቢሕ ላድርግ /አላህን ላወድስ/ ፤ ወይንስ ኢስቲግፋር /ምህረት/ ልጠይቅ የቱ ይሻለኛል?› አላቸው፡፡ እርሣቸውም ‹አንድ ሰው ልብሱ የቆሸሸ እንደሆነ ሽቶ ከመቀባት ይልቅ ማጠቡ ይሻለዋል፡፡› አሉት፡፡ (ከአላህ ምህረት መጠየቅን አስቀድም፡፡) ማለታቸው ነው፡፡
ኢማሙ አሽሻፊዒይ ‹ዓሊም የማያውቀውን ጥያቄ ይጠየቃል ወይ?› ተብለው ተጠየቁ፡፡ እርሣቸውም ‹ዓሊም የሚያውቀውንም የማያውቀውንም ሊጠየቅ ይችላል፡፡ የሚያውቀውን ይመልሣል፤ የማያውቀውን ይማራል፤ ጃሂል ግን ሲጠየቅ ይቆጣል፤ ለመማርም ዝግጁ አይደለም፡፡› አሉ፡፡
ኢማም አሽሻፊዕይ ‹ በእድሜ ወጣት ሆነው ሣለ ለምን ምርኩዝ ይይዛሉ?› ተብለው ተጠየቁ፡፡ እርሣቸውም ‹ መንገደኛ መሆኔን መርሣት እንደሌለብኝ እራሴን ለማስታወስ፡፡› ብለው መለሱ፡፡