ለዒልም ተማሪዎች ጉርሻ
~
ኪታብ ከሚቀሩ ተማሪዎች ውስጥ ብዙዎቹ ለልፋታቸው የሚመጥን በቂ ግንዛቤ አይጨብጡም። ከነዚህ በተቃራኒ ደግሞ በቂራአት ማእድ ላይ ያላቸው ቆይታ አነስተኛ ሆኖ የተሻለ የሚጠቀሙ አሉ። ልዩነቱ ከምን የመነጨ ነው? ለዚህ ልዩነት ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ አድምቶ አለመቅራት የሚያመጣው ክፍተት ነው። የብዙ ተማሪዎች አያያዝ የለብ ለብ ነው። አንዱን ኪታብ ጥንቅቅ አድርገን ሳንይዝ ከፍ ወዳለው ለመግባት ያለን ጉጉት ብዙ ቀርተናል የሚል ጉጉታችንን ከማርካት ባለፈ ብስለት እንዳይኖረን ሊያደርገን ይችላል።
ይህንን ክፍተታችንን ለመድፈን ከሚያግዙ መንገዶች ውስጥ ሶስቱን ላንሳ፦
1- ቃላት ለቀማ
2- መልእክቱን መጨበጥ
3- ነጠብጣቦችን ማገናኘት
ላብራራቸው።
1- ቃላት ለቀማ፦
ከምንቀራው ኪታብ ውስጥ አንድ የማናውቀው ቃል መኖር የለበትም። በተቻለ መጠን ሁሉንም ልቅም አድርገን ልንይዝ ይገባል። በዚህ መልኩ ስንሄድ ደርስ በጣም እየቀለለን ነው የሚሄደው። ቃላት በቅጡ ሳንይዝ የምንጓዝ ከሆነ ግን ወደላይ በገፋን ቁጥር ይበልጥ እየከበደን ይሄዳል። በዚያ ላይ ቃላት የማንይዝ ከሆነ አጠቃላይ የደርሱን ጭብጥ የመያዝ እድላችን እያነሰ ነው የሚሄደው።
2- መልእክቱን መጨበጥ:-
ከኪታብ ትምህርት ዋናው የሚፈለገው አላማ መልእክቱን መጨበጥ ነው። ቁርኣን የወረደው፣ ሐዲሥ የተላለፈው የቃላት ትርጉም ለማስተማር ሳይሆን ለሰዎች የሚበጃቸውን መልእክት ለማስተላለፍ ነው። በብዛት በሃገራችን የተለመደው የቃል በቃል ትርጉም የማስተማር ዘዴ በዚህ በኩል ጉልህ ክፍተት አለበት። ስለዚህ ለመልእክት በቂ ትኩረት መስጠት ይገባል።
እዚህ ላይ አንድ ወሳኝ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። "የተማርነውን ኪታብ በበቂ ሁኔታ እንደተገነዘብነው መለኪያው ምንድነው?" የሚል። መለኪያው የተማርነውን ኪታብ ለሌላ ማስተማር በሚያስችል መጠን ይዘነዋል ወይ?" ብለን ራሳችንን መጠየቅ ነው። ለራሳችን እውነተኛ ሆነን እንመልስ። አንዳንዴ አስተማሪዎች ሲሳሳቱ "ማግኘታችን" የራስ ሽንገላ ውስጥ እንዳይከተን ልንጠነቀቅ ይገባል። የእውነት ኪታቡን በስርአት ቁጭ ብለን ማስተማር እንችላለን? ካልሆነ ወደሌላ ኪታብ ለመቀጠል ከመጓጓታችን በፊት አጥርተን እንማር። "ይህንን ኪታብ ቀርተነዋል፤ ሌላ ይሁንልን" ከማለታችን በፊት ራሳችንን እንገምግም።
3- ነጠብጣቦችን ማገናኘት:-
በዚህ ክፍል ሁለት ነጥቦችን ነው መጠቆም የፈለግኩት።
1ኛ፦ ማስረጃን ከነጥቡ ጋር፣ በአንድ ባብ (ርእስ) ስር የተደረደሩ የቁርኣን አንቀፆችንና ሐዲሦችን ከርእሱ ጋር ማገናዘብ። እየነጠሉ መረዳት በቂ አይደለም። ይሄ ሐዲሥ እንዴት ነው ማስረጃ የሚሆነው? ይሄ መልእክት ከርእሱ ጋር እንዴት ነው የሚናኘው? እያልን ማስተዋል ይኖርብናል።
2ኛ፦ ከራሳችንና ከህዝባችን ተጨባጭ ጋር ማገናኘት። ይህም የምንማረው ትምህርት ራስንም ወገንንም ለመለወጥ እንዲያግዘን ይረዳናል።
ወላሁ አዕለም